Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 1:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል፦ ኤርምያስ ሆይ፥ ምን ታያለህ? እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም፦ የለውዝ በትር አያለሁ አልሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የእግዚአብሔር ቃል፣ “ኤርምያስ ሆይ፣ ምን ታያለህ?” ሲል ወደ እኔ መጣ። እኔም፣ “የአልሙን በትር አያለሁ” አልሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ደግሞ የጌታ ቃል፦ “ኤርምያስ ሆይ! ምን ታያለህ?” እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም “የለውዝ በትር አያለሁ” አልኩት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔርም “ኤርምያስ ሆይ! የምታየው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “የለውዝ ቅርንጫፍ አያለሁ” አልኩት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ደግሞ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ “ኤር​ም​ያስ ሆይ! ምን ታያ​ለህ?” እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም፥ “የሎሚ በትር አያ​ለሁ” አልሁ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 1:11
11 交叉引用  

ያዕቆብም ልብን ለውዝ ኤርሞን ከሚባሉ እንጨቶች እርጥብ በትርን ወስዶ በበትሮቹ ውስጥ ያለውን ነጭ እንዲታይ ነጭ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው።


ከአፌ የሚወጣ ቃል እንዲሁ ይሆናል፥ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።


እግዚአብሔርም፦ ኤርምያስ ሆይ፥ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦ በለስን አያለሁ፥ እጅግ መልካም የሆነ መልካም በለስ፥ ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ የሆነ ክፉ በለስ ነው አልሁ።


እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ እናገራለሁ የምናገረውም ቃል ይፈጸማል፥ ደግሞም አይዘገይም፥ እናንተ ዓመፀኛ ቤት ሆይ፥ በዘመናችሁ ቃሌን እናገራለሁ እፈጽመውማለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ስለዚህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የምናገረው ቃል ይፈጸማል እንጂ ከቃሌ ሁሉ ደግሞ የሚዘገይ የለም፥ ይላል እግዚአብሔር።


እነሆ ቀኑ፥ እነሆ፥ መጥቶአል፥ ተራህ ወጥቶአል፥ ብትር አብቦአል፥ ትዕቢትም አጅብጅፎአል።


እግዚአብሔርም፦ አሞጽ ሆይ፥ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦ ቱንቢ ነው አልሁ። ጌታም፦ እነሆ፥ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ቱንቢ አደርጋለሁ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ደግሞ አላልፋቸውም፥


እርሱም፦ አሞጽ ሆይ፥ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦ የቃርሚያ ፍሬ የሞላበት ዕንቅብ ነው አልሁት። እግዚአብሔርም አለኝ፦ ፍጻሜ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መጥቶአል፥ ከእንግዲህ ወዲህ ደግሞ አላልፋቸውም።


እርሱም፦ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦ እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነውን መቅረዝ አየሁ፥ የዘይትም ማሰሮ በራሱ ላይ ነበረ፥ ሰባትም መብራቶች ነበሩበት፥ በራሱም ላይ ለነበሩት መብራቶች ሰባት ቧንቧዎች ነበሩአቸው።


እርሱም፦ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦ በራሪ የመጽሐፍ ጥቅልል አያለሁ፥ ርዝመቱ ሀያ ክንድ ወርዱም አሥር ክንድ ነው አልሁ።


እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነች የአሮን በትር አቈጠቈጠች፥ ለመለመችም፥ አበባም አወጣች፥ የበሰለ ለውዝም አፈራች።


跟着我们:

广告


广告