Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 21:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ፣ የመልክያን ልጅ ፋስኮርን እንዲሁም የመዕሤያን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን ወደ እርሱ በላከ ጊዜ፣ ቃል ከእግዚአብሔር ወደ ኤርምያስ መጣ፤ የተላኩትም እንዲህ ብለውት ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፤ ይህም የሆነው ንጉሡ ሴዴቅያስ የመልክያን ልጅ ጳስኮርንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል በላከበት ጊዜ ነው፦

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ የመልክያን ልጅ ፓሽሑርንና የመዕሤያን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን ወደ እኔ ልኮ እንዲህ ሲል አስጠየቀኝ፦

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ የመ​ል​ክ​ያን ልጅ ጳስ​ኮ​ር​ንና የካ​ህ​ኑን የመ​ዕ​ሴ​ይን ልጅ ሶፎ​ን​ያ​ስን ወደ ኤር​ም​ያስ በላከ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ እን​ዲ​ህም አለ፦

参见章节 复制




ኤርምያስ 21:1
20 交叉引用  

“አባቶቻችን በእርስዋ የተጻፈውን ሁሉ ይሠሩ ዘንድ የዚህችን መጽሐፍ ቃል ስላልሰሙ በላያችን የነደደ የእግዚአብሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳችሁ ስለ እኔና ስለ ሕዝቡ ስለ ይሁዳም ሁሉ የዚህችን የተገኘችውን መጽሐፍ ቃል እግዚአብሔርን ጠይቁ፤” ብሎ አዘዛቸው።


የኢዮስያስም ልጆች፤ በኵሩ ዮሐናን፥ ሁለተኛውም ኢዮአቄም፥ ሦስተኛውም ሴዴቅያስ፥ አራተኛውም ሰሎም።


የመልክያ ልጅ የጳስኮር ልጅ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፤ የኢሜር ልጅ የምሺላሚት ልጅ የሜሱላም ልጅ የየሕዜራ ልጅ የዓዲኤል ልጅ መዕሣይ፤


ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጕልማሶቻቸውን በቤተመቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጕልማሳውንና ቈንጆይቱን ሽማግሌውንና አሮጌውን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።


የቤቱንም ሥራ የሠሩ ወንድሞቻቸው ስምንት መቶ ሀያ ሁለት፥ የመልክያ ልጅ የፋስኮር ልጅ የዘካርያስ ልጅ የአማሲ ልጅ የፈላልያ ልጅ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፥


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ወዳለው ሕዝብ ሁሉ፥ ወደ ካህኑም ወደ መዕሤያ ልጅ ወደ ሶፎንያስ፥ ወደ ካህናቱም ሁሉ ደብዳቤዎችን በስምህ እንዲህ ስትል ልከሃል፦


ካህኑም ሶፎንያስ ይህን ደብዳቤ በነቢዩ በኤርምያስ ጆሮ አነበበው።


ወደ እግዚአብሔርም ቤት በበረኛው በሰሎም ልጅ በመዕሤያ ጓዳ በላይ ባለው በአለቆች ጓዳ አጠገብ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ጌዴልያ ልጅ ወደ ሐናን ልጆች ጓዳ አገባኋቸው።


የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር በይሁዳ ያነገሠው የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ በኢዮአቄም ልጅ በኢኮንያን ፋንታ ነገሠ።


ንጉሡ ሴዴቅያስ ልኮ አስመጣው፥ ንጉሡም በቤቱ፦ በውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ቃል አለን? ብሎ በቈይታ ጠየቀው። ኤርምያስም፦ አዎን አለ። ደግሞም፦ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፈህ ትሰጣለህ አለ።


ንጉሡም ሴዴቅያስ፦ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ስለ እኛ ጸልይ ብሎ የሰሌምያን ልጅ ዮካልንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ላከ።


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከእኔ ትጠይቁ ዘንድ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ እነሆ፥ ሊረዳችሁ የወጣው የፈርዖን ሠራዊት ወደ አገሩ ወደ ግብጽ ይመለሳል።


ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ የተናገረውን ቃል የማታን ልጅ ስፋጥያስ፥ የጳስኮርም ልጅ ጎዶልያስ፥ የሰሌምያም ልጅ ዮካል፥ የመልክያም ልጅ ጳስኮር ሰሙ።


ንጉሡም ሴዴቅያስ ልኮ በእግዚአብሔር ቤት ወደ ነበረው ወደ ሦስተኛው መግቢያ ወደ እርሱ ነቢዩን ኤርምያስን አስመጣው፥ ንጉሡም ኤርምያስን፦ አንዲት ነገር እጠይቅሃለሁ፥ ምንም አትሸሽገኝ አለው።


የዘበኞቹም አለቃ ታላቁን ካህን ሠራያን ሁለተኛውንም ካህን ሶፎንያስን ሦስቱንም በረኞች ወሰደ፥


跟着我们:

广告


广告