Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 12:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ቤቴን ትቼአለሁ ርስቴንም ጥያለሁ፥ ነፍሴም የምትወድዳትን በጠላቶችዋ እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ቤቴን እተዋለሁ፤ ርስቴን እጥላለሁ፤ የምወድዳትን እርሷን፣ አሳልፌ በጠላቶቿ እጅ እሰጣታለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 “ቤቴን ትቼአለሁ ርስቴንም ጥያለሁ፥ ነፍሴም የምትወድዳትን በጠላቶችዋ እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ቤቴንና ርስቴን ትቼአለሁ፤ የምወዳቸውን ሕዝቤንም ለጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ቤቴን ትች​አ​ለሁ፤ ርስ​ቴ​ንም ጥያ​ለሁ፤ ነፍሴ የም​ት​ወ​ድ​ዳ​ት​ንም በጠ​ላ​ቶ​ችዋ እጅ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቻ​ለሁ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 12:7
23 交叉引用  

የርስቴንም ቅሬታ እጥላለሁ፤ በጠላቶቻቸውም እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ለጠላቶቻቸውም ሁሉ ምርኮና ብዝበዛ ይሆናሉ፤


ሕዝብህን የያዕቆብን ቤት ትተሃልና፥ ይኸውም የምሥራቅን ሰዎች አመል ስለ ተሞሉ፥ እንደ ፍልስጥኤማውያንም ምዋርተኞች ስለ ሆኑ፥ ከባዕድ ልጆችም ጋር ስለ ተባበሩ ነው።


ወዳጄ በቤቴ ውስጥ ምን አላት? ስእለት ወይም የተቀደሰ ሥጋ ክፋትሽን ከአንቺ ያስወግዳልን? ወይስ በእነዚህ ታመልጫለሽን?


በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ጠልታታለችን? ስለ ምን መታኸን? ፈውስስ ስለ ምን የለንም? ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፥ ፈውስን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ።


አንተም የሰጠሁህን ርስት ትለቅቃለህ ለዘላለምም በማታውቃትም ምድር ለጠላቶቻችሁ ባሪያ አደርግሃለሁ፥ ለዘላለም የሚነድደውን እሳት በቍጣዬ አንድዳችኋልና።


ነገር ግን ይህን ቃል ባትሰሙ፥ ይህ ቤት ወና እንዲሆን በራሴ ምያለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ይህ ሕዝብ ወይም ነቢይ ወይም ካህን፦ የእግዚአብሔር ሸክም ምንድር ነው? ብሎ ቢጠይቅህ፥ አንተ፦ ሸክሙ እናንተ ናችሁ፥ እጥላችሁማለህ፥ ይላል እግዚአብሔር ትላቸዋለህ።


የእግዚአብሔር ሸክም ብላችኋልና ስለዚህ፥ እነሆ፥ ፈጽሜ እረሳችኋለሁ እናንተንም ለእናንተና ለአባቶቻችሁም የሰጠኋትን ከተማ ከፊቴ እጥላለሁ።


ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ላይ በተሠራው በደል ምንም እንኳ የተሞላች ብትሆን፥ እስራኤልም ሆነ ይሁዳ በአምላኩ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ዘንድ አልተጣለም።


ስለዚህ በሴሎ እንዳደረግሁ እንዲሁ ስሜ በተጠራበት በምትታመኑበት ቤት ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ስፍራ አደርጋለሁ።


እግዚአብሔር የቍጣውን ትውልድ ጥሎአልና፥ ትቶታልምና ጠጕርሽን ቍረጪ፥ ጣዪውም፥ በወናዎች ኮረብቶችም ላይ አሙሺ።


ለእስራኤል ቤት ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የኃይላችሁን ትምክሕት፥ የዓይናችሁን አምሮት፥ የነፍሳችሁን ምኞት መቅደሴን አረክሳለሁ፥ ያስቀራችኋቸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።


እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት።


ክፋታቸው ሁሉ በጌልገላ አለ፥ በዚያ ጠልቻቸዋለሁ፥ ስለ ሠሩት ክፋት ከቤቴ አሳድዳቸዋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲያ አልወድዳቸውም፥ አለቆቻቸው ሁሉ ዓመፀኞች ናቸው።


በጽዮን መለከትን ንፉ፥ ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፥


አሕዛብን ሁሉ ሰብስቤ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፥ በዚያም ስለ ሕዝቤና ስለ ርስቴ ስለ እስራኤል በአሕዛብ መካከል የበተኑአቸውን ምድሬንም የተካፈሉአትን እፋረድባቸዋለሁ።


በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብ ሁሉም ይማረካሉ፤ የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።


ስለ ብንያምም እንዲህ አለ፦ 2 በእግዚአብሔር የተወደደ በእርሱ 2 ዘንድ ተማምኖ ይኖራል፤ 2 ቀኑን ሁሉ ይጋርደዋል፥ 2 በትከሻውም መካከል ያድራል።


跟着我们:

广告


广告