Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 13:27 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 አስጸያፊ ሥራሽን፥ ምንዝርናሽን፥ ማሽካካትሽን፥ የግልሙትናሽንም መዳራት በኮረብቶች ላይ በሜዳም አይቻለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ወዮልሽ! ለመንጻት እንቢ ብለሻል፥ ይህስ እስከ መቼ ነው?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 በኰረብቶችና በሜዳዎች ላይ፣ አስጸያፊ ተግባርሽን፣ ምንዝርናሽንና ማሽካካትሽን፣ ኀፍረተ ቢስ ግልሙትናሽን አይቻለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ወዮልሽ! ከርኩሰትሽ የማትጸጂው እስከ መቼ ነው?”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 አስጸያፊ ሥራሽን፥ ምንዝርናሽን፥ ማሽካካትሽን፥ የአመንዝራነትሽንም መዳራት በኮረብቶች ላይ፥ በሜዳም አይቻለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ወዮልሽ! ለመንጻት እንቢ ብለሻል፤ ይህስ እስከ መቼ ነው?”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እርሱ የሚጠላውን ነገር ስታደርጉ አይቶአችኋል፤ ከባልንጀራው ሚስት ጋር ለማመንዘር እንደሚጐመጅ ሰውና ባዝራ እንደሚፈልግ ሰንጋ ፈረስ፥ እናንተም የአሕዛብ አማልክትን ተከትላችሁ በየኰረብታው ራስና በየሜዳው ስትኳትኑ አይቶአችኋል። የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ፥ ወዮላችሁ፥ ከቶ ንጹሕ መሆን የምትችሉት መቼ ይሆን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 አስ​ጸ​ያፊ ሥራ​ሽን፥ ምን​ዝ​ር​ና​ሽን፥ ማሽ​ካ​ካ​ት​ሽን፥ የዝ​ሙ​ት​ሽ​ንም መዳ​ራት በኮ​ረ​ብ​ቶች ላይ፥ በሜ​ዳም ላይ አይ​ቻ​ለሁ። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! ወዮ​ልሽ! ለመ​ን​ጻት እንቢ ብለ​ሻል፤ ይህስ እስከ መቼ ነው?

参见章节 复制




ኤርምያስ 13:27
32 交叉引用  

ከፍ ባለውም በረዘመውም ተራራ ላይ መኝታሽን አደረግሽ፥ መሥዋዕትንም ትሠዊ ዘንድ ወደዚያ ወጣሽ።


በተራሮችም ላይ ስላጠኑ፥ በኮረብቶችም ላይ ስለ ሰደቡኝ፥ ስለዚህ አስቀድመው የሠሩትን ሥራቸውን በብብታቸው እሰፍራለሁ።


ወዳጄ በቤቴ ውስጥ ምን አላት? ስእለት ወይም የተቀደሰ ሥጋ ክፋትሽን ከአንቺ ያስወግዳልን? ወይስ በእነዚህ ታመልጫለሽን?


እግዚአብሔርም በንጉሡ በኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ፦ ከዳተኛይቱ እስራኤል ያደረገችውን አየህን? ወደ ረዘመው ተራራ ሁሉ ከለመለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች በዚያም ጋለሞተች።


ወዮ! ወዮልሽ! ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥


በፊቴም ዘረጋው፥ በውስጥና በውጭም ተጽፎበት ነበር፥ ልቅሶና ኃዘን ዋይታም ተጽፎበት ነበር።


እሰጣቸውም ዘንድ ወደ ማልሁላቸው ምድር ባገባኋቸው ጊዜ፥ ከፍ ያለውን ኮረብታ ሁሉ ቅጠልማውንም ዛፍ ሁሉ አዩ፥ በዚያም መሥዋዕታቸውን ሠዉ በዚያም የሚያስቈጣኝን ቍርባናቸውን አቀረቡ በዚያም ደግሞ ጣፋጩን ሽታቸውን አደረጉ በዚያም የመጠጥ ቍርባናቸውን አፈሰሱ።


በከንቱ ደከመች፥ ሆኖም ዝገትዋ በእሳት ስንኳ አልለቀቀም።


በርኵሰትሽ ሴሰኝነት አለ፥ አነጻሁሽ አልነጻሽምና መዓቴን በላይሽ እስክጨርስ ድረስ እንግዲህ ከርኵሰትሽ አትነጺም።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዝገትዋ ላለባት ዝገትዋም ከእርስዋ ላልወጣ ምንቸት፥ ለደም ከተማ ወዮላት! ቍራጭ ቍራጩን አውጣ፥ ዕጣ አልወደቀባትም።


ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ፥ ከርኵሰታችሁም ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለዚህ ደግሞ አደግላቸው ዘንድ የእስራኤል ቤት ይሹኛል ሰውንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ።


ተወግተውም የሞቱ ሰዎቻቸው በጣዖቶቻቸው መካከልና በመሠዊያዎቻቸው ዙሪያ፥ ለጣዖቶቻቸው ጣፋጭ ሽታ ባቀረቡበት ስፍራ፥ ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ በተራሮችም ራስ ሁሉ ላይ፥ ከለመለመውም ዛፍ ሁሉ በታች ቅጠሉም ከበዛ ከአድባር ዛፍ ሁሉ በታች በሆኑ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።


እግዚአብሔር መጀመሪያ በሆሴዕ በተናገረ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ሆሴዕን፦ ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ርቃ ታላቅ ግልሙትና ታደርጋለችና ሂድ፥ ጋለሞታን ሴትና የግልሙትናን ልጆች ለአንተ ውሰድ አለው።


እርግማንና ሐሰት ግዳይና ስርቆት ምንዝርናም ወጥተዋል፥ ደምም ወደ ደም ደርሶአል።


ሰማርያ ሆይ፥ እምቦሳህን፥ ጥሎአል፥ ቍጣዬ በላያቸው ነድዶአል፥ እስከ መቼ ድረስ ንጹሕ ሊሆኑ አይችሉም?


ለዓመፀኛይቱና ለረከሰች ለአስጨናቂይቱም ከተማ ወዮላት!


ወዮልሽ ኮራዚ፤ ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ፤ በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው አመድም ነስንሰው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበርና።


እንደ ገና ስመጣ በእናንተ ዘንድ አምላኬ እንዲያዋርደኝ፥ አስቀድመውም ኃጢአት ከሠሩትና ስላደረጉት ርኵሰትና ዝሙት መዳራትም ንስሐ ካልገቡት ወገን ስለ ብዙዎች ምናልባት አዝናለሁ ብዬ እፈራለሁ።


እንግዲህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ።


አመንዝሮች ሆይ፥ ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።


አየሁም፥ አንድም ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ፦ ሊነፉ ያላቸው የሦስቱ መላእክት መለከት ስለሚቀረው ድምፅ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው፥ ወዮላቸው፥ ወዮላቸው ሲል ሰማሁ።


跟着我们:

广告


广告