Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 15:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ፥ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ቃልህ በተገኘ ጊዜ በላሁት፤ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በስምህ ተጠርቻለሁና፣ ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነልኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ቃላትህ ተገኝተዋል እኔም በልቼአቸዋለሁ፤ አቤቱ! የሠራዊት አምላክ ጌታ ሆይ! በስምህ ተጠርቻለሁና ቃላትህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆኑኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! እኔ በስምህ ተጠርቼአለሁ፤ ቃልህ ወደ እኔ በመጣ ጊዜ በሙሉ ተቀብዬዋለሁ፤ ልቤንም በደስታና በሐሴት ሞላው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ቃልህ ተገ​ኝ​ቶ​አል፤ እኔም በል​ች​ዋ​ለሁ፤ አቤቱ! የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ ሆይ! ቃል​ህን የከዱ ሰዎ​ችን አጥ​ፋ​ቸው፤ ስምህ በእኔ ላይ ተጠ​ር​ት​ዋ​ልና፥ ቃልህ ሐሤ​ትና የልብ ደስታ ሆነኝ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 15:16
13 交叉引用  

ሕዝቡም ሁሉ የተነገረላቸውን ቃል አስተውለዋልና ሊበሉና ሊጠጡ እድል ፈንታም ሊሰድዱ ደስታም ሊያደርጉ ሄዱ።


ከከንፈሩ ትእዛዝ አልተመለስሁም፥ የአፉን ቃል በልቤ ሰውሬአለሁ።


እንዳንቀላፋ ሰው ሰው፥ ያድንም ዘንድ እንደማይችል ኃያል ስለ ምን ትሆናለህ? አንተ ግን፥ አቤቱ፥ በመካከላችን ነህ እኛም በስምህ ተጠርተናል፥ አትተወን።


አንተ ግን፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የምነግርህን ስማ እንደዚያ እንደ ዓመፀኛው ቤት ዓመፀኛ አትሁን፥ አፍህን ክፈት የምሰጥህንም ብላ።


የያዕቆብ ቤት የተባልህ ሆይ፥ በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? ወይስ ሥራው እንደዚያች ናትን? ቃሌስ በቅን ለሚሄድ በጎነት አያደርግምን?


跟着我们:

广告


广告