Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 32:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እስከ ዛሬም ድረስ ምልክትንና ድንቅን ነገር በግብጽ ምድር ደግሞም በእስራኤልና በሌሎች ሰዎች መካከል አድርገሃል፥ እንደ ዛሬም ለአንተ ስም አድርገሃል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በግብጽ ታምራትንና ድንቆችን አደረግህ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በእስራኤልና በሰው ልጆች ሁሉ መካከል እንደዚያው እያደረግህ ዛሬም ስምህ ገናና ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ምልክትንና ድንቅን ነገር በግብጽ ምድር፥ እስከ ዛሬም ድረስ በእስራኤልና በሌሎች ሰዎች መካከል አድርገሃል፥ በዚህም እስከ ዛሬዋ ቀን ስምህን አጽንተሃል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በቀድሞ ጊዜ በግብጽ ምድር ተአምራትንና አስደናቂ ነገሮችን አደረግህ፤ እስከ አሁንም ድረስ እነዚያን ድንቅ ሥራዎች በእስራኤል ሕዝብና በሌሎች ሰዎች መካከል ከማድረግ አልተቈጠብክም፤ ከዚህም የተነሣ በሁሉ ስፍራ ስምህ ገኗል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እስከ ዛሬም ድረስ ምል​ክ​ት​ንና ድን​ቅን ነገር በግ​ብፅ ምድር፥ ደግ​ሞም በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በሌ​ሎች ሰዎች መካ​ከል አድ​ር​ገ​ሃል፤ እንደ ዛሬም ለአ​ንተ ስም አድ​ር​ገ​ሃል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 32:20
21 交叉引用  

ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ይቤዥ ዘንድ ለእርሱ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ፥ በአሕዛብና በአምላኮቻቸውም ፊት ከግብጽ በተቤዠው ሕዝብ ፊት ተአምራትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ሄደለት እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?


አንተ እግዚአብሔር ከግብጽ ካወጣኸው ከሕዝብህ ፊት አሕዛብን በማሳደድ በታላቅና በሚያስፈራ ነገር ለአንተ ስም ታደርግ ዘንድ፥ ለአንተም ሕዝብ ትቤዥ ዘንድ እንደ ሄድህለት እንደ አንተ ሕዝብ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ሌላ ሕዝብ አለን?


እንደ ታበዩባቸውም አውቀህ ነበርና በፈርዖንና በባሪያዎቹ ሁሉ በምድሩም ሕዝብ ሁሉ ላይ ምልክትና ተአምራት አሳየህ፥ ዛሬም እንደ ሆነው ስምህን አስጠራህ።


ከፊታቸውም ባሕሩን ከፈልህ፥ በባሕሩም መካከል በደረቅ አለፉ፥ ጠላቶቻቸውን ግን ድንጋይ ለጥልቅ ውኃ እንዲጣል በቀላይ ውስጥ ጣልሃቸው።


ይህንንም ያደረግሁት ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ ግብፃውያንን እንደቀጣሁና ምን ዓይነት ተአምራትን እንዳደረግሁ መንገር ትችሉ ዘንድ ነው፤ በዚህም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


እኔም እጄን እዘረጋለሁ፤ በማደርግባቸውም ተአምራቴ ሁሉ ግብፅን እመታለሁ፤ ከዚያም በኋላ ይለቅቃችኋል።


እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ፤ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ።


ነገር ግን ኃይሌን እገልጥብህ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ስለዚህ አስነሥቼሃለሁ።


የከበረውንም ክንድ በሙሴ ቀኝ ያስሄደ፥ ለራሱም የዘላለምን ስም ያደርግ ዘንድ ውኃውን በፊታቸው የከፈለ፥


ወደ ሸለቆ እንደሚወርዱ ከብቶች፥ እንዲሁ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ዕረፍት አመጣቸው፥ እንዲሁም ለራስህ የከበረ ስም ታደርግ ዘንድ ሕዝብን መራህ።


መታጠቂያ በሰው ወገብ ላይ እንደምትጣበቅ፥ እንዲሁ ሕዝብና ስም ምስጋናና ክብር ይሆኑልኝ ዘንድ የእስራኤልን ቤት ሁሉ የይሁዳንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣብቄአለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ነገር ግን አልሰሙም።


ይህም ዳንኤል በዳርዮስ መንግሥትና በፋርሳዊው በቂሮስ መንግሥት ኑሮው ተቃናለት።


አሁንም ሕዝብህን ከግብጽ ምድር በበረታች እጅ ያወጣህ፥ እንደ ዛሬም ቀን ዝና ለአንተ ያገኘህ ጌታ አምላካችን ሆይ፥ ኃጢአትን ሠርተናል፥ ክፋትንም አድርገናል።


ይህ ሰው በግብፅ ምድርና በኤርትራ ባሕር በምድረ በዳም አርባ ዓመት ድንቅና ምልክት እያደረገ አወጣቸው።


በግብፅም መካከል በንጉሡ በፈርዖንና በአገሩ ሁሉ ላይ ያደረጋትን ተአምራቱንና ሥራውን፥


አምላካችሁ እግዚአብሔር በዓይናችሁ ፊት በግብፅ ለእናንተ እንደ ሠራው ሁሉ፥ በፈተናና በተአምራት፥ በድንቅና በሰልፍ፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ በታላቅም ማስፈራት እግዚአብሔር ከሌላ ሕዝብ መካከል ገብቶ ለእርሱ ሕዝብን ይወስድ ዘንድ ሞክሮ ነበርን?


እግዚአብሔርም በግብፅና በፈርዖን በቤቱም ሁሉ ላይ እኛ እያየን ታላቅና ክፋ ምልክት ተአምራትም አደረገ።


አምላክህ እግዚአብሔር፥ ዓይንህ እያየች፥ ታላቅን መቅሠፍት ምልክትንም ተአምራትንም የጸናችውን እጅ የተዘረጋውንም ክንድ አድርጎ እንዳወጣህ፥ አስብ፤ እንዲሁ አምላክህ እግዚአብሔር አንተ በምትፈራቸው በአሕዛብ ሁሉ ላይ ያደርጋል።


跟着我们:

广告


广告