Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 37:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የፈርዖንም ሠራዊት ከግብጽ ወጣ፥ ኢየሩሳሌምንም ከብበዋት የነበሩ ከለዳውያን ይህን ወሬ በሰሙ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ተመለሱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የፈርዖንም ሰራዊት ከግብጽ ወጥቶ ነበርና ኢየሩሳሌምን ከብበው የነበሩት ባቢሎናውያን ይህን ሲሰሙ ኢየሩሳሌምን ለቅቀው ሄዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የፈርዖንም ሠራዊት ከግብጽ ወጣ፤ ኢየሩሳሌምንም ከብበዋት የነበሩ ከለዳውያን ይህን ወሬ በሰሙ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ተመለሱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በዚያን ጊዜ የባቢሎን ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከበበ፤ ነገር ግን የግብጽ ሠራዊት ድንበሩን አልፎ መምጣቱን በሰማ ጊዜ ወደ ኋላው አፈገፈገ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የፈ​ር​ዖ​ንም ሠራ​ዊት ከግ​ብፅ ወጣ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ከብ​በ​ዋት የነ​በሩ ከለ​ዳ​ው​ያን ይህን ወሬ​አ​ቸ​ውን በሰሙ ጊዜ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 37:5
7 交叉引用  

የባቢሎንም ንጉሥ ለግብጽ ንጉሥ የነበረውን ሁሉ ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ወስዶ ነበርና የግብጽ ንጉሥ ከዚያ ወዲያ ከአገሩ አልወጣም።


የይሁዳንም ንጉሥ ሴዴቅያስንና አለቆቹን ለጠላቶቻቸው እጅ ነፍሳቸውንም ለሚሹአት እጅ ከእናንተም ለተመለሱት ለባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ።


የከለዳውያንም ሠራዊት ከፈርዖን ሠራዊት ፊት የተነሣ ከኢየሩሳሌም በተመለሰ ጊዜ፥


የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከእኔ ትጠይቁ ዘንድ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ እነሆ፥ ሊረዳችሁ የወጣው የፈርዖን ሠራዊት ወደ አገሩ ወደ ግብጽ ይመለሳል።


እርሱ ግን በእርሱ ላይ ሸፈተ ፈረሶችንና ብዙንም ሕዝብ ይሰጡት ዘንድ መልእክተኞችን ወደ ግብጽ ላከ። በውኑ ይከናወንለት ይሆንን? ይህንስ ያደረገ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንንስ አፍርሶ ያመልጣልን?


ብዙዎችን ነፍሳት ለማስወገድ አፈርን በደለደሉ ምሽግም በሠሩ ጊዜ፥ ፈርዖን ከብዙ ሠራዊቱና ከታላቁ ጉባኤው ጋር በሰልፍ አይረዳውም።


跟着我们:

广告


广告