Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 16:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ታላላቆችና ታናናሾች በዚህች ምድር ይሞታሉ፥ አይቀበሩም ሰዎችም አያለቅሱላቸውም ስለ እነርሱም ገላን አይነጩላቸውም ራስንም አይላጩላቸውም፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ታላላቆችና ታናናሾች በዚህች ምድር ይሞታሉ፤ አይቀበሩም፤ አይለቀስላቸውም፤ ሰውነቱን የሚቧጥጥላቸው፣ ጠጕሩንም የሚላጭላቸው አይገኝም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ታላላቆችና ታናናሾች በዚህች ምድር ይሞታሉ፤ አይቀበሩም፥ ሰዎችም አያለቅሱላቸውም፥ ስለ እነርሱም ማንም ገላውን አይነጭም ራሱንም አይላጭም፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በዚህች ምድር የሚገኙ ሀብታሞችም ድኾችም ሁሉ ይሞታሉ፤ አልቅሶ የሚቀብራቸውም አያገኙም፤ ስለ እነርሱ ሐዘኑን ለመግለጥ ፊቱን የሚነጭም ሆነ ጠጒሩን የሚላጭ አይኖርም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ታላ​ላ​ቆ​ችና ታና​ና​ሾች በዚች ምድር ይሞ​ታሉ ፥ አይ​ቀ​በ​ሩም ሰዎ​ችም አያ​ለ​ቅ​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ ስለ እነ​ር​ሱም ፊት አይ​ነ​ጩ​ላ​ቸ​ውም፤ ራስ​ንም አይ​ላ​ጩ​ላ​ቸ​ውም፤

参见章节 复制




ኤርምያስ 16:6
20 交叉引用  

ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጕልማሶቻቸውን በቤተመቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጕልማሳውንና ቈንጆይቱን ሽማግሌውንና አሮጌውን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።


በዚያም ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደ ልቅሶና ወደ ዋይታ ራስን ወደ መንጨትና ማቅንም ወደ መልበስ ጠራ።


እንደ ሕዝቡም እንዲሁ ካህኑ፥ እንደ ባሪያውም እንዲሁ ጌታው፥ እንደ ባሪያይቱም እንዲሁ እመቤትዋ፥ እንደሚገዛም እንዲሁ የሚሸጠው፥ እንደ አበዳሪውም እንዲሁ ተበዳሪው፥ እንደ ዕዳ አስከፋዩም እንዲሁ ዕዳ ከፋዩ ይሆናል።


አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ፥ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡትን ነገሥታት ካህናቱንም ነቢያቱንም በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን ሁሉ በስካር እሞላቸዋለሁ።


በክፉ ሞት ይሞታሉ፥ አይለቀስላቸውም አይቀበሩምም፥ በመሬትም ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ፥ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፥ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናሉ።


ጢማቸውን ላጭተው ልብሳቸውንም ቀድደው ገላቸውንም ነጭተው፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ያቀርቡ ዘንድ የእህል ቍርባንና ዕጣን በእጃቸው እየያዙ፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ ከሰማርያም መጡ።


ቡሀነት በጋዛ ላይ መጥቶአል፥ አስቀሎና ጠፋች፥ የዔናቅ ቅሬታዎች ሆይ! እስከ መቼ ድረስ ገላችሁን ትነጫላችሁ?


ራስ ሁሉ መላጣ ጢምም ሁሉ የተላጨ ነውና፥ በእጅም ሁሉ ላይ ክትፋት በወገብም ላይ ማቅ አለና።


እግዚአብሔር የቍጣውን ትውልድ ጥሎአልና፥ ትቶታልምና ጠጕርሽን ቍረጪ፥ ጣዪውም፥ በወናዎች ኮረብቶችም ላይ አሙሺ።


በወደዱአቸውና ባመለኩአቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጉአቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል፥ አያከማቹአቸውም አይቀብሩአቸውምም፥ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ።


የራስ ጠጕራችሁንም ዙሪያውን አትከርክሙት፥ ጢማችሁንም ዙሪያውን አትቍረጡት።


ስለ ሞተውም ሥጋችሁን አትንጩ፥ ገላችሁንም አትንቀሱት፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


እነሆም፥ እግዚአብሔር ያዝዛል፥ ታላቁንም ቤት በማፍረስ፥ ታናሹንም ቤት በመሰባበር ይመታል።


ኢየሱስም ወደ መኵኦንኑ ቤት በደረሰ ጊዜ፥ እምቢልተኞችንና የሚንጫጫውን ሕዝብ አይቶ፦


እናንተ የአምላካችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፥ በምድርም ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ እግዚአብሔር አንተን መርጦአልና ስለ ሞተው ሰው አካላችሁን አትንጩ፥ በዓይኖቻችሁም መካከል ራሳችሁን አትላጩ።


ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፥ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።


የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ፥


跟着我们:

广告


广告