Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 2:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ፍሬዋንና በረከትዋንም ትበሉ ዘንድ ወደ ፍሬያማ ምድር አገባኋችሁ፥ ነገር ግን በገባችሁ ጊዜ ምድሬን አረከሳችሁ፥ ርስቴንም አጐሳቈላችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እኔ፣ ፍሬዋንና በረከቷን እንድትበሉ፣ ለም ወደ ሆነ መሬት አመጣኋችሁ፤ እናንተ ግን መጥታችሁ ምድሬን አረከሳችሁ፤ ርስቴንም ጸያፍ አደረጋችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ፍሬዋንና በረከትዋንም እንድትበሉ ወደ ፍሬያማ ምድር አስገባኋችሁ፤ ነገር ግን በገባችሁ ጊዜ ምድሬን አረከሳችሁ፥ ርስቴንም የተጠላች አደረጋችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የምታስገኘውን ሰብልና ሌሎችን መልካም ነገሮች ሁሉ አግኝተው እንዲደሰቱ ለም ወደ ሆነች ምድር አገባኋቸው፤ እነርሱ ግን ምድሬን አበላሹ፤ የሰጠኋቸውን አገር አረከሱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ፍሬ​ዋ​ንና በረ​ከ​ቷ​ንም ትበሉ ዘንድ ወደ ቀር​ሜ​ሎስ አገ​ባ​ኋ​ችሁ፤ ነገር ግን በገ​ባ​ችሁ ጊዜ ምድ​ሬን አረ​ከ​ሳ​ችሁ፤ ርስ​ቴ​ንም አጐ​ሳ​ቈ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 2:7
28 交叉引用  

ምሽጎቹንም ከተሞች የሰባውንም ምድር ወሰዱ፥ መልካሙን ነገር የሞሉትን ቤቶች፥ የተማሱትንም ጕድጓዶች፥ ወይኖቹንና ወይራዎቹን ብዙዎቹንም የፍሬ ዛፎች ወረሱ፥ በሉም፥ ጠገቡም፥ ወፈሩም፥ በታላቅ በጎነትህም ደስ አላቸው።


ነገር ግን እንቢተኞች ነበሩ፥ ዐመፁብህም፥ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፥ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፥ እጅግም አስቈጡህ።


ምድሬንም በተጠሉ በጣዖቶቻቸው ሬሳዎች አርክሰዋልና፥ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና አስቀድሜ የበደላቸውንና የኃጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።


በሰው ዘንድ፦ ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ ከእርሱም ዘንድ ሄዳ ሌላ ወንድ ብታገባ፥ በውኑ ደግሞ ወደ እርሱ ትመለሳለችን? ያች ሴት እጅግ የረከሰች አይደለችምን? ይባላል። አንቺ ከብዙ ውሽሞች ጋር አመንዝረሻል፥ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል እግዚአብሔር።


ዓይንሽን አንሥተሽ ወደ ወናዎች ኮረብቶች ተመልከቺ፥ ያልተጋደምሽበት ስፍራ ወዴት አለ? ዓረባዊ በምድረ በዳ እንደሚቀመጥ አንቺ በመንገድ ላይ ተቀምጠሽ ትጠብቂያቸው ነበር፥ በግልሙትናሽና በኃጢአትሽ ምድሪቱን አረከስሽ።


በግልሙትናዋም በመቅለልዋም ምድሪቱ ረከሰች፥ እርስዋም ከድንጋይና ከግንድ ጋር አመነዘረች።


እነርሱም ገብተው ወረሱአት፥ ነገር ግን ቃልህን አልሰሙም በሕግህም አልሄዱም፥ ያደርጉም ዘንድ ካዘዝሃቸው ሁሉ ምንም አላደረጉም፥ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣህባቸው።


የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች ከታናሽነታቸው ጀምሮ በፊቴ ክፉ ነገርን ብቻ አድርገዋልና፥ የእስራኤልም ልጆች እኔን በእጃቸው ሥራ ከማስቈጣት በቀር ሌላ ሥራ አላደረጉምና።


ሥርዓቴንም ጥሰዋልና፥ ሰንበታቴንም አርክሰዋልና፥ ዓይናቸውም የአባቶቻቸውን ጣዖታቶች ተከትለዋልና።


እሰጣቸውም ዘንድ ወደ ማልሁላቸው ምድር ባገባኋቸው ጊዜ፥ ከፍ ያለውን ኮረብታ ሁሉ ቅጠልማውንም ዛፍ ሁሉ አዩ፥ በዚያም መሥዋዕታቸውን ሠዉ በዚያም የሚያስቈጣኝን ቍርባናቸውን አቀረቡ በዚያም ደግሞ ጣፋጩን ሽታቸውን አደረጉ በዚያም የመጠጥ ቍርባናቸውን አፈሰሱ።


በዚያ ቀን ከግብጽ ምድር ወዳዘጋጀሁላችሁ፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው፥ የምድርም ሁሉ ጌጥ ወደምትሆን ምድር አወጣቸው ዘንድ ማልሁላቸው፥


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዘንግተሽኛልና፥ ወደ ኋላሽም ጥለሽኛልና አንቺ ደግሞ ሴሰኝነትሽንና ግልሙትናሽን ተሸከሚ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት በምድራቸው በተቀመጡ ጊዜ በመንገዳቸውና በሥራቸው አረከሱአት፥ መንገዳቸውም በፊቴ እንደ መርገም አደፍ ነበረ።


በእግዚአብሔር ምድር ላይ አይቀመጡም፥ ኤፍሬምም ወደ ግብጽ ይመለሳል፥ በአሦርም ርኵስን ነገር ይበላሉ።


በዚህ ዕረፍት የላችሁምና ተነሥታችሁ ሂዱ፥ በርኵሰት ምክንያት ክፉ ጥፋት ታጠፋችኋለች።


እንዲህም ብለው ነገሩት፦ ወደ ላክኸን ምድር ደረስን፥ እርስዋም ወተትና ማር ታፈስሳለች፥ ፍሬዋም ይህ ነው።


በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና ሬሳው በእንጨት ላይ አይደር፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር እንዳታረክስ በእርግጥ በዚያው ቀን ቅበረው።


የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ሕዝቡ ነው፤ 2 ያዕቆብም የርስቱ ገምድ ነው።


መልካምም ይሆንልህ ዘንድ፥ እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብተህ እርስዋን ትወርስ ዘንድ፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ ያወጣልህ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ፊት ቅኑንና መልካሙን አድርግ።


跟着我们:

广告


广告