Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 23:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በሰማርያ ነቢያት ላይ ስንፍናን አይቻለሁ፥ በበኣል ትንቢት ይናገሩ ነበር፥ ሕዝቤንም እስራኤል ያስቱ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “በሰማርያ ባሉ ነቢያት ላይ፣ ደስ የማያሰኝ ነገር አይቻለሁ፤ በበኣል ስም ትንቢት ተናገሩ፤ ሕዝቤን እስራኤልን አሳቱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በሰማርያ ነቢያት መካከል አጸያፊን ነገር አይቻለሁ፤ በበዓል ትንቢት ይናገሩ ነበር፥ ሕዝቤንም እስራኤልን ያስቱ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የሰማርያ ነቢያት የሠሩትን አጸያፊ ነገር አይቼአለሁ፤ እነርሱ በበዓል ስም እየተነበዩ ሕዝቤን እስራኤልን ያስታሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በበ​ዓል ትን​ቢት የተ​ና​ገ​ሩ​በ​ትን የሰ​ማ​ር​ያን ነቢ​ያት ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን አይ​ቻ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አሳ​ት​ዋ​ቸው።

参见章节 复制




ኤርምያስ 23:13
12 交叉引用  

ኤልያስም “ከበኣል ነቢያት አንድ ሰው እንዳያመልጥ ያዙ!” አላቸው። ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ በዚያ አሳረዳቸው።


ምናሴም እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት ካጠፋቸው ከአሕዛብ ይልቅ ክፉ ይሠሩ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳተ።


ይህን ሕዝብ የሚመሩ ያስቱአቸዋል፥ ተመሪዎቹም ይጠፋሉ።


ካህናቱም፦ እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፥ ባለ ኦሪቶችም አላወቁኝም፥ ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥ ነቢያትም በበኣል ትንቢት ተናገሩ፥ የማይረባንም ነገር ተከተሉ።


እነሆ፥ ሐሰትን በሚያልሙ በሚናገሩም በሐሰታቸውና በድፍረታቸውም ሕዝቤን በሚያስቱ በነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እኔም አልላክኋቸውም አላዘዝኋቸውምም ለእነዚህም ሕዝብ በማናቸውም አይረቡአቸውም፥ ይላል እግዚአብሔር።


አንድ የመጽሐፍ ክርታስ ውሰድ፥ ለአንተም ከተናገርሁበት ቀን ከኢዮስያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤልና በይሁዳ ላይ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተናገርሁህን ቃል ሁሉ ጻፍበት።


ግልሙትናና የወይን ጠጅ ስካርም አእምሮን ያጠፋል።


የግልሙትና መንፈስ ሕዝቤን አስቶአቸዋልና፥ እነርሱም ከአምላካቸው ርቀው አመንዝረዋልና በትራቸውን ይጠይቃሉ፥ ዘንጋቸውም ይመልስላቸዋል።


ይህ ሁሉ ስለ ያዕቆብ በደልና ስለ እስራኤል ቤት ኃጢአት ነው። የያዕቆብም በደል ምንድር ነው? ሰማርያ አይደለችምን? የይሁዳስ የኮረብታው መስገጃ ምንድር ነው? ኢየሩሳሌም አይደለችምን?


跟着我们:

广告


广告