Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 15:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ኢየሩሳሌም ሆይ፥ የሚራራልሽ ማን ነው? የሚያዝንልሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅንነትሽ ይጠይቅ ዘንድ ፈቀቅ የሚል ማነ ነው?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ኢየሩሳሌም ሆይ፤ የሚራራልሽ ማን ነው? ማንስ ያለቅስልሻል? ደኅንነትሽንስ ማን ጐራ ብሎ ይጠይቃል?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “ኢየሩሳሌም ሆይ! የሚራራልሽ ማን ነው? የሚያዝንልሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅንነትሽ ቆም ብሎ የሚጠይቅ ማነ ነው?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ማን ይራራላችኋል? የሚያዝንላችሁስ ማን ነው? ለአንድ አፍታ ቆም ብሎ ስለ ሁኔታችሁስ የሚጠይቅ ማን ነው?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! የሚ​ራ​ራ​ልሽ ማን ነው? የሚ​ያ​ዝ​ን​ል​ሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅ​ን​ነ​ትሽ ይጠ​ይቅ ዘንድ ፈቀቅ የሚል ማን ነው?

参见章节 复制




ኤርምያስ 15:5
15 交叉引用  

እናንተ ወዳጆቼ ሆይ፥ ማሩኝ፥ የእግዚአብሔር እጅ መትታኛለችና ማሩኝ።


ሙሴም አማቱን ሊገናኝ ወጣ፥ ሰገደም፥ ሳመውም፤ እርስ በርሳቸውም ደኅንነታቸውን ተጠያየቁ፥ ወደ ድንኳኑም ገቡ።


እነዚህ ሁለት ነገሮች ሆነውብሻል፥ ማንስ ያስተዛዝንሻል? መፈታትና ጥፋት ራብና ሰይፍ ናቸው፥ እንዴትስ አድርጌ አጽናናሻለሁ?


ሰውንም በሰው ላይ፥ አባቶችንና ልጆችን በአንድ ላይ፥ እቀጠቅጣቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ አጠፋቸዋለሁ እንጂ አልራራም፥ አላዝንም፥ አልምርም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰላሜን፥ ቸርነትና ምሕረትን፥ ከዚህ ሕዝብ አስወግጄአለሁና ልቅሶ ወዳለበት ቤት አትግባ፥ ታለቅስም ታዝንም ዘንድ አትሂድ።


ከዚህ በኋላ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ከቸነፈርና ከሰይፍ ከራብም በዚህች ከተማ የቀሩትንም ባሪዎቹንና ሕዝቡን በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውንም በሚሹት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፥ እርሱም በሰይፍ ስለት ይመታቸዋል፥ አያዝንላቸውም፥ አይራራላቸውም፥ አይምራቸውም።


ፌ። ጽዮን እጅዋን ዘረጋች የሚያጽናናት የለም፥ እግዚአብሔር በያዕቆብ ዙሪያ ያሉትን እንዲያስጨንቁት አዘዘ፥ ኢየሩሳሌም በመካከላቸው እንደ ርኩስ ነገር ሆናለች።


ከመንገዱም ፈቀቅ ብለው ጕልማሳው ሌዋዊ ወደ ነበረበት ወደ ሚካ ቤት መጡ፥ ደኅንነቱንም ጠየቁት።


ሰላምታም ይሰጡሃል፥ ሁለትም ዳቦ ይሰጡሃል፥ ከእጃቸውም ትቀበላለህ።


ዳዊትም ዕቃውን በዕቃ ጠባቂው እጅ አኖረው፥ ወደ ሠራዊቱም ሮጠ፥ የወንድሞቹንም ደኅንነት ጠየቀ።


ዳዊትም አሥር ጕልማሶች ላከ ለጕልማሶችም አለ፦ ወደ ቀርሜሎስ ወጥታችሁ ወደ ናባል ሂዱ፥ በስሜም ስለ ሰላም ጠይቁት፥ እንዲህም በሉት፦


跟着我们:

广告


广告