Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 32:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህች ምድር ቤትንና እርሻን የወይን ቦታንም እንደ ገና ይገዛሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ሰዎች በዚህ ምድር ቤት፣ የዕርሻ ቦታና የወይን አትክልት ስፍራ እንደ ገና ይገዛሉ።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህች ምድር ቤትንና እርሻን የወይን ቦታንም እንደገና ይገዛሉ።’”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እንደገና በዚህች ምድር ቤቶችን፥ የእርሻ መሬቶችን፥ የወይን ተክል ቦታዎችን መግዛት የሚቻልበት ጊዜ ይመጣል ብሎአል።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤት​ንና እር​ሻን የወ​ይን ቦታ​ንም እንደ ገና ይገ​ዛሉ።”

参见章节 复制




ኤርምያስ 32:15
13 交叉引用  

የባሪያዬን ቃል አጸናለሁ፥ የመልእክተኞቼንም ምክር እፈጽማለሁ፥ ኢየሩሳሌምን፦ የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፥ የይሁዳንም ከተሞች፦ ትታነጻላችሁ ፍራሾቻችሁንም አቆማለሁ እላለሁ፥


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፥ ለማደሪያውም እራራለሁ፥ ከተማይቱም በጉብታዋ ላይ ትሠራለች፥ አዳራሹም እንደ ዱሮው የሰው መኖሪያ ይሆናል።


ይመጣሉ በጽዮንም ተራራ እልል ይላሉ፥ ወደ እግዚአብሔርም በጎነት፥ ወደ እህልና ወደ ወይን ጠጅ ወደ ዘይትም፥ ወደ በጎችና ወደ ላሞች ይሰበሰባሉ፥ ነፍሳቸውም እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አያዝኑም።


በይሁዳ ከተሞችና በአገሩ ሁሉ ከገበሬዎችና መንጋን ይዘው ከሚዞሩ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ይገኛሉ።


እንደ ገናም በሰማርያ ተራሮች ላይ የወይን ቦታዎችን ትተክሊአለሽ፥ አትክልተኞች ይተክላሉ በፍሬውም ደስ ይላቸዋል።


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብዙ ቀን ይጠበቁ ዘንድ የታተመውንና የተከፈተውን ይህን የውል ወረከት ወስደህ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኑራቸው።


አንተም፥ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፦ እርሻውን በብር ግዛ ምስክሮችንም ጥራ አልኸኝ፥ ከተማይቱ ግን ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች።


እነሆ፥ በቍጣዬና በመዓቴ በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት አገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፥ ተዘልለውም እንዲኖሩ አደርጋለሁ፥


ተዘልለውም ይቀመጡባታል፥ ቤቶችንም ይሠራሉ ወይኑንም ይተክላሉ በዙሪያቸውም ባሉ በሚንቋቸው ሁሉ ላይ ፍርድን ባደረግሁ ጊዜ ተዘልለው ይቀመጣሉ፥ እኔም እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።


በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ሆኖ ባልንጀራውን ይጠራል።


跟着我们:

广告


广告