Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 17:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 አቤቱ፥ የእስራኤል ተስፋ ሆይ፥ የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ፥ ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ውኃ ምንጭ እግዚአብሔርን ትተዋልና በምድር ላይ ይጻፋሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የእስራኤል ተስፋ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጥለውህ የሚሄዱ ሁሉ ያፍራሉ፤ ፊታቸውን ከአንተ የሚመልሱ በምድር ውስጥ ይጻፋሉ፤ የሕይወትን ውሃ ምንጭ፣ እግዚአብሔርን ትተዋልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የእስራኤል ተስፋ አቤቱ! የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ፤ ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ውኃ ምንጭ ጌታን ትተዋልና በምድር ላይ ይጻፋሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የእስራኤል ተስፋ ነህ፤ አንተን የሚተዉ ሁሉ ያፍራሉ፤ የሕይወት ውሃ ምንጭ የሆንከውን አንተን እግዚአብሔርን ስለ ተዉ በትቢያ ላይ እንደ ተጻፈ ስም ይደመሰሳሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አቤቱ! የእ​ስ​ራ​ኤል ተስፋ ሆይ! የሚ​ተ​ዉህ ሁሉ ያፍ​ራሉ፤ ከአ​ን​ተም የሚ​ለዩ የሕ​ይ​ወ​ትን ውኃ ምንጭ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተ​ዋ​ልና በም​ድር ላይ ይጻ​ፋሉ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 17:13
40 交叉引用  

በደለኞችና ኃጢአተኞች ግን በአንድነት ይሰበራሉ፥ እግዚአብሔርንም የሚተዉ ይጠፋሉ።


በቃሉ የምትንቀጠቀጡ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ የጠሉአችሁ ስለ ስሜም ያባረሩአችሁ ወንድሞቻችሁ፦ ደስታችሁን እናይ ዘንድ እግዚአብሔር ይክበር ብለዋል፥ ነገር ግን ያፍራሉ።


አንተ የእስራኤል ተስፋ ሆይ በመከራም ጊዜ የምታድነው፥ በምድር እንደ እንግዳ፥ ወደ ማደሪያ ዘወር እንደሚል መንገደኛ ስለ ምን ትሆናለህ?


ለማስፈራራት አትሁንብኝ፥ በመከራ ቀን አንተ መጠጊያዬ ነህ።


አሳዳጆቼ ይፈሩ፥ እኔ ግን አልፈር፥ እነርሱ ይደንግጡ፥ እኔ ግን አልደንግጥ፥ ክፉንም ቀን አምጣባቸው፥ በሁለት እጥፍ ጥፋት አጥፋቸው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው።


ትተውኛልና፥ ይህንም ስፍራ እንግዳ አድርገውታልና፥ እነርሱና አባቶቻቸውም ለማያውቋቸው ለሌሎች አማልክት ዐጥነዋልና የይሁዳም ነገሥታት ይህን ስፍራ በንጹህ ደም ሞልተዋልና፥


ሕዝቤ ሁለቱን ክፉ ነገሮች አድርገዋልና፥ እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል፥ የተቀደዱትንም ጕድጓዶች፥ ውኃውን ይይዙ ዘንድ የማይችሉትን ጕድጓዶች፥ ለራሳቸው ቆፍረዋል።


ይህ ሁሉ የሆነብሽ እኔን ስለ ተውሽ አይደለምን? ይላል እግዚአብሔር አምላክሽ።


ያገኙአቸው ሁሉ በሉአቸው፥ ጠላቶቻቸውም፦ በጽድቅ ማደሪያ በእግዚአብሔር ላይ፥ በአባቶቻቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ስለ ሠሩ እኛ አልበደልንም አሉ።


እጄም ከንቱ ራእይን በሚያዩ፥ በውሸትም በሚያምዋርቱ ነቢያት ላይ ትሆናለች፥ እነርሱም በሕዝቤ ማኅበር ውስጥ አይገኙም፥ በእስራኤልም ቤት መጽሐፍ አይጻፉም፥ ወደ እስራኤልም ምድር አይገቡም፥ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።


ይህን የሠራሁ ስለ እናንተ እንዳይደለ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለ መንገዳችሁ እፈሩና ተዋረዱ።


በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ፥ እኵሌቶቹ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ እኵሌቶቹም ወደ እፍረትና ወደ ዘላለም ጕስቍልና።


እግዚአብሔርም በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል፥ ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፥ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ መሸሸጊያ፥ ለእስራኤልም ልጆች መጠጊያ ይሆናል።


በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።


እናንተ በተስፋ የምትኖሩ እስሮች ሆይ፥ ወደ ጽኑ አምባ ተመለሱ፥ ሁለት እጥፍ አድርጌ እንድመልስልሽ ዛሬ እነግርሻለሁ።


ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ሰለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።


ኢየሱስ መልሶ፦ የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ወኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት።


እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት።


ስለዚህም ምክንያት አያችሁና እነግራችሁ ዘንድ ጠራኋችሁ፤ ስለ እስራኤል ተስፋ ይህን ሰንሰለት ለብሻለሁና።”


መድኃኒታችን እግዚአብሔር ተስፋችንም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳዘዘው ትእዛዝ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥


በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ።


አለኝም፦ ተፈጽሞአል። አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ።


በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውኃ ወንዝ አሳየኝ።


መንፈሱና ሙሽራይቱም፦ ና ይላሉ። የሚሰማም፦ ና ይበል። የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።


በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፥ ወደ ሕይወትም ውኃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል።


跟着我们:

广告


广告