Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 1:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እነሆ፥ እኔ በሰሜን ያሉትን የመንግሥታትን ወገኖች ሁሉ እጠራለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እነርሱም ይመጣሉ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌም በር መግቢያ በዙሪያዋ በቅጥርዋ ሁሉ ላይ በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ላይ ዙፋናቸውን ያስቀምጣሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እነሆ፤ የሰሜን መንግሥታትን ሕዝቦች ሁሉ እጠራለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ንጉሦቻቸው ይመጣሉ፤ ዙፋናቸውን በኢየሩሳሌም መግቢያ በሮች፣ በቅጥሮቿ ዙሪያ ሁሉ፣ በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ይዘረጋሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እነሆ፥ እኔ በሰሜን ያሉትን የመንግሥታትን ወገኖች ሁሉ እጠራለሁ፥ ይላል ጌታ፤ እነርሱም ይመጣሉ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌም በር መግቢያ በዙሪያዋም ባለ ቅጥርዋ ሁሉ ላይ በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ላይ ዙፋናቸውን ያስቀምጣሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በስተ ሰሜን የሚኖሩ ሕዝቦች ወደዚህ እንዲመጡ እጠራለሁ፤ ኢየሩሳሌምንና በዙሪያዋ ያሉትን የይሁዳ ከተሞች አደጋ ጥለው ይይዙአቸዋል፤ ከዚያም በኢየሩሳሌም መግቢያ በር ላይ ዙፋናቸውን ይዘረጋሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እነሆ እኔ በሰ​ሜን ያሉ​ትን የመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቱን ወገ​ኖች ሁሉ እጠ​ራ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ይመ​ጣሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በር መግ​ቢያ በዙ​ሪ​ያ​ዋና በቅ​ጥ​ርዋ ሁሉ ላይ፥ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ሁሉ ላይ ዙፋ​ና​ቸ​ውን ያስ​ቀ​ም​ጣሉ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 1:15
24 交叉引用  

መልካሞቹንም ሸለቆችሽን ሰረገሎች ሞሉባቸው፥ ፈረሰኞችም መቆሚያቸውን በበር ላይ አደረጉ።


የወሬን ድምፅ ስሙ፥ እነሆም፥ የይሁዳን ከተሞች ባድማና የቀበሮ ማደሪያ ያደርጋቸው ዘንድ ከሰሜን ምድር ጽኑ ሽብር መጥቶአል።


ያዕቆብን በልተውታልና፥ ውጠውትማልና፥ አጥፍተውትማልና፥ ማደሪያውንም አፍርሰዋልና በማያውቁህ አሕዛብ ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ መዓትህን አፍስስ።


ዓይናችሁን አንሥታችሁ እነዚህን ከሰሜን የሚመጡትን ተመልከቱ፥ ለአንቺ የተሰጠ መንጋ፥ የተዋበ መንጋሽ፥ ወዴት አለ?


ይጠጡም ዘንድ ጽዋውን ከእጅህ ለመቀበል እንቢ ቢሉ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ፈጽማችሁ ትጠጣላችሁ በላቸው።


ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ ባሪያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፥ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመደነቂያና ለማፍዋጫም ለዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተ፦ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ያለች ባድማ ናት በምትሉአት በዚህች ስፍራ፥ የሚቀመጥባቸው በሌላ፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባድማ በሆኑ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ፥


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ ከእጁም ግዛት በታች ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ አሕዛብም ሁሉ ኢየሩሳሌምንና ከተሞችዋን ሁሉ ይወጉ በነበረ ጊዜ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው።


እነሆ፥ አዝዛለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ወደዚህችም ከተማ እመልሳቸዋለሁ፥ እርስዋንም ይወጋሉ ይይዙአትማል በእሳትም ያቃጥሉአታል፥ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የሌለበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


የባቢሎንም ንጉሥ አለቆች ሁሉ፥ ኤርጌል ሳራስር፥ ሳምጋርናቦ፥ ሠርሰኪም፥ ራፌስ፥ ኤርጌል ሳራስር፥ ራብማግ፥ ከቀሩት ከባቢሎን ንጉሥ አለቆች ሁሉ ጋር ገብተው በመካከለኛው በር ውስጥ ተቀመጡ።


ለአሕዛብ አሰሙና፦ እነሆ፥ ጠባቂዎች ከሩቅ አገር ይመጣሉ፥ በይሁዳም ከተሞች ላይ ይጮኻሉ ብላችሁ በኢየሩሳሌም ላይ አውሩ።


ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና ወደ ጽዮን ዓላማን አንሡ፥ ሽሹ፥ አትዘግዩ።


እንዲህም በላቸው፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ልኬ ባሪያዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን አመጣለሁ፥ ዙፋኑንም እኔ በሸሸግኋቸው በእነዚህ ድንጋዮች ላይ አኖራለሁ፥ እርሱም ማለፊያውን ድንኳኑን በላያቸው ይዘረጋል።


ስለዚህ መዓቴና ቍጣዬ ፈሰሱ፥ በይሁዳም ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ነደዱ፥ ዛሬም እንደ ሆነው ፈረሱ ባድማም ሆኑ።


የግብጽ ልጅ ታፍራለች፥ በሰሜን ሕዝብ እጅ አልፋ ትሰጣለች።


የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እነሆ፥ ሕዝብን ከሩቅ አመጣባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ኃያል ጥንታዊ ሕዝብ ነው፥ ቋንቋቸውንም የማታውቀው የሚናገሩትንም የማታስተውለው ሕዝብ ነው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሕዝብ ከሰሜን አገር ይመጣል፥ ታላቅ ሕዝብም ከምድር ዳርቻ ይነሣል።


ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፥ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይቀመጥባት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


በጽዮን ሴቶችን፥ በይሁዳም ከተሞች ደናግልን አጐሰቈሉ።


የሰሜን አለቆች ሁሉ ሲዶናውያንም ሁሉ ከተገደሉት ጋር ወርደው በዚያ አሉ፥ በኃይላቸውም ያስፈሩ በነበረው ፍርሃት አፍረዋል፥ በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ሳይገረዙ ተኝተዋል፥ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱት ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል።


የሰሜንንም ሠራዊት ከእናንተ ዘንድ አርቃለሁ፥ ወደ በረሃና ወደ ምድረ በዳ፥ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር አድርጌ አሳድደዋለሁ፥ እርሱም ትዕቢትን አድርጎአልና ግማቱ ይወጣል፥ ክርፋቱም ይነሣል አለ።


ዱሪ ፈረሶች ያሉበት ወደ ሰሜን ይወጣል፥ አምባላዮቹም ከእነርሱ በኋላ ይወጣሉ፥ ቅጥልጣሎቹም ወደ ደቡብ ይወጣሉ አለኝ።


跟着我们:

广告


广告