Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 3:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የእስራኤል ልጆች መንገዳቸውን አጣምመዋልና፥ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተዋልና በወናዎች ኮረብቶች ላይ የልመናቸውና ልቅሶአቸው ድምፅ ተሰማ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እግዚአብሔር አምላካቸውን በመርሳት፣ መንገዳቸውን አጣመዋልና፣ የእስራኤል ሕዝብ ጩኸት፣ አሳዛኝ ልቅሶ ባድማ ከሆኑት ኰረብቶች ተሰማ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የእስራኤል ልጆች መንገዳቸውን አጣምመዋልና፥ አምላካቸውንም ጌታን ረስተዋልና በተራቈቱ ኮረብቶች ላይ የልመናቸው የለቅሶ ድምፅ ተሰማ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ልምላሜ በሌለባቸው ኰረብቶች ራስ ላይ ድምፅ ይሰማል፤ ይህም ድምፅ፥ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር አምላካቸውን በመርሳት ኃጢአት ሲሠሩ ኖረው፥ አሁን በመጸጸት የሚያሰሙት የለቅሶና የልመና ድምፅ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ዐም​ጸ​ዋ​ልና፥ ቅዱስ አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም ረስ​ተ​ዋ​ልና ከብዙ ሰዎች ድምፅ ተሰማ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ልቅ​ሶና ጩኸ​ትም ተሰማ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 3:21
24 交叉引用  

እርሱም በሰው ፊት እየዘመረ፦ እኔ በድያለሁ፥ ቅኑንም አጣምሜአለሁ፥ የሚገባኝንም ብድራት አልተቀበልሁም፥


ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም ለልቅሶ ወጥተዋል፥ ሞዓብ በናባውና በሜድባ ላይ ታለቅሳለች፥ ራሳቸው ሁሉ ተነጭቶአል፥ ጢማቸውም ሁሉ ተላጭቶአል።


የደኅንነትህን አምላክ ረስተሃል፥ የረድኤትህንም ጌታ አላሰብህም፥ ስለዚህ ያማረውን ተክል ተክለሃል፥ እንግዳንም ዘር ዘርተሃል።


ሐሰትን የተናገርሺው እኔንም ያላሰብሽው በልብሽም ነገሩን ያላኖርሺው ማንን ሰግተሽ ነው? ማንንስ ፈርተሽ ነው? እኔ ብዙ ጊዜ ዝም አልሁ፥ አንቺም አልፈራሽም።


በወናዎች ኮረብቶች ሁሉ ላይ በዝባዦች መጥተዋል፥ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበላልና፥ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም።


ረስተሽኛልና፥ በሐሰትም ታምነሻልና ዕጣሽ የለካሁልሽም እድል ፈንታ ይህ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር።


ሕዝቤ ግን ረስተውኛል ለከንቱ ነገርም ዐጥነዋል፥ ከመንገዱም ተሰናክለዋል ከቀድሞውም ጐዳና ርቀው ወዳልተሠራው ወደ ጠማማው መንገድ ፈቀቅ ብለዋል።


በውኑ ቆንጆ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን የማይቈጠር ወራት ረስቶኛል።


ዓይንሽን አንሥተሽ ወደ ወናዎች ኮረብቶች ተመልከቺ፥ ያልተጋደምሽበት ስፍራ ወዴት አለ? ዓረባዊ በምድረ በዳ እንደሚቀመጥ አንቺ በመንገድ ላይ ተቀምጠሽ ትጠብቂያቸው ነበር፥ በግልሙትናሽና በኃጢአትሽ ምድሪቱን አረከስሽ።


በልቅሶ ወጡ እኔም በማጽናናት አመጣቸዋለሁ፥ በወንዝ ዳር በቅን መንገድ አስኬዳቸዋለሁ፥ በእርሱም አይሰናከሉም፥ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ ኤፍሬምም በኵሬ ነውና።


እግዚአብሔር የቍጣውን ትውልድ ጥሎአልና፥ ትቶታልምና ጠጕርሽን ቍረጪ፥ ጣዪውም፥ በወናዎች ኮረብቶችም ላይ አሙሺ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዘንግተሽኛልና፥ ወደ ኋላሽም ጥለሽኛልና አንቺ ደግሞ ሴሰኝነትሽንና ግልሙትናሽን ተሸከሚ።


ከእነርሱም የሚሸሹ ይድናሉ በተራራም ላይ ይሆናሉ፥ እኔም በኃጢአታቸው ሁሉን እገድላለሁ።


ከተሰማሩ በኋላ ጠገቡ፥ በጠገቡም ጊዜ ልባቸው ታበየ፥ ስለዚህ ረሱኝ።


እስራኤል ፈጣሪውን ረስቶአል፥ መስገጃዎችንም ሠርቶአል፥ ይሁዳም የተመሸጉትን ከተሞች አብዝቶአል፥ እኔ ግን በከተሞች ላይ እሳት እሰድዳለሁ፥ አዳራሾችንም ትበላለች።


ፍርድን የምትጠሉ ቅን ነገርንም ሁሉ የምታጣምሙ እናንተ የያዕቆብ ቤት አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዦች ሆይ፥ እባካችሁ ይህን ስሙ።


የእግዚአብሔርም መልአክ፦ አህያህን ሦስት ጊዜ ለምን መታህ? እነሆ፥ መንገድህ በፊቴ ጠማማ ነውና እቍቍምህ ዘንድ ወጥቼአለሁ፤


እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ጸጸት የሌለበትን፥ ወደ መዳንም የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና፤ የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል።


跟着我们:

广告


广告