Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 18:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአሕዛብ መካከል፦ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? ብላችሁ ጠይቁ። የእስራኤል ድንግል በጣም የሚያስደነግጠውን ነገር አድርጋለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እስኪ አሕዛብን፣ ‘እንዲህ ዐይነት ነገር በመካከላችሁ ተሰምቶ ያውቃል?’ ብላችሁ ጠይቁ። ድንግሊቱ እስራኤል፣ እጅግ ክፉ ነገር አድርጋለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ በአሕዛብ መካከል፦ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? ብላችሁ ጠይቁ። የእስራኤል ድንግል በጣም የሚያስደነግጠውን ነገር አድርጋለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን የመሰለ ነገር በሕዝቦች መካከል ተሰምቶ እንደ ሆነ ጠይቁ፤ የተለዩ የእስራኤል ሕዝብ በጣም አጸያፊ የሆነ ነገር አድርገዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ያደ​ረ​ገ​ች​ውን በጣም የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ውን ነገር የሚ​ሰ​ሙት እን​ዳለ አሕ​ዛ​ብን ጠይቁ።”

参见章节 复制




ኤርምያስ 18:13
14 交叉引用  

የቤቱ አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም ጸሐፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሐፊም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ልብሳቸውን ቀድደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፥ የራፋስቂስንም ቃል ነገሩት።


ከቶ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? እንዲህስ ያለ ነገር ማን አይቶአል? በውኑ አገር በአንድ ቀን ታምጣለችን? ወይስ በአንድ ጊዜ ሕዝብ ይወለዳልን? ጽዮን እንዳማጠች ወዲያው ልጆችዋን ወልዳለችና።


እንደዚህም ብለህ ትነግራቸዋለህ፦ የወገኔ ልጅ ድንግሊቱ በታላቅ ስብራትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰብራለችና ዓይኖቼ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፍስሱ።


በውኑ የሊባኖስ በረዶ የምድረ በዳውን ድንጋይ ይተዋልን? ወይስ ከሩቅ የምትመጣው ቀዝቃዛይቱ ፈሳሽ ውኃ ትደርቃለችን?


በኢየሩሳሌምም ነቢያት ላይ የሚያስደነግጥን ነገር አይቻለሁ፥ ያመነዝራሉ በሐሰትም ይሄዳሉ፥ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፥ ሁሉም እንደ ሰዶም የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።


የእስራኤል ድንግል ሆይ፥ እንደ ገና እሠራሻለሁ አንቺም ትሠሪያለሽ፥ እንደ ገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ከዘፋኞች ጋር ወደ ዘፈን ትወጫለሽ።


የምታስደንቅና የምታስደነግጥ ነገር በምድር ላይ ሆናለች፥


ሳምኬት። ጌታ ኃያላኖቼን ሁሉ ከውስጤ አስወገዳቸው፥ ጐልማሶቼን ያደቅቅ ዘንድ ጕባኤን ጠራብኝ፥ ጌታ ድንግሊቱን የይሁዳን ልጅ በመጥመቂያ እንደሚረገጥ አድርጎ ረገጣት።


በእስራኤል ቤት የሚያስፈራን ነገር አይቻለሁ፥ በዚያ በኤፍሬም ውስጥ ግልሙትና ተገኘ፥ እስራኤልም ረክሶአል።


የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በእናንተ ላይ ለሙሾ የማነሣውን ይህን ቃል ስሙ።


የእስራኤል ድንግል ወደቀች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሣም፥ በምድርዋ ላይ ተጣለች፥ የሚያስነሣትም የለም።


በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና።


ፍልስጥኤማውያንም ፈርተው፥ እግዚአብሔር ወደ ሰፈር መጥቶአል አሉ። ደግሞም እንዲህ አሉ፦ ወዮልን፥ ከዚህ አስቀድሞ እንዲህ ያለ ነገር አልሆነም።


跟着我们:

广告


广告