Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 12:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ስንዴን ዘሩ እሾህንም አጨዱ፥ ደከሙ፥ ምንም አልረባቸውም፥ ስለ እግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ከፍሬያችሁ ታፍራላችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስንዴን ይዘራሉ፤ እሾኽን ያጭዳሉ፤ ይደክማሉ፤ የሚያገኙት ግን የለም። ከእግዚአብሔርም ጽኑ ቍጣ የተነሣ፣ በመኸራችሁ ውጤት ታፍራላችሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ስንዴን ዘሩ እሾህንም አጨዱ፤ እራሳቸውን አደከሙ፥ ምንም አልረባቸውም፤ ስለ ጌታ ጽኑ ቁጣ በፍሬያችሁ ታፍራላችሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሕዝቤ ስንዴ ዘርተው እሾኽ ሰበሰቡ፤ በሥራ እጅግ ደክመው ምንም ትርፍ አላገኙም፤ ከብርቱ ቊጣዬ የተነሣ በምርታቸው መጥፋት አዘኑ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ስን​ዴን ትዘ​ራ​ላ​ችሁ፤ እሾ​ህ​ንም ታጭ​ዳ​ላ​ችሁ፤ ዕጣ​ች​ሁም ምንም አይ​ጠ​ቅ​ማ​ች​ሁም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ የተ​ነሣ በአ​ዝ​መ​ራ​ችሁ ታፍ​ራ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 12:13
19 交叉引用  

ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።


እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።


አየሁ፥ እነሆም፥ ፍሬያማ እርሻ ምድረ በዳ ሆነች፥ ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ከጽኑ ቍጣው የተነሣ ፈርሰው ነበር።


ሰውም ሁሉ ባልንጀራውን ያታልላል በእውነትም አይናገርም፥ ሐሰትን መናገርንም ምላሳቸው ተምሮአል፥ ክፉንም ለማድረግ ይደክማሉ።


ነፋስን ዘርተዋል፥ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፥ አገዳ የለውም፥ ከፍሬውም ዱቄት አይገኝም፥ ቢገኝም እንግዶች ይበሉታል።


እኔም እንዲህ አደርግባችኋለሁ፤ ፍርሃትን፥ ክሳትንም፥ ዓይናችሁንም የሚያፈዝዝ፥ ሰውነታችሁንም የሚያማስን ትኩሳት አወርድባችኋለሁ፤ ዘራችሁንም በከንቱ ትዘራላችሁ፥ ጠላቶቻችሁ ይበሉታልና።


ጕልበታችሁም በከንቱ ያልቃል፤ ምድራችሁም እህልዋን አትሰጥም፥ የምድርም ዛፎች ፍሬአቸውን አይሰጡም።


ትዘራለህ፥ ነገር ግን አታጭድም፥ ወይራውንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፥ ወይኑንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን የወይን ጠጁን አትጠጣም።


እነሆ፥ አሕዛብ ስለ እሳት እንዲሠሩ፥ ወገኖችም ስለ ከንቱነት እንዲደክሙ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ አይደለምን?


ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፥ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፥ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልረካችሁም፥ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፥ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ያደርገው ዘንድ ደመወዙን ተቀበለ።


እናንተ ብዙ ነገርን ተስፋ አደረጋችሁ፥ እነሆም፥ ጥቂት ሆነ፥ ወደ ቤትም ባገባችሁት ጊዜ እፍ አልሁበት። ይህ ስለ ምንድር ነው? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ሁሉ ወደ እየቤታችሁ እየሮጣችሁ የእኔ ቤት ፈርሶ ስለ ተቀመጠ ነው።


እንግዲህ ዛሬ ከምታፍሩበት ነገር ያን ጊዜ ምን ፍሬ ነበራችሁ? የዚህ ነገር መጨረሻው ሞት ነውና።


እጅግ ዘር ወደ እርሻ ታወጣለህ፤ አንበጣም ይበላዋልና ጥቂት ትሰበስባለህ።


跟着我们:

广告


广告