Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 19:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እንዲህም በል፦ የይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሰማውን ሰው ጆሮ ጭው የሚያደርግ ክፉ ነገር፥ እነሆ፥ በዚህ ስፍራ አመጣለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እንዲህም በል፤ ‘የይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ለሰሚው ሁሉ ጆሮ የሚዘገንን ክፉ ነገር እነሆ በዚህ ስፍራ አመጣለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እንዲህም በል፦ ‘የይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ክፉን ነገር በዚህ ስፍራ ማምጣቴን የሚሰማ ጆሮ ሁሉ ጭው ይልበታል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ‘የይሁዳ ነገሥታትና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሁሉ እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የምነግራችሁን አድምጡ፤ እነሆ በጆሮው ለሚሰማው ሰው ሁሉ የሚዘገንን መቅሠፍት አመጣለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 “የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታ​ትና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ኖሩ ሆይ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በዚህ ስፍራ ክፉ ነገ​ርን አመ​ጣ​ለሁ፤ የሰ​ማ​ውም ሰው ሁሉ ይደ​ነ​ግ​ጣል፤ ጆሮ​ዎ​ቹ​ንም ይይ​ዛል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 19:3
18 交叉引用  

ባለፈም ጊዜ ይወስዳችኋል፥ ማለዳ ማለዳ ቀንና ሌሊት ያልፋል፥ ወሬውንም ማስተዋል ድንጋጤ ይሆናል።


ለንጉሡና ለንጉሥ እናት ለእቴጌይቱ፦ የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ተዋርዳችሁ ተቀመጡ በል።


እንዲህም በላቸው፦ በእነዚህ በሮች የምትገቡ፥ እናንተ የይሁዳ ነገሥታት፥ ይሁዳም ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁሉ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።


አሁን እንግዲህ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚቀመጡ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ክፉ ነገር እፈጥርባችኋለሁ፥ አሳብንም አስብባችኋለሁ፥ አሁንም ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ መንገዳችሁንና ሥራችሁንም አቅኑ ብለህ ተናገራቸው።


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቃሌን እንዳይሰሙ አንገታቸውን አደንድነዋልና እነሆ፥ በዚህች ከተማና በመንደሮችዋ ሁሉ ላይ የተናገርሁባትን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣለሁ።


እነሆ፥ ስሜ የተጠራባትን ከተማ አስጨንቃት ዘንድ እጀምራለሁ፥ በውኑ እናንተ ያልተቀጣችሁ ትሆናላችሁን? በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁና ያለ ቅጣት አትቀሩም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በተናገርኋቸው ጊዜ አልሰሙምና፥ በጠራኋቸውም ጊዜ አልመለሱልኝምና የተናገርሁባቸውን ክፉ ነገር ሁሉ በይሁዳ ላይ በኢየሩሳሌምም በሚቀመጡ ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ።


ይህም የሆነው ያስቈጡኝ ዘንድ ስላደረጉት ክፋት፥ ለማያውቁአቸውም ለሌሎች አማልክት ያጥኑ ዘንድ ያመልኩአቸውም ዘንድ ስለሄዱ ነው።


ምድር ሆይ፥ ስሚ፥ እነሆ፥ ቃሌን ስላልሰሙ ሕጌንም ስለ ጣሉ፥ በዚህ ሕዝብ ላይ የአሳባቸውን ፍሬ፥ ክፉን ነገር አመጣባቸዋለሁ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ክፉ ነገር፥ አንድ ክፉ ነገር፥ እነሆ፥ ይመጣል።


ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።


እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው፦ እነሆ፥ የሰማውን ሁሉ ሁለቱ ጆሮቹ ጭው የሚያደርግ አንድ ነገርን በእስራኤል አደርጋለሁ።


跟着我们:

广告


广告