Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 17:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እንዲህም በላቸው፦ በእነዚህ በሮች የምትገቡ፥ እናንተ የይሁዳ ነገሥታት፥ ይሁዳም ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁሉ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እንዲህም በላቸው፤ ‘በእነዚህ በሮች የምትገቡ የይሁዳ ነገሥታት ሆይ፤ የይሁዳ ሕዝብና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሁሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እንዲህም በላቸው፦ ‘በእነዚህ በሮች የምትገቡ፥ የይሁዳ ነገሥታት ሆይ! ይሁዳም ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁሉ፥ የጌታን ቃል ስሙ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እኔ የምነግርህንም ቃል እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የይሁዳ ነገሥታትና ሕዝብ! እንዲሁም በእነዚህ ቅጽር በሮች የምትገቡ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፥ “በእ​ነ​ዚህ በሮች የም​ት​ገቡ እና​ንተ የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት፥ ይሁ​ዳም ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የም​ት​ኖሩ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።”

参见章节 复制




ኤርምያስ 17:20
13 交叉引用  

ለንጉሡና ለንጉሥ እናት ለእቴጌይቱ፦ የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ተዋርዳችሁ ተቀመጡ በል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፦ ሂድ፥ የይሁዳም ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝቡ ልጆች በር በኢየሩሳሌምም በሮች ሁሉ ቁም፥


እንዲህም በል፦ የይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሰማውን ሰው ጆሮ ጭው የሚያደርግ ክፉ ነገር፥ እነሆ፥ በዚህ ስፍራ አመጣለሁ።


ትተውኛልና፥ ይህንም ስፍራ እንግዳ አድርገውታልና፥ እነርሱና አባቶቻቸውም ለማያውቋቸው ለሌሎች አማልክት ዐጥነዋልና የይሁዳም ነገሥታት ይህን ስፍራ በንጹህ ደም ሞልተዋልና፥


የይሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።


እንዲህም በል፦ በዳዊት ዙፋን የምትቀመጥ የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፥ አንተና ባሪያዎችህ በእነዚህም በሮች የሚገባ ሕዝብህ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።


እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ ቃሌን ትነግራቸዋለህ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌሃለሁ፥ ስለዚህ የአፌን ቃል ስማ ከእኔም ዘንድ አስጠንቅቃቸው።


ካህናት ሆይ፥ ይህን ስሙ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ አድምጡ፥ የንጉሥ ቤት ሆይ፥ ልብ አድርጉ፥ በምጽጳ ላይ ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።


በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ፥ ድሆችንም የምትበድሉ፥ ችጋረኞችንም የምታሰጨንቁ፥ ጌቶቻቸውንም፦ አምጡ እንጠጣ የምትሉ እናንተ የባሳን ላሞች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ።


እንዲህም አልሁ፦ የያዕቆብ አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዦች ሆይ፥ እባካችሁ ስሙኝ፥ ፍርድን ታውቁ ዘንድ አይገባችሁምን?


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።


跟着我们:

广告


广告