Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 14:18 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ፥ በሰይፍ የሞቱ አሉ፥ ወደ ከተማም ብገባ፥ እነሆ፥ በራብ የከሱ አሉ፥ ነቢዩና ካህኑም ወደማያውቋት አገር ሄደዋልና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ወደ ገጠር ብወጣ፣ በሰይፍ የተገደሉትን አያለሁ፤ ወደ ከተማ ብገባ፣ በራብ የወደቁትን አያለሁ ነቢዩም ካህኑም፣ ወደማያውቁት አገር ሸሽተዋል።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ፥ በሰይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተማም ብገባ፥ እነሆ፥ በራብ ደዌ የከሱ አሉ፤ ነቢዩና ካህኑም ወደማያውቁት አገር ሄደዋልና።’”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ወደየመስኩ ብወጣ በጦርነት የተገደሉ ሰዎችን ሬሳ አያለሁ፤ ወደ ከተማም ብገባ በራብ ለመሞት የሚያጣጥሩ ሰዎችን አያለሁ፤ ነቢያትና ካህናት የራሳቸውን ጉዳይ ይከታተላሉ፤ ነገር ግን የሚያደርጉትን አያውቁም።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ በሰ​ይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተ​ማም ብገባ፥ እነሆ በራብ የከሱ አሉ፤ ነቢ​ዩና ካህኑ ወደ​ማ​ያ​ው​ቋት ሀገር ሄደ​ዋ​ልና።”

参见章节 复制




ኤርምያስ 14:18
19 交叉引用  

ጩኸትና ፍጅት የተሞላብሽ ከተማ፥ ደስታ ያለሽ ከተማ ሆይ፥ በአንቺ ውስጥ የተገደሉት በሰይፍ የተገደሉ አይደሉም፥ በሰልፍም የሞቱ አይደሉም።


እነዚህ ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፥ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይፋንናሉ፥ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፥ በወይን ጠጅም ይዋጣሉ፥ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይፋንናሉ፥ በራእይ ይስታሉ፥ በፍርድም ይሰናከላሉ።


ካህናቱም፦ እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፥ ባለ ኦሪቶችም አላወቁኝም፥ ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥ ነቢያትም በበኣል ትንቢት ተናገሩ፥ የማይረባንም ነገር ተከተሉ።


እኔ ሳልልካቸው እነዚህ ነቢያት ሮጡ፥ እኔም ሳልነግራቸው ትንቢትን ተናገሩ።


ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፥ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?


ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና።


የጠላት ሰይፍና ድንጋጤ ከብበዋችኋልና ወደ ሜዳ አትውጡ በመንገድም ላይ አትሂዱ።


ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ።


ሬስ። አቤቱ፥ ተጨንቄአለሁና፥ አንጀቴም ታውኮብኛልና ተመልከት፥ ዓመፃን ፈጽሞ አድርጌአለሁና ልቤ በውስጤ ተገላበጠብኝ፥ በሜዳ ሰይፍ ልጆቼን አጠፋ በቤትም ሞት አለ።


ቆፍ። ተነሺ፥ በሌሊት በመጀመሪያ ክፍል ጩኺ፥ በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፥ በጐዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።


ጤት። በሰይፍ የሞቱ በራብ ከሞቱት ይሻላሉ፥ እነዚህ የምድርን ፍሬ አጥተው ተወግተውም ቀጥነዋል።


ሰይፍ በውጭ ቸነፈርና ራብ በውስጥ አለ፥ በሜዳ ያለው በሰይፍ ይሞታል፥ በከተማም ያለውን ቸነፈርና ራብ ይፈጁታል።


በከተማችሁ ሁሉ ጥርስን ማጥራት፥ በስፍራችሁም ሁሉ እንጀራን ማጣት ሰጠኋችሁ፥ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።


አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።


እግዚአብሔርም አንተን በአንተም ላይ የምታነግሠውን ንጉሥ አንተና አባቶችህ ወዳላወቃችኋቸው ሕዝብ ይወስድሃል፤ በዚያም ሌሎችን የእንጨትና የድንጋይ አማልክት ታመልካለህ።


እግዚአብሔርም ከምድር ዳር እስከ ዳርቻዋ ድረስ ወዳሉ አሕዛብ ሁሉ ይበትንሃል፤ በዚያም አንተና አባቶችህ ያላወቃችኋቸውን ሌሎችን አማልክት፥ እንጨትንና ድንጋይን፥ ታመልካለህ።


ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም ጥፋታቸውም አያንቀላፋም።


跟着我们:

广告


广告