Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 36:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ኤርምያስም የኔርያን ልጀ ባሮክን ጠራ፥ ባሮክም እግዚአብሔር ለእርሱ የተናገረውን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ በመጽሐፉ ክርታስ ጻፈ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ኤርምያስም የኔርያን ልጅ ባሮክን ጠራው፤ ባሮክም እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ ተቀብሎ በብራናው ላይ ጻፈ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ኤርምያስም የኔርያን ልጅ ባሮክን ጠራ፥ ባሮክም ኤርምያስ እየነገረው ጌታ ለእርሱ የተናገረውን ቃላት ሁሉ በመጽሐፉ ክርታስ ጻፈ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ስለዚህም የኔሪያን ልጅ ባሮክን ጠርቼ እግዚአብሔር የነገረኝን ቃል ሁሉ አንድ በአንድ እየነገርኩት በሚጠቀለል ብራና ጻፈው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ኤር​ም​ያ​ስም የኔ​ር​ዩን ልጅ ባሮ​ክን ጠራ፤ ባሮ​ክም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ርሱ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ሁሉ ከኤ​ር​ም​ያስ አፍ በመ​ጽ​ሐፉ ክር​ታስ ጻፈ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 36:4
22 交叉引用  

አሁንም ሂድ፥ ለሚመጣውም ዘመን ለዘላለም እንዲሆን በሰሌዳ ላይ በመጽሐፍም ውስጥ ጻፍላቸው።


እግዚአብሔርም፦ ታላቅ ሰሌዳ ወስደህ፦ ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛ ቸኰለ ብለህ በሰው ፊደል ጻፍበት።


በእርስዋም ላይ የተናገርሁትን ቃሌን ሁሉ፥ ማለት ኤርምያስ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ትንቢት የተናገረውን በዚህች መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ፥ በዚያች ምድር አመጣለሁ።


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የነገርሁህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፍ።


የአጐቴም ልጅ አናምኤል፥ የውሉንም ወረቀት የፈረሙ ምስክሮች፥ በግዞትም ቤት አደባባይ የተቀመጡ አይሁድ ሁሉ እያዩ የውሉን ወረቀት ለመሕሤያ ልጅ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት።


አለቆቹም ሁሉ፦ በሕዝቡ ጆሮ ያነበብኸውን ክርታስ በእጅህ ይዘህ ና የሚል መልእክት በኵሲ ልጅ በሰሌምያ ልጅ በናታንያ ልጅ በይሁዲ እጅ ወደ ባሮክ ላኩ። የኔርያም ልጅ ባሮክ ክርታሱን በእጁ ይዞ ወደ እነርሱ መጣ።


ንጉሡም ክርታሱን ያመጣ ዘንድ ይሁዲን ላከ፥ እርሱም ከጸሐፊው ከኤሊሳማ ጓዳ ወሰደው፥ ይሁዲም በንጉሡና በንጉሡ አጠገብ በቆሙት አለቆች ሁሉ ጆሮ አነበበው።


ይሁዲም ሦስት ወይም አራት ዓምድ ያህል ባነበበ ቍጥር፥ ንጉሡ በካራ ቀደደው፥ ክርታሱም በምድጃ ውስጥ ባለው እሳት ፈጽሞ እስኪቃጠል ድረስ በምድጃ ውስጥ ወዳለው እሳት ጣለው።


ንጉሡም ጸሐፊውን ባሮክንና ነቢዩን ኤርምያስን ይይዙ ዘንድ የንጉሡን ልጅ ይረሕምኤልንና የዓዝርኤልን ልጅ ሠራያን የዓብድኤልንም ልጅ ሰሌምያን አዘዘ፥ እግዚአብሔር ግን ሰወራቸው።


ንጉሡም ክርስታሱንና ባሮክ ከኤርምያስ አፍ የጻፈውን ቃል ካቃጠለ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦


ዳግመኛም ሌላ ክርታስ ውሰድ፥ የይሁዳም ንጉሥ ኢዮአቄም ባቃጠለው ክርታስ ላይ የነበረውን የቀድሞውን ቃል ሁሉ ጻፍበት።


ኤርምያስም ሌላ ክርታስ ወሰደ ለኔርያም ልጅ ለጸሐፊው ለባሮክ ሰጠው፥ እርሱም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ያቃጠለውን የመጽሐፉን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ ጻፈበት፥ ደግሞም እንደ ቀድሞው ያለ ቃል ብዙ ቃል ተጨመረበት።


አንተ ግን ሂድ፥ ከአፌም የጻፍኸውን የእግዚአብሔርን ቃል በጾም ቀን በእግዚአብሔር ቤት በሕዝቡ ጆር በክርታሱ አንብብ፥ ደግሞም ከከተሞቻቸው በሚወጡ በይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አንብበው።


ነገር ግን ከለዳውያን እንዲገድሉን ወደ ባቢሎንም እንዲማርኩን በእጃቸው አሳልፈህ ትሰጠን ዘንድ የኔርያ ልጅ ባሮክ በላያችን ላይ አነሣሥቶሃል አሉት።


የመሕሤያ ልጅ የኔርያ ልጅ ሠራያ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ከእርሱ ጋር ወደ ባቢሎን በሄደ ጊዜ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘው ቃል ይህ ነው። ሠራያም የቤት አዛዥ ነበረ።


በባቢሎንም ላይ የሚመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስለ ባቢሎን የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ በመጽሐፍ ላይ ጻፈው።


ባየሁም ጊዜ፥ እነሆ፥ እጅ ወደ እኔ ተዘርግታ ነበር፥ እነሆም፥ የመጽሐፍ ጥቅልል ነበረባት።


በባቢሎን ንጉሥ በብልጣሶር በመጀመሪያው ዓመት ዳንኤል በአልጋው ላይ ሕልምንና የራሱን ራእይ አየ፥ ከዚያም በኋላ ሕልሙን ጻፈ፥ ዋነኛውንም ነገር ተናገረ።


ተመልሼም ዓይኖቼን አነሣሁ፥ እነሆም፥ አንድ በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አየሁ።


ይህን መልእክት የጻፍሁ እኔ ጤርጥዮስ በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ።


跟着我们:

广告


广告