Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 19:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ይህችንም ከተማ ለመደነቂያና ለማፍዋጫ አደርጋታለሁ፥ የሚያልፍባትም ሁሉ ስለ ተደረገባት መቅሠፍት ሁሉ ይደነቃል ከንፈሩንም ይመጥጣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ይህችን ከተማ ድምጥማጧን አጠፋለሁ፤ የድንጋጤና መሣለቂያም ምልክት አደርጋታለሁ፤ በዚያም የሚያልፉ ሁሉ ከቍስሎቿም የተነሣ ወይ ጉድ! ይላሉ፣ ያሾፋሉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ይህችንም ከተማ ለመሣቀቂና ለማፍዋጫ አደርጋታለሁ፤ የሚያልፍባትም ሁሉ ይሣቀቃል፥ ስለ ተደረገባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጭባታል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ይህችን ከተማ የፍርስራሽ ክምር አደርጋታለሁ፤ በዚያ በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነግጣል፤ በደረሰባት ችግርም ይገረማል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ይህ​ች​ንም ከተማ ለጥ​ፋ​ትና ለማ​ፍ​ዋጫ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ያ​ልፍ ሁሉ ስለ ተደ​ረ​ገ​ባት መቅ​ሠ​ፍት ሁሉ ይደ​ነ​ግ​ጣል፤ ያፍ​ዋ​ጫ​ልም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 19:8
14 交叉引用  

ከፍ ከፍ ብሎ የነበረው ይህ ቤት ባድማ ይሆናል፤ በዚያም የሚያልፍ ሁሉ እያፍዋጨ ‘እግዚአብሔር በዚህ አገርና በዚህ ቤት ስለምን እንዲህ አደረገ?’ ብሎ ይደነቃል።


ምድራቸውን ለመደነቂያና ለዘላለም ማፍዋጫ አድርገዋል፥ የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፥ ራሱንም ያነቃንቃል።


ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ባድማና መደነቂያ ማፍዋጫም እርግማንም አደርጋቸው ዘንድ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ነገሥታትዋንም አለቆችዋንም አጠጣኋቸው።


ባሶራ መደነቂያና መሰደቢያ መረገሚያም እንድትሆን በራሴ ምያለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ከተሞችዋም ሁሉ ለዘላለም ባድማ ይሆናሉ።


ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ ሰው አይቀመጥባትም፥ በባቢሎንም በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል በመጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጫል።


የአሕዛብ ነጋዴዎች አፍዋጩብሽ፥ አንቺ ለድንጋጤ ሆነሻል፥ እስከ ዘላለምም አትገኚም።


ምድሪቱንም የተፈታች አደርጋለሁ፤ የሚቀመጡባት ጠላቶቻችሁም በእርስዋ የተነሣ ይደነቃሉ።


አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


ተዘልላ የተቀመጠች፥ በልብዋም፦ እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም ያለች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፥ አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ እንዴት ሆነች! በእርስዋ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፍዋጫል።


እግዚአብሔርም በሚያገባህ በአሕዛብ መካከል ሁሉ ድንጋጤ ምሳሌም ተረትም ትሆናለህ።


ከዚያም በኋላ የሚነሣ ትውልድ ከእናንተም በኋላ የሚሆኑ ልጆቻችሁ ከሩቅ አገርም የሚመጣ እንግዳ፥ የዚህን አገር መቅሠፍት፥ እግዚአብሔርም በእርስዋ ያደረገውን ሥቃይዋን፥


跟着我们:

广告


广告