ኤርምያስ 2:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 የአንበሳ ደቦሎች በእርሱ ላይ አገሡ፥ ድምፃቸውንም ሰጡ፥ ምድሩንም ባድማ አደረጉ፥ ከተሞቹም ተቃጠሉ የሚቀመጥባቸውም የለም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 አንበሶች በርሱ ላይ አገሡ፤ በኀይለኛ ድምፅም ጮኹበት። ምድሩን ባድማ አድርገውበታል፤ ከተሞቹ ተቃጥለዋል፤ ወናም ሆነዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 የአንበሳ ደቦሎች በእርሱ ላይ አገሡ፥ ድምፃቸውንም አሰሙ፤ ምድሩንም ባድማ አደረጉ፥ ከተሞቹም ፈርሰዋል የሚቀመጥባቸውም የለም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ጠላቶችዋ እንደ ደቦል አንበሳ ያገሡባታል፤ አገርዋን ወደ ምድረ በዳ ለውጠውባታል፤ ከተሞችዋም ተቃጥለው ሰው የማይኖርባቸው ወና ሆነዋል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 የአንበሳ ደቦሎች በእርሱ ላይ አገሡ፤ በእርሱም ላይ ደነፉ፤ ምድሩንም ባድማ አደረጉ፤ ከተሞቹንም አፈረሱ፤ የሚቀመጥባቸውም የለም። 参见章节 |