Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 39:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ኢየሩሳሌምም በተያዘች ጊዜ፥ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በዘጠነኛው ዓመት በአሥረኛው ወር የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ከበቡአት፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ኢየሩሳሌም የተያዘችው እንዲህ ነበር፤ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሰራዊቱን ሁሉ አሰልፎ በመምጣት ኢየሩሳሌምን ከበባት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በዘጠነኛው ዓመት፥ በአሥረኛው ወር፥ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ከበቡአት፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር መጥቶ በኢየሩሳሌም ላይ ከበባ አደረገ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርና ሠራ​ዊቱ ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጥ​ተው ከበ​ቡ​አት።

参见章节 复制




ኤርምያስ 39:1
16 交叉引用  

ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጕልማሶቻቸውን በቤተመቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጕልማሳውንና ቈንጆይቱን ሽማግሌውንና አሮጌውን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።


በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በአሥረኛው ዓመት፥ በናቡከደነፆር በአሥራ ስምንተኛው ዓመት፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ ከእጁም ግዛት በታች ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ አሕዛብም ሁሉ ኢየሩሳሌምንና ከተሞችዋን ሁሉ ይወጉ በነበረ ጊዜ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው።


እነሆ፥ አዝዛለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ወደዚህችም ከተማ እመልሳቸዋለሁ፥ እርስዋንም ይወጋሉ ይይዙአትማል በእሳትም ያቃጥሉአታል፥ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የሌለበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ቍጣዬና መዓቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፥ እንዲሁ ወደ ግብጽ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ ይፈስስባችኋል፥ እናንተም ለጥላቻና ለመደነቂያ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ትሆናላችሁ፥ ይህንም ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩትም።


ሴዴቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አንድ ዓመት ጕልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፥ እናቱም አሚጣል የተባለች የሊብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ዛፎችዋን ቍረጡ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ አፈርን ደልድሉ፥ ይህች ከተማ የምትቀሠፍ ናት፥ መካከልዋ ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።


እንዲህም ሆነ፥ በተማረክን በአሥራ ሁለተኛው ዓመት በአሥረኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን ከኢየሩሳሌም ያመለጠ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ፦ ከተማይቱ ተመታች አለኝ።


የብረት ምጣድም ወስደህ በአንተና በከተማይቱ መካከል ለብረት ቅጥር አድርገው፥ ፊትህንም ወደ እርስዋ አቅና፥ የተከበበችም ትሆናለች አንተም ትከብባታለህ። ይህም ለእስራኤል ቤት ምልክት ይሆናል።


በተማረክን በሀያ አምስተኛው ዓመት በዓመቱ መጀመሪያ ከወሩ በአሥረኛው ቀን፥ ከተማይቱ ከተመታች በኋላ በአሥራ አራተኛው ዓመት፥ በዚያው ቀን የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረ እርሱም ወደዚያ ወሰደኝ።


የመከበብም ወራት በተፈጸመ ጊዜ በከተማይቱ መካከል ሢሶውን በእሳት ታቃጥላለህ፥ ሢሶውንም ወስደህ ዙሪያውን በጐራዴ ትመታለህ፥ ሢሶውንም ወደ ነፋስ ትበትናለህ እኔም በኋላቸው ጐራዴ እመዝዛለሁ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፥ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።


እግዚአብሔርም አንተን በአንተም ላይ የምታነግሠውን ንጉሥ አንተና አባቶችህ ወዳላወቃችኋቸው ሕዝብ ይወስድሃል፤ በዚያም ሌሎችን የእንጨትና የድንጋይ አማልክት ታመልካለህ።


跟着我们:

广告


广告