Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 27:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ለባቢሎን ንጉሥ ይገዛ ዘንድ እንቢ ስላለ ሕዝብ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ፥ አንተና ሕዝብህ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ለምን ትሞታላችሁ?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 አንተና ሕዝብህ፣ እግዚአብሔር ለባቢሎን ንጉሥ አልገዛም ያለውን ሕዝብ ባስጠነቀቀበት በሰይፍ፣ በራብና በመቅሠፍት ለምን ታልቃላችሁ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ለባቢሎን ንጉሥ ማገልገልን እንቢ ስለሚል ሕዝብ ጌታ እንደ ተናገረው፥ አንተና ሕዝብህ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ለምን ትሞታላችሁ?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለምንስ አንተና ሕዝብህ በጦርነት፥ በራብና በቸነፈር ታልቃላችሁ? ለባቢሎን ንጉሥ በማይገዛ በማናቸውም ሕዝብ ላይ ይደርስበታል ብሎ እግዚአብሔር የተናገረውም ይህንኑ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ይገዛ ዘንድ እንቢ ስላለ ሕዝብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ፥ አን​ተና ሕዝ​ብህ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ለምን ትሞ​ታ​ላ​ችሁ?

参见章节 复制




ኤርምያስ 27:13
11 交叉引用  

አንተም የሰጠሁህን ርስት ትለቅቃለህ ለዘላለምም በማታውቃትም ምድር ለጠላቶቻችሁ ባሪያ አደርግሃለሁ፥ ለዘላለም የሚነድደውን እሳት በቍጣዬ አንድዳችኋልና።


በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ ለማላገጫና ለእርግማን ይሆኑ ዘንድ በምድር መንግሥታት ሁሉ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።


ለባቢሎን ንጉሥም ለናቡከደነፆር የማይገዛውን፥ ከባቢሎንም ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የማያደርገውን ሕዝብና መንግሥት፥ ያን ሕዝብ በእጁ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ኤርምያስ እንዲህ ብሎአልና፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህች ከተማ የሚቀመጥ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ይሞታል፥ ወደ ከለዳውያን ግን የሚወጣ በሕይወት ይኖራል፥ ነፍሱም እንደ ምርኮ ትሆንለታለች፥ በሕይወትም ይኖራል።


ኤርምያስም እንዲህ አለው፦ አሳልፈው አይሰጡህም። እኔ የምነግርህን የእግዚአብሔርን ቃል እባክህ፥ ስማ፥ ይቀናሃል ነፍስህም በሕይወት ትኖራለች።


ሚስቶችህንና ልጆችህንም ሁሉ ወደ ከለዳውያን ያወጣሉ፥ አንተም በባቢሎን ንጉሥ እጅ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፥ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።


ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ይልቁንስ ሰውንና እንስሳን ከእርስዋ አጠፋ ዘንድ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ ፍርዶቼን፥ ሰይፍንና ራብን ክፉዎችንም አውሬዎች ቸነፈርንም፥ ስሰድድባት!


ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ ኃጢአትንም ቢሠራ ኃጢአተኛውም እንደሚያደርገው ርኵሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራት ጽድቅ ሁሉ አትታሰብለትም፥ ባደረገው ዓመፅና በሠራት ኃጢአት በዚያች ይሞታል።


የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ ጣሉ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስም ለእናንተ አድርጉ፥ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለ ምን ትሞታላችሁ?


እኔ ሕያው ነኝና ኃጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኃጢአተኛው ይሞት ዘንድ አልፈቅድም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ተመለሱ፥ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ? በላቸው።


跟着我们:

广告


广告