Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 16:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ስለዚህ፥ እነሆ፥ አስታውቃቸዋለሁ፥ በዚህች ጊዜ እጄንና ኃይሌን አስታውቃቸዋለሁ፥ እነርሱም ስሜ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ያውቃሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “ስለዚህ አስተምራቸዋለሁ፤ ኀይሌንና ታላቅነቴን፣ አሁን አስተምራቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜ እግዚአብሔር፣ እንደ ሆነ ያውቃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 “ስለዚህ፥ እነሆ፥ አስታውቃቸዋለሁ፥ በዚህች ጊዜ እጄንና ኃይሌን አስታውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜ ጌታ እንደሆነ ያውቃሉ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “ስለዚህ ሕዝቦች በሙሉ ኀይሌንና ታላቅነቴን በማያዳግም ሁኔታ እንዲያውቁት አደርጋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር መሆኔንም ያረጋግጣሉ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 “ስለ​ዚህ እነሆ በዚህ ወራት አስ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እጄ​ንና ኀይ​ሌ​ንም አሳ​ያ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ስሜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ ያው​ቃሉ።”

参见章节 复制




ኤርምያስ 16:21
13 交叉引用  

እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ፤ እርሱም ያባርራቸዋል፤ በፈርዖንና በሠራዊቱም ሁሉ ላይ ክብር አገኛለሁ፤ ግብፃውያንም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።” እነርሱም እንዲሁ አደረጉ።


እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው፤


ለአብርሃምም ለይስሐቅም ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ፤ ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር አልታወቀላቸውም ነበር።


እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ፥ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።


ስሙ እግዚአብሔር የሆነ፥ ያደረገው እግዚአብሔር፥ ያጸናውም ዘንድ የሠራው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦


ሕዝቅኤልም ምልክት ይሆናችኋል፥ እርሱ እንዳደረገ ሁሉ እናንተ ታደርጋላችሁ፥ ይህም በመጣ ጊዜ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።


በዚያ ቀን አፍህ ላመለጠው ይከፈታል፥ አንተም ትናገራለህ ከዚያ ወዲያም ዲዳ አትሆንም፥ ምልክትም ትሆናቸዋለህ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።


በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምያስን እበቀላለሁ፥ እንደ ቍጣዬና እንደ መዓቴም መጠን በኤዶምያስ ያደርጋሉ፥ በቀሌንም ያውቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ተወግተውም የሞቱት በመካከላችሁ ይወድቃሉ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።


ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮበብ የፈጠረውን፥ የሞትን ጥላ ወደ ንጋት የሚለውጠውን፥ ቀኑንም በሌሊት የሚያጨልመውን፥ የባሕሩንም ውኆች ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሳቸውን፥


跟着我们:

广告


广告