Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 22:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤት እንዲህ ይላልና፦ አንተ በእኔ ዘንድ እንደ ገለዓድና እንደ ሊባኖስ ራስ ነህ፥ ነገር ግን በእርግጥ ምድረ በዳ ማንም የማይቀመጥባቸውም ከተሞች አደርግሃለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት እንዲህ ይላል፤ “አንተ ለእኔ እንደ ገለዓድ፣ እንደ ሊባኖስ ተራራ ጫፍ ውብ ብትሆንም፣ በርግጥ እንደ ምድረ በዳ፣ ሰው እንደማይኖርባቸው ከተሞች አደርግሃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ጌታ ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤት እንዲህ ይላልና፦ አንተ በእኔ ዘንድ እንደ ገለዓድና እንደ ሊባኖስ ራስ ነህ፥ ነገር ግን በእርግጥ ምድረ በዳ ማንም የማይቀመጥባቸውም ከተሞች አደርግሃለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “የይሁዳ ነገሥታት ቤተ መንግሥት የገለዓድን አገርና የሊባኖስን ተራራዎች ያኽል ለእኔ የተዋበ ነው፤ ነገር ግን ማንም የማይኖርበት ባድማ አደርገዋለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤት እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “አንተ በእኔ ዘንድ እንደ ገለ​ዓ​ድና እንደ ሊባ​ኖስ ራስ ነህ፤ በር​ግጥ ምድረ በዳና ማንም የማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው ከተ​ሞች አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 22:6
26 交叉引用  

እንጀራም ሊበሉ ተቀመጡ ዓይናቸውንም አንሥተው አዩ፥ እነሆም የእስማኤላውያን ነገዶች ወደ ግብፅ ለመውረድ ከገለዓድ መጡ ግመሎቻቸውም ሽቱና በለሳን ከርቤም ተጭነው ነበር።


ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፥ እነሆ፥ አንቺ ወብ ነሽ፥ በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እንደ ርግቦች ናቸው፥ ጠጕርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ እንደ ፍየል መንጋ ነው።


እግሮቹ በምዝምዝ ወርቅ እንደ ተመሠረቱ እንደ ዕብነ በረድ ምሰሶች ናቸው፥ መልኩ እንደ ሊባኖስና እንደ ዝግባ ዛፍ መልካም ነው።


የተመሸገችው ከተማ ብቻዋን ሆነች፥ እንደ ምድረ በዳ ሆና የተፈታችና የተተወች መኖሪያ ናት፥ በዚያም ጥጃ ይሰማራል በዚያም ይተኛል ቅርንጫፍዋንም ይበላል።


አንተም፦ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሲባኖስ ጥግ ላይ ወጥቻለሁ፥ ረጃጅሞቹንም ዝግባዎች የተመረጡትንም ጥንዶች እቈርጣለሁ፥ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ።


እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው? አልሁ። እርሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ ከተሞች የሚኖሩባቸውን አጥተው እስኪፈርሱ ድረስ፥ ቤቶችም ሰው አልቦ እስኪሆኑ ምድርም ፈጽማ ባድማ ሆና እስክትቀር ድረስ፥


የይሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።


እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፥ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።


እኔ ሕያው ነኝና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን የቀኝ እጄ ማኅተም ቢሆን ኖሮ እንኳ፥ ከዚያ እነቅልህ ነበር፥ ይላል እግዚአብሔር፥


ሞሬታዊው ሚክያስ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነቢይ ነበረ፥ ለይሁዳም ሕዝብ ሁሉ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል ብሎ ተናገረ።


መከራ በመከራ ላይ ተጠርቶአል፥ ምድርም ሁሉ ተበዝብዛለችና፥ በድንገትም ድንኳኔ በቅጽበት ዓይንም መጋረጃዎቼ ጠፉ።


አንበሳ ከጭፍቅ ዱር ወጥቶአል፥ አሕዛብንም የሚዘርፍ ተነሥቶአል፥ ምድርሽን ባድማ ያደርግ ዘንድ ከስፍራው ወጥቶአል፥ ከተሞችሽም ሰው የሌለባቸው ፍርስራሾች ይሆናሉ።


እናታችሁ እጅግ ታፍራለች፥ የወለደቻችሁም ትጐሰቍላለች፥ እነሆ፥ በአሕዛብ መካከል ኋለኛይቱ ትሆናለች፥ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር በረሀም ትሆናለች።


ምድሪቱም ባድማ ትሆናለችና ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም አደባባይ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ አጠፋለሁ።


በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አልሆነም?


ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፥ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይቀመጥባት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፥ ኢየሩሳሌም የድንጋይ ክምር ትሆናለች፥ የቤቱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል።


ሊባኖስ ሆይ፥ ደጆችህን ክፈት፥ እሳትም ዝግባዎችህን ትብላ።


የሮቤልና የጋድ ልጆችም እጅግ ብዙ እንስሶች ነበሩአቸው፤ እነሆም፥ የኢያዜር ምድርና የገለዓድ ምድር ለእንስሶች የተመቸ ስፍራ እንደ ነበረ ባዩ ጊዜ፥


እኔ ልሻገር፥ በዮርዳኖስም ማዶ ያለችውን መልካሚቱን ምድር ያንም መልካሙን ተራራማውን አገር ሊባኖስንም ልይ።


跟着我们:

广告


广告