Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 40:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በሞዓብም በአሞንም ልጆች መካከል በኤዶምያስም በምድርም ሁሉ ላይ የነበሩ አይሁድ ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የይሁዳን ቅሬታ እንዳስቀረ፥ የሳፋንንም ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በሞዓብ፣ በአሞን፣ በኤዶምና በሌሎች አገሮች ሁሉ የነበሩ አይሁድ በሙሉ የባቢሎን ንጉሥ፣ ሰዎችን በይሁዳ እንዳስቀረና የሳፋን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው እንደ ሾመ በሰሙ ጊዜ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እንዲሁም ደግሞ በሞዓብም፥ በአሞንም ልጆች መካከል፥ በኤዶምያስም በምድሪቱም ሁሉ ላይ የነበሩ አይሁድ ሁሉ፥ የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ትሩፍ እንዳስቀረ፥ የሳፋንንም ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ይህ በዚህ እንዳለ በሞአብ፥ በዐሞን፥ በኤዶምና በሌሎችም አገሮች የሚኖሩ እስራኤላውያን የባቢሎን ንጉሥ ጥቂት የአይሁድ ቅሪቶችን ማስቀረቱንና ለእነርሱም ገዳልያን ገዢ አድርጎ መሾሙን ሰሙ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በሞ​ዓ​ብና በአ​ሞ​ንም ልጆች መካ​ከል፥ በኤ​ዶ​ም​ያ​ስም፥ በም​ድ​ርም ሁሉ ላይ የነ​በሩ አይ​ሁድ ሁሉ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የይ​ሁ​ዳን ቅሬታ እን​ዳ​ስ​ቀረ፥ የሳ​ፋ​ን​ንም ልጅ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በላ​ያ​ቸው እንደ ሾመው ሰሙ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 40:11
23 交叉引用  

ዔሳውም በሴይር ተራራ ተቀመጠ ዔሳውም ኤዶም ነው።


በምዕራብም በኩል በፍልስጥኤማውያን ጫንቃ ላይ እየበረሩ ይወርዳሉ፥ የምሥራቅንም ልጆች በአንድነት ይበዘብዛሉ፥ በኤዶሚያስና በሞአብም ላይ እጃቸውን ይዘረጋሉ፥ የአሞንም ልጆች ለእነርሱ ይታዘዛሉ።


ከሞዓብ የተሰደዱት ከአንቺ ጋር ይቀመጡ፥ ከሚያጠፋቸው ፊት መጋረጃ ሁኛቸው። የሚያስጨንቁ አልቀዋል፥ ጥፋትም ቀርቷል፥ ይጨቍኑ የነበሩ ከምድር ጠፍተዋል።


በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ ለማላገጫና ለእርግማን ይሆኑ ዘንድ በምድር መንግሥታት ሁሉ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።


እስማኤልም በምጽጳ የነበረውን የሕዝቡን ቅሬታ ሁሉ፥ የንጉሡን ሴቶች ልጆች የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ የሰጠውን በምጽጳ የቀሩትን ሕዝብ ሁሉ ማረካቸው፥ የናታንያም ልጅ እስማኤል ማርኮ ወደ አሞን ልጆች ይሄድ ዘንድ ተነሣ።


የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የጭፍራ አለቆችም ሁሉ በይሁዳ ምድር ለመቀመጥ ከተሰደዱባቸው ከአሕዛብ ሁሉ የተመለሱትን የይሁዳን ቅሬታ ሁሉ፥


ወንዶችንና ሴቶችን ልጆችንም የንጉሡንም ሴቶች ልጆች፥ የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ከሳፋን ልጅ ከአኪቃም ልጅ ከጎዶልያስ ጋር የተዋቸውን ሰዎች ሁሉ፥ ነቢዩንም ኤርምያስን የኔርያንም ልጅ ባሮክን ወሰዱ፥


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ኤዶምያስ በይሁዳ ቤት ላይ በቀል አድርጎአልና፥ ቂም ይዞአልና፥ ብድራትንም አስከፍሎአልና፥


የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ አሞን ልጆች አቅንተህ ትንቢት ተናገርባቸው።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእጅህ አጨብጭበሃልና፥ በእግርህም አሸብሽበሃልና፥ በእስራኤልም ምድር ላይ በነፍስህ ንቀት ሁሉ ደስ ብሎሃልና


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሞዓብና ሴይር፦ እነሆ፥ የይሁዳ ቤት እንደ አሕዛብ ሁሉ ነው ብለዋልና


በጎቼ በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ሁሉ ላይ ተቅበዝብዘዋል፥ በጎቼም በምድር ፊት ሁሉ ላይ ተበትነዋል፥ የሚሻም የሚፈልግም አልነበረም።


የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ በላዩ ደስ እንዳለህ፥ እንዲሁ አደርግብሃለሁ፥ የሴይር ተራራ ሆይ፥ አንተና ኤዶምያስ ሁሉ ሁለንተናውም ባድማ ትሆናላችሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።


የዘላለም ጥል ስላለህ በመከራቸውም ጊዜ በኋለኛይቱ የኃጢአታቸው ቀጠሮ ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በሰይፍ እጅ ጥለሃቸዋልና


ከአንቺም ሢሶው በቸነፈር ይሞታል፥ በመካከልሽም በራብ ያልቃል፥ ሢሶውም በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃል፥ ሢሶውንም ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ በኋላቸውም ሰይፍ እመዝዛለሁ።


ከዚያም በጥቂቱ ውሰድ በመጐናጸፊያህም ጫፍ ቋጥራቸው።


የእስራኤልም ልጆች ተጓዙ፥ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በዮርዳኖስ ማዶ ባለው በሞዓብ ሜዳ ሰፈሩ።


እስራኤልም በሰጢም ተቀመጡ፤ ሕዝቡም ከሞዓብ ልጆች ጋር ያመነዝሩ ጀመር።


ሕዝቡንም ወደ አምላኮቻቸው መሥዋዕት ጠሩ፤ ሕዝቡም በሉ፥ ወደ አምላኮቻቸውም ሰገዱ።


እንዲህም ሆነ፥ ከአንድ ወር በኋላ አሞናዊው ናዖስ ወጣ፥ በኢያቢስ ገለዓድም ሰፈረ፥ የኢያቢስም ሰዎች ሁሉ፦ ቃል ኪዳን አድርግልን፥ እኛም እንገዛልሃለን አሉት።


የአሞንም ልጆች ንጉሥ ናዖስ እንደ መጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ንጉሣችሁ ሳለ፦ እንዲህ አይሁን፥ ነገር ግን ንጉሥ ይንገሥልን አላችሁኝ።


跟着我们:

广告


广告