Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 22:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ውሽሞችሽ ሁሉ ጠፍተዋልና ወደ ሊባኖስ ወጥተሽ ጩኺ፥ በባሳን ላይ ድምፅሽን አንሺ፥ በዓባሪምም ውስጥ ሆነሽ ጩኺ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 “ሊባኖስ ላይ ወጥተሽ ጩኺ፤ ድምፅሽን በባሳን አሰሚ፤ በዓባሪም ሆነሽ ጩኺ፤ ወዳጆችሽ ሁሉ ወድመዋልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 “ውሽሞችሽ ሁሉ ጠፍተዋልና ወደ ሊባኖስ ወጥተሽ ጩኺ፤ በባሳን ላይ ድምፅሽን ከፍ አድርጊ፤ ከዓባሪምም ሆነሽ ጩኺ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! የጦር ጓደኞቻችሁ ሁሉ ስለ ተሸነፉ ወደ ሊባኖስ ሂዱና ጩኹ፤ ወደ ባሳን ምድርም ሄዳችሁ አልቅሱ፤ በሞአብ ተራራዎች ላይ ሆናችሁም ተጣሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ወዳ​ጆ​ችሽ ሁሉ ጠፍ​ተ​ዋ​ልና ወደ ሊባ​ኖስ ወጥ​ተሽ ጩኺ፤ በባ​ሳ​ንም ላይ ድም​ፅ​ሽን አንሺ፤ በባ​ሕ​ሩም ማዶ ጩኺ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 22:20
22 交叉引用  

የባቢሎንም ንጉሥ ለግብጽ ንጉሥ የነበረውን ሁሉ ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ወስዶ ነበርና የግብጽ ንጉሥ ከዚያ ወዲያ ከአገሩ አልወጣም።


ወደ አንቺ የሰበሰብሻቸው በጮኽሽ ጊዜ ይታደጉሽ፥ ንፋስ ግን ይወስዳቸዋል ሽውሽውታም ሁሉን ያስወግዳቸዋል። በእኔ የታመነ ግን ምድሪቱን ይገዛል፥ የተቀሰውንም ተራራዬን ይወርሳል።


እግርሽን ከሸካራ መንገድ ጕሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ፥ አንቺ ግን፦ እጨክናለሁ፥ እንግዶችን ወድጄአለሁና፥ እከተላቸዋለሁም አልሽ።


መንገድሽን ትለውጪ ዘንድ ለምን እጅግ ትሮጫለሽ? አሦር እንዳሳፈረሽ ግብጽ ያሳፍርሻል።


እግዚአብሔር የታመንሽባቸውን ጥሎአልና፥ በእነርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ።


በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይጠብቃቸዋል፥ ውሽሞችሽም ተማርከው ይሄዳሉ፥ በዚያን ጊዜም ስለ ክፋትሽ ሁሉ ታፍሪያለሽ ትጐሳቈይማለሽ።


ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ ባሪያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፥ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመደነቂያና ለማፍዋጫም ለዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


በሰው ዘንድ፦ ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ ከእርሱም ዘንድ ሄዳ ሌላ ወንድ ብታገባ፥ በውኑ ደግሞ ወደ እርሱ ትመለሳለችን? ያች ሴት እጅግ የረከሰች አይደለችምን? ይባላል። አንቺ ከብዙ ውሽሞች ጋር አመንዝረሻል፥ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል እግዚአብሔር።


አንቺም የተበዘበዝሽ ሆይ፥ ምን ታደርጊአለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም ባጌጥሽ ጊዜ፥ ዓይንሽንም በኵል በተኳልሽ ጊዜ፥ በከንቱ ታጌጫለሽ፥ ውሽሞችሽ አቃለሉሽ፥ ነፍስሽን ይሹአታል።


ቆፍ። ውሽሞቼን ጠራሁ እነርሱም አታለሉኝ፥ ካህናቶቼና ሽማግሌዎቼ ሰውነታቸውን ያበረቱ ዘንድ መብል ሲፈልጉ በከተማ ውስጥ ሞቱ።


ቤት። በሌሊት እጅግ ታላቅሳለች፥ እንባዋም በጉንጭዋ ላይ አለ፥ ከውሽሞችዋ ሁሉ የሚያጽናናት የለም፥ ወዳጆችዋ ሁሉ ወነጀሉአት ጠላቶችም ሆኑአት።


ስለዚህ፥ ኦሖሊባ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፍስሽ ከእነርሱ የተለየች ውሽሞችሽን አስነሣብሻለሁ፥ በዙሪያሽም በአንቺ ላይ አመጣቸዋለሁ።


ስለዚህ በፍቅር በተከተለቻቸው በውሽሞችዋ በአሦራውያን እጅ አሳልፌ ሰጠኋት።


ከባሳን ኮምቦል መቅዘፊያሽን ሠርተዋል፥ በዝሆን ጥርስ ከታሻበ ከኪቲም ደሴቶች ዛፍ መቀመጫዎችሽን ሠርተዋል።


እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ወደዚህ ወደ ዓባሪም ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤልም ልጆች የሰጠኋትን ምድር እይ፤


ወደዚህ በኢያሪኮ አንጻር በሞዓብ ምድር በዓባሪም ተራራ ውስጥ ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤልም ልጆች ርስት አድርጌ የምሰጣቸውን የከነዓንን ምድር እይ፤


跟着我们:

广告


广告