Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 4:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 መከራ በመከራ ላይ ተጠርቶአል፥ ምድርም ሁሉ ተበዝብዛለችና፥ በድንገትም ድንኳኔ በቅጽበት ዓይንም መጋረጃዎቼ ጠፉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ጥፋት በጥፋት ላይ ይመጣል፤ ምድሪቱም በሞላ ባድማ ትሆናለች፤ ድንኳኔ በድንገት፣ መጠለያዬም በቅጽበት ጠፋ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 መከራ በመከራ ላይ ተጠርቶአል፤ ምድሪቱም ሁሉ ጠፍታለችና፤ በድንገትም ድንኳኔ በዐይን ቅጽበትም መጋረጃዎቼ ጠፉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 መቅሠፍት በመቅሠፍት ላይ ይደራረባል፤ አገሪቱ በሙሉ ፈራርሳ ጠፍ ሆናለች፤ ድንኳኖቻችን በድንገት ወደሙ፤ መጋረጃዎቻቸውም በቅጽበት ተቀደዱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 መከራ በመ​ከራ ላይ ተጠ​ር​ቶ​አል፤ ምድር ሁሉ ተዋ​ር​ዳ​ለ​ችና፤ በድ​ን​ገ​ትም ድን​ኳኔ ጠፋ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችም ተቀ​ዳ​ደዱ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 4:20
29 交叉引用  

እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ለእስራኤል ልጆች፦ እናንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ናችሁ፥ አንድ ጊዜ በእናንተ መካከል ብወጣ አጠፋችኋለሁ፤ አሁንም የማደርግባችሁን አውቅ ዘንድ ጌጣችሁን ከእናንተ አውጡ በላቸው አለው።


የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ አልቅሱ፥ ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ እንደሚመጣ ጥፋት ይመጣል።


ልቤ ስለ ሞዓብ ጮኸ፥ ከእርስዋ የሚሸሹ ወደ ዞዐር ወደ ዔግላት ሺሊሺያ ኮበለሉ፥ በሉሒት ዓቀበት ላይ እያለቀሱ ይወጣሉ፥ በሖሮናይምም መንገድ የዋይታ ጩኽት ያነሣሉ።


የባዓላችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፥ ዓይኖችህ የሰላም ማደሪያ፥ ካስማውም ለዘላለም የማይነቀል አውታሩም ሁሉ የማይበጠስ፥ የማይወገድ ድንኳን የሆነውን ኢየሩሳሌምን ያያሉ።


አሁን ግን በአንድ ቀን እነዚህ ሁለት ነገሮች፥ የወላድ መካንነትና መበለትነት፥ በድንገት ይመጡብሻል፥ ስለ መተቶችሽ ብዛትና ስለ አስማቶችሽ ጽናት ፈጽመው ይመጡብሻል።


የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፥ አትቈጥቢ፥ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ።


ባድማ አድርገውታል፥ ፈርሶም ወደ እኔ ያለቅሳል፥ ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች በልቡም የሚያስባት የለም።


አሳዳጆቼ ይፈሩ፥ እኔ ግን አልፈር፥ እነርሱ ይደንግጡ፥ እኔ ግን አልደንግጥ፥ ክፉንም ቀን አምጣባቸው፥ በሁለት እጥፍ ጥፋት አጥፋቸው።


ዓላማውን የምመለከት፥ የመለከቱንስ ድምፅ የምሰማ እስከ መቼ ነው?


እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች፥ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋትም።


ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና ወደ ጽዮን ዓላማን አንሡ፥ ሽሹ፥ አትዘግዩ።


ዓይኖቻችንም እንባ እንዲያፈስሱ የዓይናችንም ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ ፈጥነው ለእኛ ልቅሶውን ይያዙ።


ድንጋጤና ቍጣ፥ ጥፋትና ቅጥቃጤ ሆነብን።


ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ይልቁንስ ሰውንና እንስሳን ከእርስዋ አጠፋ ዘንድ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ ፍርዶቼን፥ ሰይፍንና ራብን ክፉዎችንም አውሬዎች ቸነፈርንም፥ ስሰድድባት!


የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና ለቀኑ ወዮ! እርሱም ሁሉን ከሚችል ከአምላክ ዘንድ እንደ ጥፋት ይመጣል።


እስከዚህም ድረስ ባትሰሙኝ፥ ስለ ኃጢአታችሁ በቅጣታችሁ ላይ ሰባት እጥፍ እጨምራለሁ።


በእንቢተኝነትም ብትሄዱብኝ ባትሰሙኝም፥ እንደ ኃጢአታችሁ መጠን በመቅሠፍት ላይ ሰባት እጥፍ እጨምራለሁ።


እኔ ደግሞ በእንቢተኝነት እሄድባችኋለሁ፤ ስለ ኃጢአታችሁም ሰባት እጥፍ እመታችኋለሁ።


እኔ ደግሞ በቍጣ እሄድባችኋለሁ፤ ስለ ኃጢአታችሁም ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ።


የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፥ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።


ሁሉን በቅጽበት አጠፋቸው ዘንድ ከዚህ ማኅበር መካከል ፈቀቅ በሉ።


ከዚህ ማኅበር መካከል ፈቀቅ በሉ፥ እኔም በቅጽበት አጠፋቸዋለሁ። በግምባራቸውም ወደቁ።


ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።


በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር፥ ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊገረም ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኃይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።


跟着我们:

广告


广告