Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 27:18 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እነርሱ ግን ነቢያት ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔርም ቃል በእነርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት በኢየሩሳሌምም የቀረችው ዕቃ ወደ ባቢሎን እንዳትሄድ ወደ ሠራዊት ጌታ ወደ እግዚአብሔር ይማለሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እውነተኞች ነቢያት ከሆኑና በርግጥ የእግዚአብሔር ቃል ካላቸው፣ በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት በኢየሩሳሌምም የቀሩት ዕቃዎች ወደ ባቢሎን እንዳይወሰዱ ወደ ሰራዊት ጌታ ወደ እግዚአብሔር እስኪ ይማልዱ!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እነርሱ ግን ነቢያት ቢሆኑ፥ የጌታም ቃል በእነርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ በጌታ ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት በኢየሩሳሌምም የቀሩት ዕቃዎች ወደ ባቢሎን እንዳይሄዱ እስቲ ወደ ሠራዊት ጌታ ይማለሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እነርሱ ነቢያት ከሆኑና እኔም የሰጠኋቸው የትንቢት ቃል በእነርሱ ዘንድ ካለ፥ ገና ያልተወሰደው በቤተ መቅደስ፥ በይሁዳ ቤተ መንግሥትና በኢየሩሳሌም የቀረው ዕቃ ሁሉ ወደ ባቢሎን እንዳይወሰድ አደርግ ዘንድ እየተማጠኑ ሁሉን ቻይ የሆንኩትን እኔን እግዚአብሔርን ይጠይቁኝ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እነ​ርሱ ግን ነቢ​ያት ቢሆኑ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የቀ​ሩት ዕቃ​ዎች ወደ ባቢ​ሎን እን​ዳ​ይ​ሄዱ ወደ ሠራ​ዊት ጌታ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይማ​ለሉ።”

参见章节 复制




ኤርምያስ 27:18
18 交叉引用  

አብርሃምም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን ሚስቱንም ባሪያዎቹንምም ፈውሳቸው


እናንተም የአምላካችሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁ፤ ሰምቶም በእሳት የሚመልስ አምላክ፥ እርሱ አምላክ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ “ይህ ነገር መልካም ነው፤” ብለው መለሱ።


ወይፈኑንም ወስደው አዘጋጁ፤ ከጥዋትም እስከ ቀትር ድረስ “በኣል ሆይ! ስማን፤” እያሉ የበኣልን ስም ጠሩ። ድምፅም አልነበረም፤ የሚመልስም አልነበረም፤ በሠሩትም መሠዊያ ዙሪያ እያነከሱ ያሸበሽቡ ነበር።


ንጉሡም ሕዝቅያስና የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለዚህ ጸለዩ፤ ወደ ሰማይም ጮኹ።


እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ፦ ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አይዘነብልም፥ ከፊቴ ጣላቸው፥ ይውጡ።


ለነፍሴ ጕድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም እናገር ዘንድ ቍጣህንም ከእነርሱ እመልስ ዘንድ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስብ።


ነብዩንም ኤርምያስን፦ ዓይኖችህ እንዳዩን ከብዙ ጥቂት ቀርተናልና ልመናችን፥ እባክህ፥ በፊትህ ትድረስ፥ አምላክህም እግዚአብሔር የምንሄድበትን መንገድና የምናደርገውን ነገር ያሳየን ዘንድ ስለ እኛ፥ ስለዚህ ቅሬታ ሁሉ፥ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ አሉት።


እንግዲህም አልሰማህምና ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ ስለ እነርሱም ልመናና ጸሎት አታድርግ፥ አትማልድላቸው።


እነዚህ ሦስት ሰዎች፥ ኖኅና ዳንኤል ኢዮብም፥ ቢኖሩባት በጽድቃቸው የገዛ ነፍሳቸውን ብቻ ያድናሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ቅጥርን የሚጠግንን፥ ምድሪቱንም እንዳላጠፋት በፈረሰበት በኩል በፊቴ የሚቆምላትን ሰው በመካከላቸው ፈለግሁ፥ ነገር ግን አላገኘሁም።


አሁንም ጸጋን ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔርን ለምኑ፥ ይህ ከእጃችሁ የተሰጠ ሲሆን ከቶ ፊታችሁን ይቀበላልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ሕዝቡም ሁሉ ሳሙኤልን፦ ንጉሥ በመለመናችን በኃጢአታችን ሁሉ ላይ ይህን ክፋት ጨምረናልና እንዳንሞት ስለ ባሪያዎችህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ አሉት።


ደግሞ መልካሙንና ቅኑን መንገድ አስተምራችኋለሁ እንጂ ስለ እናንተ መጸለይን በመተው እግዚአብሔርን እበድል ዘንድ ይህ ከእኔ ይራቅ።


የእስራኤልም ልጆች ሳሙኤልን፦ ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድነን ዘንድ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ትጸልይልን ዘንድ አትታክት አሉት።


跟着我们:

广告


广告