Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 1:17 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፥ ተነሥም፥ ያዘዝሁህንም ሁሉ ንገራቸው፥ በፊታቸው እንዳላስፈራህ አትፍራቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፤ ተነሥተህም ያዘዝሁን ሁሉ ንገራቸው፤ አትፍራቸውም፤ አለዚያ በፊታቸው አስፈራሃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፥ ተነሥም፥ ያዘዝሁህንም ሁሉ ንገራቸው፤ በእነርሱ ፊት እንዳላስፈራህ አትፍራቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለዚህ ኤርምያስ ሆይ! እኔ የማዝህን ሁሉ እንድትነግራቸው ወደ እነርሱ ለመሄድ ተዘጋጅ፤ እነሆ እነርሱን አትፍራ፤ አለበለዚያ በእነርሱ ፊት የበለጠ እንድትፈራ አደርግሃለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 አንተ ግን ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤ ተነ​ሥም፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ሁሉ ንገ​ራ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ አት​ፍራ። በፊ​ታ​ቸ​ውም አት​ደ​ን​ግጥ አድ​ንህ ዘንድ እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制




ኤርምያስ 1:17
26 交叉引用  

የእግዚአብሔርም እጅ በኤልያስ ላይ ነበረች፤ ወገቡንም አሸንፍጦ ወደ ኢይዝራኤል እስኪገባ ድረስ በአክዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።


የእግዚአብሔርም መልአክ ኤልያስን “ከእርሱ ጋር ውረድ፤ አትፍራውም፤” አለው። ተነሥቶም ከእርሱ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ።


ግያዝንም “ወገብህን ታጠቅ፤ በትሬንም በእጅህ ይዘህ ሂድ፤ ሰውም ብታገኝ ሰላም አትበል፤ እርሱም ሰላም ቢልህ አትመልስለት፤ በትሬንም በሕፃኑ ፊት ላይ አኑር፤” አለው።


ነቢዩም ኤልሳዕ ከነቢያት ልጆች አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለው “ወገብህን ታጥቀህ ይህን የዘይት ማሰሮ በእጅህ ያዝ፤ ወደ ሬማት ዘገለዓድም ሂድ።


እንግዲህ እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ፥ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ተናገረኝ።


እርሱም፦ “በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ነው፤ ሕዝቡን ከግብፅ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ ለእግዚአብሔር ትገዛላችሁ፤” አለ።


ያዘዝሁህን ነገር ሁሉ አንተ ትነግረዋለህ፤ ወንድምህም አሮን የእስራኤልን ልጆች ከአገሩ ይለቅቅ ዘንድ ከፈርዖን ጋር ይናገራል።


እነሆ፥ በምድሪቱ ሁሉ ላይ በይሁዳም ነገሥታት በአለቆችዋና በካህናትዋ ላይ በምድሪቱም ሕዝብ ላይ እንደ ተመሸገ ከተማ እንደ ብረትም ዓምድ እንደ ናስም ቅጥር ዛሬ አድርጌሃለሁ።


አሳዳጆቼ ይፈሩ፥ እኔ ግን አልፈር፥ እነርሱ ይደንግጡ፥ እኔ ግን አልደንግጥ፥ ክፉንም ቀን አምጣባቸው፥ በሁለት እጥፍ ጥፋት አጥፋቸው።


የሚያልም ነቢይ ሕልምን ይናገር፥ ቃሌም ያለበት ቃሌን በእውነት ይናገር። ገለባ ከስንዴ ጋር ምን አለው?


ኤርምያስም ለአለቆችና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ በሰማችሁት ቃል ሁሉ በዚህች ቤትና በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት እናገር ዘንድ እግዚአብሔር ልኮኛል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ቁም፥ በእግዚአብሔርም ቤት ውስጥ ይሰግዱ ዘንድ ለሚመጡት ለይሁዳ ከተሞች ሁሉ ትነግራቸው ዘንድ ያዘዝሁህን ቃል ሁሉ ተናገራቸው፥ አንዲትም ቃል አትጕድል።


የኔርያም ልጅ ባሮክ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ፥ በእግዚአብሔርም ቤት የእግዚአብሔርን ቃል በመጽሐፉ አነበበ።


በጠራሁህ ቀን ቀርበህ፦ አትፍራ አልህ።


ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤


ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ንስሐንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን ለአይሁድና ለግሪክ ሰዎች እየመሰከርሁ በጉባኤም በየቤታችሁም አወራሁላችሁና አስተማርኋችሁ እንጂ፥ ከሚጠቅማችሁ ነገር አንዳች ስንኳ አላስቀረሁባችሁም።


የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፥ ምንም አላስቀረሁባችሁም።


ወንጌልን ብሰብክ እንኳ የምመካበት የለኝም፤ ግድ ደርሶብኝ ነውና፤ ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ።


ነገር ግን እንደምታውቁት በፊልጵስዩስ አስቀድመን መከራ ተቀብለን ተንገላትተንም፥ በብዙ ገድል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እንናገር ዘንድ በአምላካችን ደፈርን።


ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።


跟着我们:

广告


广告