Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 20:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ለራስህና ለወዳጆችህ ሁሉ ፍርሃት አደርግሃለሁ፥ እነርሱም በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ ዓይኖችህም ያያሉ፥ ይሁዳንም ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል በሰይፍም ይገድላቸዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘አንተንና ወዳጆችህ ሁሉ ለሽብር እዳርጋለሁ፤ የገዛ ዐይንህ እያየ በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ። ይሁዳን ሁሉ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል፤ በሰይፍም ይገድላቸዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ጌታ እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ለራስህና ለወዳጆችህ ሁሉ ፍርሃት አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ ዐይኖችህም ያያሉ፤ ይሁዳንም ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል በሰይፍም ይገድላቸዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እግዚአብሔር ራሱ እንዲህ ብሎአል፦ ‘ለራስህና ለጓደኞችህም ጭምር አሸባሪ ላደርግህ ነው፤ እነርሱም ሁሉ በጠላቶቻቸው ሰይፍ ሲገደሉ ታያለህ፤ የይሁዳን ሕዝብ ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ ሥልጣን ሥር አደርጋለሁ፤ እርሱ እኩሌቶቹን እስረኛ አድርጎ ወደ ባቢሎን ይወስዳቸዋል፤ እኩሌቶቹንም እዚሁ ይገድላቸዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ አን​ተን ከወ​ዳ​ጆ​ችህ ሁሉ ጋር አፈ​ል​ስ​ሃ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ሰይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ዐይ​ኖ​ች​ህም ያያሉ፤ አን​ተ​ንና ይሁ​ዳ​ንም ሁሉ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እር​ሱም ወደ ባቢ​ሎን ያፈ​ል​ሳ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍም ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 20:4
22 交叉引用  

የሴዴቅያስንም ልጆች በፊቱ ገደሉአቸው፤ የሴዴቅያስንም ዐይኖች አወጡ፤ በሰንሰለትም አሰሩት፤ ወደ ባቢሎንም ወሰዱት።


ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ የሚሉ፥ በልባቸውም እልከኝነት የሚሄዱ፥ ያመልኩአቸውና ይሰግዱላቸው ዘንድ ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ እነዚህ ክፉ ሕዝብ አንዳች እንዳማትረባ እንደዚች መታጠቂያ ይሆናሉ።


የደቡብ ከተሞች ተዘግተዋል፥ የሚከፍታቸውም የለም፥ ይሁዳ ሁሉ ተማርኮአል፥ ፈጽሞ ተማርኮአል።


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቃሌን እንዳይሰሙ አንገታቸውን አደንድነዋልና እነሆ፥ በዚህች ከተማና በመንደሮችዋ ሁሉ ላይ የተናገርሁባትን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣለሁ።


አንተም፥ ጳስኮር ሆይ፥ በቤትህም የሚኖሩት ሁሉ ተማርካችሁ ትሄዳላችሁ፥ አንተም በሐሰትም ትንቢት የተናገርህላቸው ወዳጆችህ ሁሉ ወደ ባቢሎን ትገባላችሁ፥ በዚያም ትሞታላችሁ፥ በዚያም ትቀበራላችሁ።


ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ ባሪያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፥ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመደነቂያና ለማፍዋጫም ለዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ስለሚናገሩላችሁ ስለ ቆላያ ልጅ ስለ አክዓብና ስለ መዕሤያ ልጅ ስለ ሴዴቅያስ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፥ በዓይኖቻችሁም ፊት ይገድላቸዋል።


ፈርተው ወደ ኋላ ሲመለሱ፥ ኃያላኖቻቸውም ሲደበደቡ ወደ ኋላቸውም ሳይመለከቱ ፈጥነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዚህና በዚያ ድንጋጤ አለ፥ ይላል እግዚአብሔር።


የዘበኞቹም አለቃ ታላቁን ካህን ሠራያን ሁለተኛውንም ካህን ሶፎንያስን ሦስቱንም በረኞች ወሰደ፥


የባቢሎንም ንጉሥ መታቸው፥ በሐማትም ምድር ባለችው በሪብላ ገደላቸው። እንዲሁ ይሁዳ ከአገሩ ተማረከ።


የጠላት ሰይፍና ድንጋጤ ከብበዋችኋልና ወደ ሜዳ አትውጡ በመንገድም ላይ አትሂዱ።


ከመሠዊያዬ ያልተቆረጠ ልጅህ ቢገኝ ዓይንህን ያፈዝዘዋል፥ ነፍስህንም ያሳዝናል ከቤትህም የሚወለዱ ሰዎች ሁሉ በጎልማስነት ይሞታሉ።


跟着我们:

广告


广告