Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 10:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ድንኳኔ ተበዘበዘ አውታሬም ሁሉ ተቈረጠ፥ ልጆቼም ከእኔ ወጥተው አይገኙም፥ ድንኳኔንም ከእንግዲህ ወዲህ የሚዘረጋ መጋረጃዎችንም የሚያነሣ የለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ድንኳኔ ፈርሷል፤ ገመዶቹም ሁሉ ተበጣጥሰዋል፤ ልጆቼ ጥለውኝ ሄደዋል፤ ከእንግዲህም አይመለሱም፤ ድንኳኔን ለመትከል፣ መጋረጃዬንም ለመዘርጋት ማንም የቀረ የለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ድንኳኔ ተበዘበዘ አውታሬም ሁሉ ተቈረጠ፤ ልጆቼም ከእኔ ወጥተው አይገኙም፤ ድንኳኔንም ከእንግዲህ ወዲህ የሚዘረጋ መጋረጃዎችንም የሚያነሣ የለም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ድንኳኖቻችን ፈራረሱ፤ መወጠሪያ ገመዶችም ተቈራረጡ፤ ልጆቻችን በሙሉ ተሰደው ስለ ሄዱ፥ ድንኳኖቻችንን መልሶ የሚተክልልንና መጋረጃዎቻችንን የሚሰቅልልን አንድ እንኳ አልቀረም።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ድን​ኳ​ኔም ተበ​ዘ​በዘ፤ አው​ታ​ሬም ሁሉ ተቈ​ረጠ፤ ልጆ​ችና በጎ​ችም የሉም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ለድ​ን​ኳ​ኔም ቦታ የለም ለመ​ን​ጎ​ችም መሰ​ማ​ሪያ የለም፤

参见章节 复制




ኤርምያስ 10:20
12 交叉引用  

የሚያየኝ ሰው ዓይን ከእንግዲህ ወዲህ አያየኝም፥ ዓይንህ በእኔ ላይ ይሆናል፥ እኔም አልገኝም።


ሰማያትን እዘረጋ ዘንድ ምድርንም እመሠርት ዘንድ፥ ጽዮንንም፦ አንቺ ሕዝቤ ነሽ እል ዘንድ ቃሌን በአፍህ አድርጌአለሁ፥ በእጄም ጥላ ጋርጄሃለሁ።


ከወለደቻቸው ልጆች ሁሉ የሚመራት የለም፥ ካሳደገቻቸውም ልጆች ሁሉ እጅዋን የሚይዝ የለም።


የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፥ አትቈጥቢ፥ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ።


እኔ ጤናህን እመልስልሃለሁ ቍስልህንም እፈውሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ማንም የማይሻት፥ የተጣለች ጽዮን ብለው ጠርተውሻልና።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።


መከራ በመከራ ላይ ተጠርቶአል፥ ምድርም ሁሉ ተበዝብዛለችና፥ በድንገትም ድንኳኔ በቅጽበት ዓይንም መጋረጃዎቼ ጠፉ።


ሄ። ስለ ኃጢአትዋ ብዛት እግዚአብሔር አስጨንቆአታልና አስጨናቂዎችዋ ራስ ሆኑ ጠላቶችዋም ተከናወነላቸው፥ ሕፃናቶችዋ በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል።


የሕዝቤንም ሴቶች ከተሸለሙ ቤቶቻቸው አሳደዳችኋቸው፥ ከሕፃናቶቻቸውም ክብሬን ለዘላለም ወሰዳችሁ።


跟着我们:

广告


广告