Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 26:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ደግሞም በእግዚአብሔር ስም ትንቢት የተናገረ አንድ ሰው ነበረ፥ እርሱም የቂርያትይዓሪም ሰው የሸማያ ልጅ ኦርዮ ይባል ነበር፥ በዚህችም ከተማ በዚህችም ምድር ላይ እንደ ኤርምያስ ቃል ሁሉ ትንቢት ተናገረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ደግሞም የቂርያትይዓይሪም ሰው፣ የሸማያ ልጅ ኦርዮ፣ በእግዚአብሔር ስም ትንቢት የተናገረ ሌላው ሰው ነበር፤ እርሱም እንደ ኤርምያስ በዚህች ከተማና በዚህ ምድር ላይ ትንቢት ተናግሮ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ደግሞም በጌታ ስም ትንቢት የተናገረ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም የቂርያት-ይዓሪም ሰው የሸማያ ልጅ ኦርዮ ይባል ነበር፥ በዚህችም ከተማ በዚህችም ምድር ላይ እንደ ኤርምያስ ቃላት ሁሉ ትንቢት ተናገረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በቂርያትይዓሪም የሚኖር የሸማያ ልጅ ኡሪያ የተባለ ሌላም ሰው ነበር፤ ይህ ሰው ልክ እንደ ኤርምያስ በዚህች ከተማና በዚህች ምድር ላይ ጥፋት እንደሚመጣ በእግዚአብሔር ስም ትንቢት ተናግሮ ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ደግ​ሞም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ትን​ቢት የተ​ና​ገረ አንድ ሰው ነበር፤ እር​ሱም የቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሰው የሸ​ማያ ልጅ ኡርያ ይባል ነበር፤ በዚ​ችም ከተማ፥ በዚ​ችም ምድር ላይ እንደ ኤር​ም​ያስ ቃል ሁሉ ትን​ቢት ተና​ገረ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 26:20
9 交叉引用  

አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን! ጌታዬ ይፈልግህ ዘንድ ያልላከበት ሕዝብ ወይም መንግሥት የለም፤ ሁሉም ‘በዚህ የለም፤’ ባሉ ጊዜ አንተን እንዳላገኙ መንግሥቱንና ሕዝቡን አምሎአቸው ነበር።


አባቶቹም እንዳደረጉ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ።


ልጆቻችሁን በከንቱ ቀሥፌአቸዋለሁ፥ ተግሣጽን አልተቀበሉም፥ ሰይፋችሁ እንደሚሰብር አንበሳ ነቢያቶቻችሁን በልቶአል።


አለቆቹም ባሮክን፦ አንተና ኤርምያስ ሂዱ፥ ተሸሸጉ፥ ወዴትም እንደ ሆናችሁ ማንም አይወቅ አሉት።


ቂርያትይዓሪም የምትባለው ቂርያትበኣል፥ ረባት፥ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።


ድንበሩም ወደ ምዕራብ ሄደ፥ በቤትሖሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ ደቡብ ዞረ፥ መውጫውም ቂርያትይዓሪም በምትባል በይሁዳ ልጆች ከተማ በቂርያትበኣል ነበረ፥ ይህ የምዕራቡ ዳርቻ ነበረ።


የእስራኤልም ልጆች ተጉዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው መጡ፥ የከተሞቻቸውም ስም ገባዖን፥ ከፊራ፥ ብኤሮት፥ ቂርያትይዓሪም ነበረ።


በቂርያትይዓሪምም ወደ ተቀመጡት ሰዎች መልክተኞች ልከው፦ ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት መልሰዋል፥ ወርዳችሁም ወደ እናንተ አውጡት አሉ።


ታቦቱም በቂርያትይዓሪም ከተቀመጠበት ቀን ጀምሮ ወራቱ ረዘመ፥ ሀያ ዓመትም ሆነ፥ የእስራኤልም ቤት ሁሉ አዝኖ እግዚአብሔርን ተከተለ።


跟着我们:

广告


广告