Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 14:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አቤቱ፥ ኃጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኃጢአት ሠርተናልና ኃጢአታችን ይመሰክርብናል ነገር ግን ስለ ስምህ ብለህ አድርግ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከአንተ መኰብለል አብዝተናል፤ በአንተም ላይ ዐምፀናል፤ ኀጢአታችን ቢመሰክርብንም እንኳ፣ ስለ ስምህ ብለህ አንድ ነገር አድርግልን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 “ኃጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኃጢአትን ሠርተናል፤ ምንም እንኳ ኃጢአታችን ቢመሰክርብንም ስለ ስምህ ብለህ አቤቱ! አድርግ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ሕዝቤም ወደ እኔ እንዲህ በማለት ይጮኻሉ፤ ‘ምንም እንኳ የበደላችን ብዛት በእኛ ላይ ቢመሰክርም፥ እግዚአብሔር ሆይ! በተስፋ ቃልህ መሠረት እርዳን፤ ከአንተ ርቀናል፤ አንተንም አሳዝነናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አቤቱ! ኀጢ​አ​ታ​ችን ብዙ ነውና፥ በአ​ን​ተም ላይ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ና​ልና ኀጢ​አ​ታ​ችን ተቃ​ው​ሞ​ናል፤ ነገር ግን ስለ ስምህ ብለህ አድ​ርግ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 14:7
30 交叉引用  

አቤቱ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው እኛ አምልጠን ቀርተናል፤ እነሆ በፊትህ በበደላችን አለን፤ ስለዚህ በፊትህ ሊቆም የሚችል የለም።”


ስለ እኔ፥ ስለ ራሴ አደርገዋለሁ ስሜ ተነቅፎአልና፥ ክብሬን ለሌላ አልሰጥም።


ዓመፃችን በአንተ ፊት በዝቶአልና፥ ኃጢአታችን መስክሮብናልና፥ ዓመፃችን ከእኛ ጋር ነውና፥ በደላችንን እናውቃለንና።


ስለ ስብራቴ ወዮልኝ! ቍስሌም ክፉ ነው፥ እኔ ግን፦ በእውነት የመከራ ቍስሌ ነው እርሱንም መሸከም ይገባኛል አልሁ።


ክፋትሽ ይገሥጽሻል ክዳትሽም ይዘልፍሻል፥ አምላክሽንም እግዚአብሔርን የተውሽ እኔንም መፍራት የሌለብሽ ክፉና መራራ ነገር እንደ ሆነ እወቂ፥ ተመልከቺ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርተናልና፥ የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማንምና በእፍረታችን እንጋደም፥ ውርደታችንም ይክደነን።


እግዚአብሔርም በንጉሡ በኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ፦ ከዳተኛይቱ እስራኤል ያደረገችውን አየህን? ወደ ረዘመው ተራራ ሁሉ ከለመለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች በዚያም ጋለሞተች።


በደላችሁ እነዚህን አስቀርታለች፥ ኃጢአታችሁም መልካምን ነገር ከለከለቻችሁ።


ስለዚህ ኃጢአታቸው በዝቶአልና፥ የክዳታቸውም ብዛት ጸንቶአልና ስለዚህ አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፥ የበረሀም ተኵላ ያጠፋቸዋል፥ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ይተጋል፥ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል።


ዝም ብለን ለምን እንቀመጣለን? እግዚአብሔርን ስለ በደልን አምላካችን እግዚአብሔር አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም ውኃ አጠጥቶናልና ተሰብስባችሁ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንግባ በዚያም እንጥፋ።።


እንግዲህ ይህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዘወትር ስለ ምን ወደ ኋላው ይመለሳል? ተንኰልን ይዞአል ሊመለስም እንቢ ብሎአል።


ነገር ግን በፊታቸው ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


ነገር ግን እጄን መለስሁ፥ በፊታቸውም ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


ነገር ግን በመካከላቸው ባሉ ከግብጽም ምድር አወጣቸው ዘንድ በፊታቸው በተገለጥሁላቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


የእስራኤልም ትዕቢት በፊቱ ይመሰክራል፥ ስለዚህ እስራኤልና ኤፍሬም በኃጢአታቸው ይሰናከላሉ፥ ይሁዳም ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይሰናከላል።


የእስራኤልም ትዕቢት በፊቱ መሰከረ፥ ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ግን አልተመለሱም፥ በዚህም ሁሉ አልፈለጉትም።


የምድሩንም ሣር በልተው ከጨረሱ በኋላ፥ እኔ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፥ ያዕቆብ ታናሽ ነውና እንዴት ይቆማል? አልሁ።


በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን ለእኔ እስኪያደርግ ድረስ ቍጣውን እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቅንም አያለሁ።


ይኸውም፥ በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው።


በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ።


ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፦ 2 እጃችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ 2 እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አላደረገም 2 እንዳይሉ፥ 2 ስለ ጠላቱ ቁጣ ፈራሁ።


ከነዓናውያንም በምድሪቱ የሚኖሩ ሁሉ ሰምተው ይከብቡናል፥ ስማችንንም ከምድር ያጠፋሉ፥ ለታላቁ ስምህም የምታደርገው ምንድር ነው?


跟着我们:

广告


广告