Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 27:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ለካህናትም ለዚህም ሕዝብ እንዲህ ብዬ ተናገርሁ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሐሰተኛውን ትንቢት ይናገሩላችኋልና፦ የእግዚአብሔር ቤት ዕቃ በቅርብ ጊዜ ከባቢሎን ይመለሳል የሚሉአችሁን የነቢያቶቻችሁን ቃል አትስሙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እኔም ለካህናቱና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ እንዲህ አልሁ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የእግዚአብሔር ቤት ዕቃ ከባቢሎን ቶሎ ይመለሳል’ የሚሏችሁን ነቢያት አትስሟቸው፤ የሚነግሯችሁ የሐሰት ትንቢት ነውና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ለካህናትም ለዚህም ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብዬ ተናገርሁ፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሐሰተኛን ትንቢት ለእናንተ በመናገር፦ ‘እነሆ፥ የጌታ ቤት ዕቃዎች በቅርብ ጊዜ ከባቢሎን ይመለሳሉ’ ብለው ትንቢት የሚነግሩአችሁን የነብዮቻችሁን ቃላት አትስሙ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህ በኋላ ለካህናቱና ለሕዝቡ እንዳስታውቅ እግዚአብሔር የሚከተለውን ነገረኝ፤ እንዲህ ብዬም ነገርኳቸው፦ “ ‘የቤተ መቅደሱ ዕቃ ሁሉ ከባቢሎን ተመልሶ በፍጥነት ይመጣል’ እያሉ የሚነግሩአችሁን ነቢያት ሁሉ አትስሙአቸው፤ እነርሱ የሚናገሩት የሐሰት ትንቢት ነው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ለካ​ህ​ና​ትም ለዚ​ህም ሕዝብ እን​ዲህ ብዬ ተና​ገ​ርሁ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሐሰ​ተ​ኛ​ውን ትን​ቢት ይና​ገ​ሩ​ላ​ች​ኋ​ልና፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃ በቅ​ርብ ጊዜ ከባ​ቢ​ሎን ይመ​ለ​ሳል የሚ​ሉ​አ​ች​ሁን የነ​ቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ቃል አት​ስሙ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 27:16
7 交叉引用  

የእግዚአብሔርንም ቤት ቤተ መዛግብት ሁሉ የንጉሡንም ቤተ መዛግብት ከዚያ አወጣ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሠራውን የወርቁን ዕቃ ሁሉ ሰባበረ።


ሽማግሌውና ከበርቴው እርሱ ራስ ነው፥ በሐሰትም የሚያስተምር ነቢይ እርሱ ጅራት ነው።


ከምድራቸሁ እንዲያርቁአችሁ፥ እኔም እንዳሳድዳችሁ እናንተም እንድትጠፉ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና።


ሐሰተኛን ትንቢት ይናገሩላችኋልና፦ ለባቢሎን ንጉሥ አትገዙም የሚሉአችሁን የነቢያትን ቃል አትስሙ።


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከዚህች ስፍራ ወደ ባቢሎን የወሰዳትን የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ሁሉ በሁለት ዓመት ውስጥ ወደዚህች ስፍራ እመልሳታለሁ፥


ጌታም የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምን ከእግዚአብሔርም ቤት ዕቃ ከፍሎ በእጁ አሳልፎ ሰጠው፥ እርሱም ወደ ሰናዖር ምድር ወደ አምላኩ ቤት ወሰደው፥ ዕቃውንም ወደ አምላኩ ግምጃ ቤት አገባው።


跟着我们:

广告


广告