Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 4:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በይሁዳ ዘንድ ተናገሩ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩና፦ በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ በሉ፥ ጮኻችሁም፦ ሁላችሁ ተሰብሰቡ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ በሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ ‘በምድሪቱ ሁሉ መለከትን ንፉ’ ብላችሁ፤ በይሁዳ ተናገሩ፣ በኢየሩሳሌም ዐውጁ፤ ጩኹ፤ እንዲህም በሉ፤ ‘በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ወደ ተመሸጉት ከተሞች እንሽሽ!’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በይሁዳ ላይ ተናገሩ በኢየሩሳሌምም ላይ አውጁ፦ “በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ በሉ፤ ጮኻችሁም፦ ‘ሁላችሁ ተሰብሰቡ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ’ በሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በምድሪቱ ሁሉ ላይ መለከት ንፉ! ድምፃችሁንም ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ! የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ወደተመሸጉ ከተሞች እንዲሸሹ ንገሩአቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በይ​ሁዳ ዘንድ ተና​ገሩ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ላይ አው​ሩና፦ በሀ​ገ​ሪቱ ላይ መለ​ከት ንፉ በሉ፤ ጮኻ​ች​ሁም፦ ሁላ​ችሁ ተሰ​ብ​ሰቡ፤ ወደ ተመ​ሸ​ጉ​ትም ከተ​ሞች እን​ግባ በሉ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 4:5
16 交叉引用  

ባለፈም ጊዜ ይወስዳችኋል፥ ማለዳ ማለዳ ቀንና ሌሊት ያልፋል፥ ወሬውንም ማስተዋል ድንጋጤ ይሆናል።


የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስማ፥ ለይሁዳም ሰዎች በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ተናገር፥


ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደዚህች ምድር በመጣ ጊዜ፦ ኑ ከከለዳውያን ሠራዊትና ከሶርያ ሠራዊት ፊት የተነሣ ወደ ኢየሩሳሌም እንሂድ አልን፥ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ተቀመጥን።


ይህን በያዕቆብ ቤት አውሩ፥ በይሁዳም አሰሙ፦


እናንተ የብንያም ልጆች፥ ክፉ ነገር ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ይጐበኛልና ከኢየሩሳሌም ውስጥ ሽሹ፥ በቴቁሔ መለከቱን ንፉ፥ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት አንሡ።


ዝም ብለን ለምን እንቀመጣለን? እግዚአብሔርን ስለ በደልን አምላካችን እግዚአብሔር አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም ውኃ አጠጥቶናልና ተሰብስባችሁ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንግባ በዚያም እንጥፋ።።


ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ያወራስ ዘንድ የእግዚአብሔር አፍ ለማን ተናገረ? ሰው እንዳያልፍባት ምድርስ ስለምን ጠፋች፥ እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተቃጠለች?


መለከቱን ነፍተዋል ሁሉንም አዘጋጅተዋል፥ ነገር ግን መዓቴ በብዙዎች ሁሉ ላይ ነውና ወደ ሰልፍ የሚሄድ የለም።


መለከትን ወደ አፍህ አቅርብ፥ ቃል ኪዳኔን ተላልፈዋልና፥ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና በእግዚአብሔር ቤት ላይ እንደ ንስር ይመጣል።


የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥ እርሱም ቀርቦአልና በጽዮን መለከትን ንፉ፥ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ እሪ በሉ፥ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ፥ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥


ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? ወይስ ክፉ ነገር በከተማ ላይ የመጣ እንደ ሆነ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?


አንበሳው አገሣ፥ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፥ ትንቢት የማይናገር ማን ነው?


ሁለት የብር መለከቶች አጠፍጥፈህ ለአንተ አድርግ፤ ማኅበሩን ለመጥራት ከሰፈራቸውም ለማስጓዝ ይሁኑልህ።


ሁለቱም መለከቶች በተነፉ ጊዜ ማኅበሩ ሁሉ ወደ አንተ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይሰብሰቡ።


እስኪጠፉም ድረስ ኢያሱና የእስራኤል ልጆች በታላቅ መምታት መምታታቸውን በፈጸሙ ጊዜ፥ ከእነርሱም ያመለጡት ወደ ተመሸገ ከተማ በገቡ ጊዜ፥


跟着我们:

广告


广告