Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 27:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እኔ አልላክኋቸውምና፥ ነገር ግን እኔ እንዳሳድዳችሁ፥ እናንተና ትንቢት የሚናገሩላችሁ ነቢያትም እንድትጠፉ በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ‘እኔ አልላክኋቸውም’ ይላል እግዚአብሔር ‘የሐሰት ትንቢት በስሜ ይናገራሉ፤ ስለዚህ እናንተንና ትንቢት የሚናገሩላችሁን ነቢያት አሳድዳለሁ፤ እናንተም ትጠፋላችሁ።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እኔ አልላክኋቸውምና፤ ነገር ግን እኔ እንዳሳድዳችሁ፥ እናንተና ትንቢት የሚነግሩአችሁ ነቢያትም እንድትጠፉ፥ በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገራሉ፥ ይላል ጌታ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እርሱ ያልላካቸው መሆኑንና እነርሱ በስሙ የሚነግሩአችሁ ሁሉ ውሸት መሆኑን እግዚአብሔር ራሱ ነግሮአችኋል። ስለዚህ እርሱ ያሳድዳችኋል፤ እናንተና ይህን ውሸት የሚነግሩአችሁ ነቢያት ሁሉ ትጠፋላችሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እኔ አል​ላ​ክ​ኋ​ቸ​ው​ምና፤ ነገር ግን እኔ እን​ዳ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ፥ እና​ን​ተና ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ችሁ ነቢ​ያ​ትም እን​ድ​ት​ጠፉ በስሜ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ራሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

参见章节 复制




ኤርምያስ 27:15
27 交叉引用  

እርሱም ሲናገር ንጉሡ “በውኑ አንተ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሾመነሃልን? ተው፤ ቅጣትን ስለ ምን ትሻለህ?” አለው። ነቢዩም “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና እግዚአብሔር ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ተወ።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ነቢያቱ ውሸት በስሜ ትንቢት ይናገራሉ፥ አላክኋቸውም፥ አላዘዝኋቸውም፥ አልተናገርኋቸውም፥ የውሸቱን ራእይ ምዋርትንም ከንቱንም ነገር የልባቸውንም ሽንገላ ይሰብኩላችኋል።


አንተም፥ ጳስኮር ሆይ፥ በቤትህም የሚኖሩት ሁሉ ተማርካችሁ ትሄዳላችሁ፥ አንተም በሐሰትም ትንቢት የተናገርህላቸው ወዳጆችህ ሁሉ ወደ ባቢሎን ትገባላችሁ፥ በዚያም ትሞታላችሁ፥ በዚያም ትቀበራላችሁ።


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከኢየሩሳሌም ነቢያት ዘንድ ርኵሰት በምድር ሁሉ ላይ ወጥቶአልና እሬትን አበላቸዋለሁ የሐሞትንም ውኃ አጠጣቸዋለሁ።


እኔ ሳልልካቸው እነዚህ ነቢያት ሮጡ፥ እኔም ሳልነግራቸው ትንቢትን ተናገሩ።


አለምሁ አለምሁ እያሉ በስሜ ሐሰትን የሚናገሩትን የነቢያትን ነገር ሰምቻለሁ።


ከምድራቸሁ እንዲያርቁአችሁ፥ እኔም እንዳሳድዳችሁ እናንተም እንድትጠፉ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና።


የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመካከላችሁ ያሉት ነቢያቶቻችሁና ምዋርተኞቻችሁ አያታልሉአችሁ፥ እናንተም የምታልሙትን ሕልም አትስሙ።


በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና፥ እኔም አልላክኋቸውም።


እነሆ፥ በይሁዳ ንጉሥ ቤት የቀሩትን ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ያወጣሉ፥ እነዚያም ሴቶች፦ ባለምዋሎችህ አታልለውሃል አሸንፈውህማል፥ እግሮችህ ግን አሁን በጭቃ ውስጥ ከገቡ እነርሱ ከአንተ ወደ ኋላ ተመልሰዋል ይላሉ።


ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ አለ።


ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።


አውሬውም ተያዘ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።


跟着我们:

广告


广告