Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 32:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የይሁዳም ንጉሥ ሴዴቅያስ በእውነት በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰጣል፥ አፍ ለአፍም ይናገረዋል፥ ዓይኑም ዓይኑን ያያል እንጂ ከከለዳውያን እጅ አያመልጥም፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስም ለባቢሎን ንጉሥ ዐልፎ ይሰጣል፤ ፊት ለፊትም ያነጋግረዋል፤ በዐይኖቹም ያየዋል እንጂ ከባቢሎናውያን እጅ አያመልጥም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የይሁዳም ንጉሥ ሴዴቅያስ በእውነት በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰጣል፥ ፊት ለፊትም ያነጋግረዋል፥ ዓይኑም ዓይኑን ያያል እንጂ ከከለዳውያን እጅ አያመልጥም፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ንጉሥ ሴዴቅያስም ማምለጫ የለውም፤ እርሱ ለባቢሎን ንጉሥ ተላልፎ ይሰጣል፤ ንጉሡን ፊት ለፊት ያየዋል፤ በግሉም ያነጋግረዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ በእ​ው​ነት በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰ​ጣል፤ አፍ ለአ​ፍም ይና​ገ​ረ​ዋል፤ ዐይን ለዐ​ይ​ንም ይተ​ያ​ያሉ እንጂ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅ አያ​መ​ል​ጥም፤

参见章节 复制




ኤርምያስ 32:4
13 交叉引用  

ከዚህ በኋላ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ከቸነፈርና ከሰይፍ ከራብም በዚህች ከተማ የቀሩትንም ባሪዎቹንና ሕዝቡን በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውንም በሚሹት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፥ እርሱም በሰይፍ ስለት ይመታቸዋል፥ አያዝንላቸውም፥ አይራራላቸውም፥ አይምራቸውም።


ሽሽትም ከእረኞች ማምለጥም ከመንጋ አውራዎች ይጠፋል።


የይሁዳንም ንጉሥ ሴዴቅያስንና አለቆቹን ለጠላቶቻቸው እጅ ነፍሳቸውንም ለሚሹአት እጅ ከእናንተም ለተመለሱት ለባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ።


አንተም በእርግጥ ትያዛለህ በእጅም አልፈህ ትሰጣለህ እንጂ ከእጁ አታመልጥም፥ ዓይንህም የባቢሎንን ንጉሥ ዓይን ታያለች፥ እርሱም ከአንተ ጋር አፍ ለአፍ ይናገራል፥ ወደ ባቢሎንም ትገባለህ።


ንጉሡ ሴዴቅያስ ልኮ አስመጣው፥ ንጉሡም በቤቱ፦ በውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ቃል አለን? ብሎ በቈይታ ጠየቀው። ኤርምያስም፦ አዎን አለ። ደግሞም፦ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፈህ ትሰጣለህ አለ።


ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ባትወጣ ግን፥ ይህች ከተማ በከለዳውያን እጅ ትሰጣለች፥ በእሳትም ያቃጥሉአታል አንተም ከእጃቸው አታመልጥም አለው።


ሚስቶችህንና ልጆችህንም ሁሉ ወደ ከለዳውያን ያወጣሉ፥ አንተም በባቢሎን ንጉሥ እጅ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፥ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።


跟着我们:

广告


广告