Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 26:18 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሞሬታዊው ሚክያስ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነቢይ ነበረ፥ ለይሁዳም ሕዝብ ሁሉ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል ብሎ ተናገረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “ሞሬታዊው ሚክያስ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን፣ ለይሁዳም ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ሲል ትንቢት ተናግሮ ነበር፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ጽዮን እንደ ዕርሻ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ የቤተ መቅደሱም ኰረብታ፣ ዳዋ የወረሰው ጕብታ ይሆናል።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 “ሞሬታዊው ሚክያስ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ትንቢት ተናግሮ ነበር፤ እርሱም ለይሁዳ ሕዝብ ሁሉ፦ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል’ ብሎ ተናገረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 “ሕዝቅያስ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን የሞሬሼቱ ነቢይ ሚክያስ የሠራዊት አምላክ የተናገረውን የትንቢት ቃል ለሕዝቡ እንዲህ ሲል ዐውጆ ነበር፦ ‘ጽዮን እንደ ማሳ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ ቤተ መቅደሱም የተሠራበት ኰረብታ ዳዋ ይበቅልበታል።’

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 “ሞሬ​ታ​ዊው ሚክ​ያስ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ዘመን ትን​ቢት ይና​ገር ነበር፤ ለይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ሁሉ፦ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታ​ረ​ሳ​ለች፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ምድረ በዳ ትሆ​ና​ለች፤ የቤ​ቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆ​ናል ብሎ ተና​ገረ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 26:18
13 交叉引用  

“‘እኔ ጥንቱን እንደ ሠራሁት፥ ቀድሞውንም እንዳደረግሁት አልሰማህምን? አሁንም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር እስኪሆኑ ድረስ እንድታፈርስ አደረግሁህ።


ሕዝቅያስም ከኢየሩሳሌም ሰዎች ጋር ስለ ልቡ ኵራት ሰውነቱን አዋረደ፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ በሕዝቅያስ ዘመን አልመጣባቸውም።


በወንድሞቹና በሰማርያ ሠራዊትም ፊት፦ እነዚህ ደካሞች አይሁድ የሚሠሩት ምንድር ነው? ይተዉላቸዋልን? ይሠዋሉን? በአንድ ቀንስ ይጨርሳሉን? የተቃጠለውንስ ድንጋይ ከፍርስራሹ መልሰው ያድኑታልን? ብሎ ተናገረ።


በሜዳ ያለው ተራራዬ ሆይ፥ ባለጠግነትህንና መዝገብህን ሁሉ የኮረብታውን መስገጃዎችህም ስለ ኃጢአት በድንበሮችህ ሁሉ ለመበዝበዝ እሰጣለሁ።


ባቢሎንም የድንጋይ ቍልልና የቀበሮ ማደሪያ መደነቂያም ማፍዋጫም ትሆናለች፥ የሚቀመጥባትም ሰው አይገኝም።


ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፥ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይቀመጥባት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታምና በአካዝ በሕዝቅያስም ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው፥ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው፥ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።


ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የድንጋይ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል።


በመጨረሻውም ዘመን የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ጽዮን ተመልሻለሁ፥ በኢየሩሳሌምም መካከል እኖራለሁ፥ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላለች፥ የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ተራራ የተቀደሰ ተራራ ይባላል።


跟着我们:

广告


广告