Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 18:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ምድራቸውን ለመደነቂያና ለዘላለም ማፍዋጫ አድርገዋል፥ የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፥ ራሱንም ያነቃንቃል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ምድራቸው ባድማ፣ ለዘላለም መሣለቂያ ይሆናል፤ በዚያ የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፤ በመገረምም ራሱን ይነቀንቃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ምድራቸውን ለመሣቀቂያና ለዘለዓለም ማፍዋጫ አድርገዋል፤ የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፥ ራሱንም ይነቀንቃል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ምድራቸው የዘለዓለም መሳለቂያ፥ ባድማ ትሆናለች፤ በአጠገብዋ የሚያልፉ ሁሉ በማፌዝ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ምድ​ራ​ቸ​ውን ለጥ​ፋ​ትና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ማፍ​ዋጫ አድ​ር​ገ​ዋል፤ የሚ​ያ​ል​ፍ​ባት ሁሉ ይደ​ነ​ቃል፤ ራሱ​ንም ያነ​ቃ​ን​ቃል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 18:16
35 交叉引用  

ከፍ ከፍ ብሎ የነበረው ይህ ቤት ባድማ ይሆናል፤ በዚያም የሚያልፍ ሁሉ እያፍዋጨ ‘እግዚአብሔር በዚህ አገርና በዚህ ቤት ስለምን እንዲህ አደረገ?’ ብሎ ይደነቃል።


ስለዚህም የእግዚአብሔር ቍጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ሆነ፤ በዓይናችሁም እንደምታዩ ለድንጋጤና ለመደነቂያ፥ ለመዘበቻም አሳልፎ ሰጣቸው።


እግዚአብሔር ስለ እርሱ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ቀላል አድርጋሃለች፥ በንቀትም ስቃብሃለች፥ የኢየሩሳሌም ልጅ ራስዋን ነቅንቃብሃለች።


እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው? አልሁ። እርሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ ከተሞች የሚኖሩባቸውን አጥተው እስኪፈርሱ ድረስ፥ ቤቶችም ሰው አልቦ እስኪሆኑ ምድርም ፈጽማ ባድማ ሆና እስክትቀር ድረስ፥


ይህችንም ከተማ ለመደነቂያና ለማፍዋጫ አደርጋታለሁ፥ የሚያልፍባትም ሁሉ ስለ ተደረገባት መቅሠፍት ሁሉ ይደነቃል ከንፈሩንም ይመጥጣል።


ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ ባሪያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፥ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመደነቂያና ለማፍዋጫም ለዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


በሰይፍም በራብም በቸነፈርም አሳዳድዳቸዋለሁ፥ ባሳደድሁባቸውም አሕዛብ ሁሉ ዘንድ ለጥላቻና ለመደነቂያ ለማፍዋጫም ለመሰደቢያም እንዲሆኑ በምድር መንግሥታት ሁሉ ዘንድ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ቍጣዬና መዓቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፥ እንዲሁ ወደ ግብጽ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ ይፈስስባችኋል፥ እናንተም ለጥላቻና ለመደነቂያ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ትሆናላችሁ፥ ይህንም ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩትም።


ወደ ግብጽም ይገቡ ዘንድ በዚያም ይቀመጡ ዘንድ ፊታቸውን ያቀኑትን የይሁዳን ቅሬታ እወስዳለሁ፥ ሁሉም ይጠፋሉ፥ በግብጽም ምድር ይወድቃሉ፥ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፥ ከታናሹም ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በሰይፍና በራብ ይሞታሉ፥ ለጥላቻና ለመደነቂያ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ይሆናሉ።


እስራኤል ለአንተ መሳቂያ አልሆነምን? ወይስ በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን? ስለ እርሱ በተናገርህ ጊዜ ራስህን ትነቀንቃለህ።


ባሶራ መደነቂያና መሰደቢያ መረገሚያም እንድትሆን በራሴ ምያለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ከተሞችዋም ሁሉ ለዘላለም ባድማ ይሆናሉ።


ኤዶምያስም መደነቂያ ትሆናለች፥ የሚያልፍባትም ሁሉ ይደነቃል፥ ስለ መጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጭባታል።


ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ ሰው አይቀመጥባትም፥ በባቢሎንም በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል በመጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጫል።


ባቢሎንም የድንጋይ ቍልልና የቀበሮ ማደሪያ መደነቂያም ማፍዋጫም ትሆናለች፥ የሚቀመጥባትም ሰው አይገኝም።


ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፥ ሰውም የማይቀመጥበት የሰውም ልጅ የማያልፍበት ምድር ሆኑ።


ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፥ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይቀመጥባት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


ላሜድ። እናንተ መንገድ አላፊዎች ሁሉ፥ በእናንተ ዘንድ ምንም የለምን? እግዚአብሔር በጽኑ ቍጣው ቀን እኔን እንዳስጨነቀበት በእኔ ላይ እንደ ተደረገው እንደ እኔ መከራ የሚመስል መከራ እንዳለ ተመልከቱ፥ እዩ።


ለምድሪቱም ሕዝብ፦ ጌታ እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ስለሚኖሩ ስለ እስራኤልም ምድር እንዲህ ይላል፦ ስለሚኖሩባት ሁሉ ግፍ ምድሪቱ ከነሞላዋ ትጠፋ ዘንድ እንጀራቸውን በችግር ይበላሉ ወኃቸውንም በድንጋጤ ይጠጣሉ።


የአሕዛብ ነጋዴዎች አፍዋጩብሽ፥ አንቺ ለድንጋጤ ሆነሻል፥ እስከ ዘላለምም አትገኚም።


ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ ባድማ አድርገዋችኋልና፥ ውጠዋችሁማልና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የሕዝብ ማላገጫ ሆናችኋልና


እጄንም እዘረጋባቸዋለሁ፥ በሚኖሩበትም ስፍራ ሁሉ ምድሪቱን ከዴብላታ ምድረ በዳ ይልቅ ውድማና በረሃ አደርጋታለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።


ምድሪቱንም የተፈታች አደርጋለሁ፤ የሚቀመጡባት ጠላቶቻችሁም በእርስዋ የተነሣ ይደነቃሉ።


ምድርም ከእነርሱ መጥፋት የተነሣ ባዶ ትቀራለች፤ እነርሱም ሳይኖሩ በተፈታችበት ዘመን ሰንበት በማድረግዋ ትደሰታለች፤ ፍርዴንም ስለ ናቁ፥ ነፍሳቸውም ሥርዓቴን ስለ ተጸየፈች የኃጢአታቸውን ቅጣት ይሸከማሉ።


አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና፦


የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና፦ ዋ፥ ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራ፥


እግዚአብሔር መቅሠፍትህን፥ የዘርህንም መቅሠፍት፥ ብዙ ዘመንም የሚኖረውን ታላቅ መቅሠፍት፥ ብዙ ዘመን የሚኖረውንም ክፉ ደዌ ያደርግብሃል።


ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው መቃጠልም እንደ ሆነባት፥ እንዳትዘራም እንዳታበቅልም፥ ማናቸውም ሣርና ልምላሜም እንዳይወጣባት፥ እግዚአብሔር በቁጣውና በመዓቱ እንደ ገለባበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ እንደ አዳማና እንደ ሲባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥


跟着我们:

广告


广告