Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 11:12 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በይሁዳም ከተሞችና በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሄደው ወደሚያጥኑላቸው አማልክት ይጮኻሉ፥ ነገር ግን በመከራቸው ጊዜ ከቶ አያድኑአቸውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ወደሚያጥኑላቸው አማልክት ሄደው ይጮኻሉ፤ እነርሱ ግን በመከራቸው ጊዜ ከቶ ሊረዷቸው አይችሉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በይሁዳም ከተሞችና በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሄደው ወደሚያጥኑላቸው አማልክት ይጮኻሉ፤ ነገር ግን በመከራቸው ጊዜ ከቶ አያድኑአቸውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በዚያን ጊዜ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ መሥዋዕት ወደሚያቀርቡላቸው ባዕዳን አማልክት ሄደው ርዳታ እንዲያደርጉላቸው ይጮኻሉ፤ ነገር ግን እነርሱ ይህ ጥፋት በሚመጣበት ጊዜ ሊያድኑአቸው አይችሉም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖሩ ሄደው ወደ​ሚ​ያ​ጥ​ኑ​ላ​ቸው፥ በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ ከቶ ወደ​ማ​ያ​ድ​ኗ​ቸው አማ​ል​ክት ይጮ​ኻሉ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 11:12
10 交叉引用  

ይህም ንጉሥ አካዝ በተጨነቀ ጊዜ እግዚአብሔርን መበደል አበዛ።


እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፥ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም።


በጫንቃቸው ላይ አንሥተው ይሸከሙታል በስፍራውም ያደርጉታል፥ በዚያም ይቆማል፥ ከስፍራውም ፈቀቅ አይልም፥ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይሰማውም ከመከራውም አያድነውም።


ሕዝቤ ግን ረስተውኛል ለከንቱ ነገርም ዐጥነዋል፥ ከመንገዱም ተሰናክለዋል ከቀድሞውም ጐዳና ርቀው ወዳልተሠራው ወደ ጠማማው መንገድ ፈቀቅ ብለዋል።


ለአንተ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ናቸውና ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ።


ሰውነታችሁንም ታጠፉ ዘንድ በምድርም አሕዛብ ሁሉ መካከል መረገሚያና መሰደቢያ ትሆኑ ዘንድ፥ ለመቀመጥ በገባችሁባት በግብጽ ምድር ለሌሎች አማልክት በማጠናችሁ በእጃችሁ ሥራ ለምን ታስቈጡኛላችሁ?


እርሱም ይላል፦ አማልክቶቻቸው የት ናቸው? 2 ይታመኑባቸው የነበሩት አማልክት?


የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፥ 2 የመጠጥ ቁርባናቸውንም የወይን ጠጅ የጠጡ? 2 እነርሱ ይነሡ፥ ይርዱአችሁም፥ 2 መጠጊያም ይሁኑላችሁ።


ሄዳችሁ የመረጣችኋቸውን አማልክት ጥሩ፥ እነርሱም በመከራችሁ ጊዜ ያድኑአችሁ።


跟着我们:

广告


广告