Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 25:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከይሁዳ ንጉሥ ከአሞጽ ልጅ ከኢዮስያስ ከአሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእነዚህ በሀያ ሦስቱ ዓመታት፥ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፥ እኔም ማልጄ ተነሥቼ ተናገርኋችሁ፥ ነገር ግን አልሰማችሁም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የይሁዳ ንጉሥ የአሞን ልጅ ኢዮስያስ ከነገሠበት ከዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ሃያ ሦስት ዓመት ሙሉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ ደጋግሜም ነገርኋችሁ፤ እናንተ ግን አልሰማችሁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከይሁዳ ንጉሥ ከአሞጽ ልጅ ከኢዮስያስ ከዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእነዚህ በሀያ ሦስቱ ዓመታት፥ የጌታ ቃል ወደ እኔ መጣ፥ እኔም ማልጄ ተነሥቼ ተናገርኋችሁ፤ ተናገርሁ፥ ሆኖም ግን አልሰማችሁም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “የዓሞን ልጅ ኢዮስያስ በይሁዳ ከነገሠ ከዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እግዚአብሔር እስከ ዛሬ ድረስ ለኻያ ሦስት ዓመት ሲናገረኝ ቈይቶአል፤ የእርሱንም ቃል ለእናንተ ከመናገር ከቶ አልቦዘንኩም፤ እናንተ ግን ልብ ብላችሁ አላስተዋላችሁም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 “ከይ​ሁዳ ንጉሥ ከአ​ሞጽ ልጅ ከኢ​ዮ​ስ​ያስ ከዐ​ሥራ ሦስ​ተ​ኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእ​ነ​ዚህ በሃያ ሦስቱ ዓመ​ታት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እኔም ማልጄ ተነ​ሥቼ ተና​ገ​ር​ኋ​ችሁ፤ ነገር ግን አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም።”

参见章节 复制




ኤርምያስ 25:3
32 交叉引用  

አብረሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ፥ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሕቅን ከእርሱ ጋር ወሰደ፥ እንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ፤ ተነስቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ።


የእስራኤልም ንጉሥ ባሪያዎቹን “ሬማት ዘገለዓድ የእኛ እንደ ሆነች፥ እኛም ከሶርያ ንጉሥ እጅ ሳንወስዳት ዝም እንዳልን ታውቃላችሁን?” አላቸው።


እግዚአብሔርም “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ለአባቶቻችሁም እንዳዘዝሁት፥ ባባሪያዎቼ በነቢያት የላክሁላችሁን ትእዛዜንና ሥርዐቴን ሕጌንም ሁሉ ጠብቁ፤” ብሎ በእያንዳንዱ ነቢይና በእያንዳንዱ ባለ ራእይ አፍ በእስራኤልና በይሁዳ መሰከረ።


ወደ እግዚአብሔርም ይመልሱአቸው ዘንድ ነቢያትን ይሰድድላቸው ነበር፤ መሰከሩባቸውም፤ እነርሱ ግን አላደመጡም።


ኢዮስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የስምንት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ።


በነገሠም በስምንተኛው ዓመት ገና ብላቴና ሳለ የአባቱን የዳዊትን አምላክ ይፈልግ ጀመር፤ በአሥራ ሁለተኛውም ዓመት ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ከኮረብታው መስገጃዎችና ከማምለኪያ ዐፀዶቹ፥ ከተቀረጹትና ቀልጠው ከተሰሩት ምስሎች ያነጻ ጀመር።


በነገሠም በአሥራ ስምንተኛው ዓመት ምድሪቱንና የእግዚአብሔርን ቤት ካነጻ በኋላ፥ የኤዜልያስ ልጅ ሳፋን፥ የከተማይቱም አለቃ መዕሤያ፥ ታሪክ ጸሐፊም የኢዮአካዝ ልጅ ኢዮአክ የእግዚአብሔርን የአምላኩን ቤት ይጠግኑ ዘንድ ሰደዳቸው።


የአባቶቻቸውም አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡና ለማደሪያው ስላዘነ ማለዳ ተነሥቶ በመልክተኞቹ እጅ ወደ እነርሱ ይልክ ነበር።


እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፤ “ማልደህ ተነሣ፤ በፈርዖንም ፊት ቁም፤ እነሆ እርሱ ወደ ውኃ ይወርዳል፤ እንዲህም በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦


ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።


በይሁዳ ንጉሥ በአሞጽ ልጅ በኢዮስያስ ዘመን በመንግሥቱ በአሥራ ሦስተኛው ዓመት የእግዚአብሔር ቃል መጣለት።


አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ በማለዳ ተነሥቼ እያስጠነቀቅሁ፦ ቃሌን ስሙ በማለት አስጠንቅቄአቸው ነበር።


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቃሌን እንዳይሰሙ አንገታቸውን አደንድነዋልና እነሆ፥ በዚህች ከተማና በመንደሮችዋ ሁሉ ላይ የተናገርሁባትን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣለሁ።


በደኅንነትሽ ጊዜ ተናገርሁሽ፥ አንቺም፦ አልሰማም አልሽ። ከሕፃንነትሽ ጀምሮ ቃሌን አለመስማትሽ መንገድሽ ነው።


እግዚአብሔርም ማልዶ ተነሥቶ ባሪያዎቹን ነቢያትን ወደ እናንተ ላከ፥ እናንተም አላደመጣችሁም ጆሮአችሁንም አላዘነበላችሁም።


ያልሰማችሁትን በማለዳ ተነሥቼ ወደ እናንተ የላክኋቸውን የባሪያዎቼን የነቢያትን ቃል ባትሰሙ፥


ይህም የሆነው ቃሌን ስላልሰሙ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በማለዳ ተነሥቼ ባሪያዎቼን ነቢያትን ወደ እነርሱ ሰድጃለሁና፥ እናንተ ግን አልሰማችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።


ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ወደ እኔ መለሱ፥ እኔም በማለዳ ተነሥቼ ሳስተምራቸው ተግሣጽን ይቀበሉ ዘንድ አልሰሙም።


የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ልጆቹ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ ያዘዛቸው ቃል ተፈጸመ፥ ለአባታቸውም ትእዛዝ ታዝዘዋልና እስከ ዛሬ ድረስ አይጠጡም፥ እኔም በማለዳ ተነሥቼ ተናግሬአችኋለሁ፥ ተናገርሁ፥ ሆኖም አልሰማችሁኝም።


ደግሞም፦ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ ሥራችሁንም አሳምሩ፥ ታመልኩአቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፥ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠሁት ምድር ትቀመጣላችሁ እያልሁ በማለዳ ተነሥቼ ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር፥ እናንተ ግን ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም እኔንም አልሰማችሁኝም።


እንዲህም ሆነ፥ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ።


አንድ የመጽሐፍ ክርታስ ውሰድ፥ ለአንተም ከተናገርሁበት ቀን ከኢዮስያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤልና በይሁዳ ላይ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተናገርሁህን ቃል ሁሉ ጻፍበት።


በማለዳም ተነሥቼ ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ሰደድሁባችሁና፦ እንደዚህ እንደ ጠላሁት ያለ ርኩስ ነገር አታድርጉ አልኋችሁ።


አሁንም ይህን ነገር ሁሉ ስላደረጋችሁ፥ በማለዳም ተነሥቼ በተናገርኋችሁ ጊዜ ስላልሰማችሁ፥ በጠራኋችሁም ጊዜ ስላልመለሳችሁ፥


አባቶቻችሁ ከግብጽ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ በየዕለቱ እየማለድሁ ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር።


የመለከቱን ድምፅ የሚሰማ ሰው ባይጠነቀቅ፥ ሰይፍ መጥቶ ቢወስደው፥ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል።


የቀደሙት ነቢያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፥ እነርሱ ግን አልሰሙም፥ እኔንም አላደመጡም፥ እንደ እነርሱ አትሁኑ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ማለዳም ተነሥቶ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ በዚያ ጸለየ።


ማለዳም ደግሞ ወደ መቅደስ ደረሰ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ። ተቀምጦም ያስተምራቸው ነበር።


ከእግዚአብሔር የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማል፤ እናንተ ከእግዚአብሔር አይደላችሁምና ስለዚህ አትሰሙም።”


ቃሉን ስበክ፥ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፥ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ፥ ዝለፍና ገሥጽ ምከርም።


跟着我们:

广告


广告