Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 38:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ኤርምያስንም ወሰዱት በግዞት ቤቱም አደባባይ ወደ ነበረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጕድጓድ ውስጥ ጣሉት፥ ኤርምያስንም በገመድ አወረዱት። በጕድጓድም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አልነበረበትም፥ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህ ኤርምያስን ወስደው፣ በዘበኞች አደባባይ በነበረው በንጉሡ ልጅ በመልክያ የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ በገመድም ኤርምያስን ወደ ጕድጓዱ አወረዱት። ጕድጓዱም ጭቃ እንጂ ውሃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ዘልቆ ገባ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ኤርምያስንም ወሰዱት፤ በእስር ቤቱም አደባባይ ወደነበረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጉድጓድ ውስጥ ኤርምያስን በገመድ አውርደው ጣሉት። በጉድጓድም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ስለዚህም እኔን ይዘው በቤተ መንግሥቱ አደባባይ በሚገኘው ወደ ንጉሥ ልጅ ወደ መልክያ የውሃ ጒድጓድ ውስጥ በገመድ ቊልቊል በመልቀቅ ወደ ታች አወረዱኝ፤ በጒድጓዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውሃ አልነበረበትም፤ እኔም በጭቃው ውስጥ ሰመጥሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ኤር​ም​ያ​ስ​ንም ወሰ​ዱት፤ በግ​ዞት ቤትም አደ​ባ​ባይ ወደ ነበ​ረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መል​ክያ ጕድ​ጓድ ውስጥ ጣሉት፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በገ​መድ አወ​ረ​ዱት። በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም፤ ኤር​ም​ያ​ስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 38:6
19 交叉引用  

በብዙ ኅብር ያጌጠቺቱ ቀሚሱን ገፈፋት ወስደውም ወደ ጕድጓድ ጣሉት ጕድጓዱም ውኃ የሌለበት ደረቅ ነበረ።


በዚያን ጊዜም የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከብቦ ነበር፥ ነቢዩም ኤርምያስ በይሁዳ ንጉሥ ቤት በነበረው በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ነበር።


ንጉሡም ጸሐፊውን ባሮክንና ነቢዩን ኤርምያስን ይይዙ ዘንድ የንጉሡን ልጅ ይረሕምኤልንና የዓዝርኤልን ልጅ ሠራያን የዓብድኤልንም ልጅ ሰሌምያን አዘዘ፥ እግዚአብሔር ግን ሰወራቸው።


ኤርምያስም ወደ ጕድጓድ ቤት ወደ ጓዳዎቹ ገባ፥ ኤርምያስም በዚያ ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኋላ፥


ንጉሡም ሴዴቅያስ አዘዘ፥ ኤርምያስንም በግዞት ቤት አደባባይ አኖሩት፥ እንጀራም ሁሉ ከከተማ እስኪጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እንጀራ ከጋጋሪዎች መንገድ ይሰጡት ነበር። እንዲሁም ኤርምያስ በግዞት ቤት አደባባይ ተቀምጦ ነበር።


ኤርምያስንም በገመዱ ጐተቱት ከጕድጓድም አወጡት፥ ኤርምያስም በግዞት ቤት አደባባይ ተቀመጠ።


እነሆ፥ በይሁዳ ንጉሥ ቤት የቀሩትን ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ያወጣሉ፥ እነዚያም ሴቶች፦ ባለምዋሎችህ አታልለውሃል አሸንፈውህማል፥ እግሮችህ ግን አሁን በጭቃ ውስጥ ከገቡ እነርሱ ከአንተ ወደ ኋላ ተመልሰዋል ይላሉ።


የዚያን ጊዜም ንጉሡ አዘዘ፥ ዳንኤልንም አምጥተው በአንበሶች ጕድጓድ ጣሉት፥ ንጉሡም ተናገረ ዳንኤልንም፦ ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ እርሱ ያድንህ አለው።


ለአንቺም ደግሞ ስለ ቃል ኪዳንሽ ደም፥ እስሮችሽን ውኃ ከሌለበት ጕድጓድ አውጥቻለሁ።


እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸ።


የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና።


跟着我们:

广告


广告