Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 32:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በውሉም ወረቀት ላይ ፈረምሁ አተምሁትም፥ ምስክሮችንም ጠርቼ ብሩን በሚዛን መዘንሁለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በውሉም ሰነድ ላይ ፈረምሁ፤ አሸግሁትም። ብሩንም በምስክሮች ፊት በሚዛን መዘንሁለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በውሉም ሰነድ ላይ ፈረምሁ አተምሁትም፥ ምስክሮችንም ጠርቼ ብሩን በሚዛን መዘንሁለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የግዢውንም ውል ምስክሮች ባሉበት ፈርሜ አሸግሁት፤ ገንዘቡንም በሚዛን መዝኜ ሰጠሁት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የው​ሉ​ንም ወረ​ቀት ጻፍሁ፤ አተ​ም​ሁ​ትም፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም ጠርቼ ብሩን በሚ​ዛን መዘ​ን​ሁ​ለት።

参见章节 复制




ኤርምያስ 32:10
23 交叉引用  

አብርሃምም የኤፍሮንን ነገር ሰማ አብርሃምም በኬጢ ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል መዝኖ ለኤፍሮን ሰጠው ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ።


እርሻውና በእርሱ ያለው ዋሻው በኬጢ ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና።


መተላልፌ በከረጢት ውስጥ ታትሞአል፥ ኃጢአቴንም ለብጠህበታል።


እንደ ማኅተም በልብህ፥ እንደ ማኅተም በክንድህ አኑረኝ፥ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና፥ ቅንዓትም እንደ ሲኦል የጨከነች ናትና። ፍንጣሪዋ እንደ እሳት ፍንጣሪ፥ እንደ እግዚአብሔር ነበልባል ነው።


አሁንም ሂድ፥ ለሚመጣውም ዘመን ለዘላለም እንዲሆን በሰሌዳ ላይ በመጽሐፍም ውስጥ ጻፍላቸው።


ይህ፦ እኔ የእግዚአብሔር ነኝ ይላል፥ ያም በያዕቆብ ስም ይጠራል፥ ይህም፦ እኔ የእግዚአብሔር ነኝ ብሎ በእጁ ይጽፋል በእስራኤልም የቍልምጫ ስም ይጠራል።


የአጐቴም ልጅ አናምኤል፥ የውሉንም ወረቀት የፈረሙ ምስክሮች፥ በግዞትም ቤት አደባባይ የተቀመጡ አይሁድ ሁሉ እያዩ የውሉን ወረቀት ለመሕሤያ ልጅ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት።


አንተም፥ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፦ እርሻውን በብር ግዛ ምስክሮችንም ጥራ አልኸኝ፥ ከተማይቱ ግን ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች።


ምርኮኞቻቸውንም እመልሳለሁና በብንያም አገር በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች በደጋውም ባሉ ከተሞች በቈላውም ባሉ ከተሞች በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ ሰዎች እርሻውን በብር ይገዛሉ በውሉም ወረቀት ፈርመው ያትማሉ ምስክሮችንም ይጠራሉ።


የተነገረውም የማታውና የጥዋቱ ራእይ እውነተኛ ነው፥ ነገር ግን ከብዙ ዘመን በኋላ ስለሚሆን ራእዩን ዝጋ።


እነርሱም ሄደው ከጠባቆች ጋር ድንጋዩን አትመው መቃብሩን አስጠበቁ።


ምስክሩን የተቀበለ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ።


ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።


ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው።


እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤


ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።


ይህ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ የለምን? 2 በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን?


ሰዎቹም ሄደው ምድሩን ዞሩ፥ እንደ ከተሞችም በሰባት ክፍል ከፈሉት፥ በመጽሐፍም ጻፉት፥ ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ሴሎ ተመለሱ።


የሕያው አምላክ ማኅተም ያለውም ሌላ መልአክ ከፀሐይ መውጫ ሲወጣ አየሁ፥ ምድርንና ባሕርንም ሊጐዱ ለተሰጣቸው ለአራቱ መላእክት በታላቅ ድምፅ እየጮኸ፦


የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተባለላቸው።


ቦዓዝም ወደ ከተማይቱ በር አደባባይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ። እነሆም፥ ቦዔዝ ስለ እርሱ ይናገር የነበረው የቅርብ ዘመድ ሲያልፍ ቦዔዝ “አንተ ቀርበህ በዚህ ተቀመጥ፤” አለው። እርሱም ቀረብ ብሎ ተቀመጠ።


跟着我们:

广告


广告