Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 12:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፥ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ብዙ እረኞች የወይን ቦታዬን ያጠፋሉ፤ ይዞታዬንም ይረግጣሉ፤ ደስ የምሰኝበትንም ማሳ፣ ጭር ያለ በረሓ ያደርጉታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ብዙ መሪዎች የወይን ተክል ቦታዬን አጥፍተዋል፤ የእርሻ ቦታዎቼንም ረጋግጠዋል፤ ደስ የምታሰኘውን ምድሬንም ወደ በረሓነት ለውጠዋታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ብዙ እረ​ኞች የወ​ይ​ኑን ቦታ​ዬን አጥ​ፍ​ተ​ዋል፤ እድል ፈን​ታ​ዬ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋል፤ የም​ወ​ድ​ዳ​ት​ንም እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድ​ር​ገ​ዋ​ታል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 12:10
21 交叉引用  

እግዚአብሔር ከሕዝቡ ሽማግሌዎችና ከአለቆቻቸው ጋር ይፋረዳል፥ የወይኑን ቦታ የጨረሳችሁ እናንተ ናችሁ፥ ከድሆች የበዘበዛችሁት በቤታችሁ አለ፥


ስለዚህ የመቅደሱን አለቆች አረከስሁ፥ ያዕቆብንም እርግማን፥ እስራኤልንም ስድብ አደረግሁ።


የተቀደሰው ሕዝብህ መቅደስህን ጥቂት ጊዜ ወረሱት፥ ጠላቶቻችንም ረግጠውታል።


የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር።


ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ የሰላም በረት ፈርሶአል።


እንደ አንበሳ መደቡን ለቅቆአል፥ ከአስጨናቂውም ሰይፍና ከጽኑ ቍጣው የተነሣ ምድራቸው ባድማ ሆናለችና።


ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ ባሪያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፥ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመደነቂያና ለማፍዋጫም ለዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


እኔ ግን፦ ከወንዶች ልጆች ጋር እንዴት አደርግሻለሁ? ያማረችውንስ ምድር የከበረችውን የአሕዛብን ሠራዊት ርስት እንዴት እሰጥሻለሁ? ብዬ ነበር። ደግሞ፦ አባቴ ብለሽ ትጠሪኛለሽ እኔንም ከመከተል አትመለሽም ብዬ ነበር።


የባቢሎንም ንጉሥ አለቆች ሁሉ፥ ኤርጌል ሳራስር፥ ሳምጋርናቦ፥ ሠርሰኪም፥ ራፌስ፥ ኤርጌል ሳራስር፥ ራብማግ፥ ከቀሩት ከባቢሎን ንጉሥ አለቆች ሁሉ ጋር ገብተው በመካከለኛው በር ውስጥ ተቀመጡ።


እረኞችና መንጐቻቸው ወደ እርስዋ ይመጣሉ፥ በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፥ እያንዳንዱም በስፍራው መንጋውን ያሰማራል።


ለተራሮች ልቅሶን ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም ዋይታን አነሣለሁ፥ ሰው እንዳያልፍባቸው በእሳት ተቃጥለዋልና። ሰዎችም የከብቱን ድምፅ አይሰሙም፥ ከሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፥ እረኞችንም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸውምን?


እረኛንም በማጣት ተበተኑ፥ ለምድርም አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ፥ ተበተኑም።


ከቅዱሳኑም አንዱ ሲናገር ሰማሁ፥ ለተናገረው ለቅዱሱም ሁለተኛው ቅዱስ፦ ስለ ዘወትሩ መሥዋዕት፥ መቅደሱና ሠራዊቱም ይረገጡ ዘንድ ስለሚሰጥና ስለሚያጠፋ ኃጢአት የሆነው ራእይ እስከ መቼ ይሆናል? አለው።


ወደ ማያውቁአቸውም አሕዛብ ሁሉ በዐውሎ ነፋስ በተንኋቸው። እንዲሁ ከእነርሱ በኋላ ምድሪቱ ባድማ ሆናለች፥ የሚተላለፍባትና የሚመላለስባትም አልነበረም፥ ያማረችውንም ምድር ባድማ አደረጉአት።


ሰለዚህ እንዴት እንድትመልሱ አስቀድማችሁ እንዳታስቡ በልባችሁ አኑሩት፤


በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።


跟着我们:

广告


广告