Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 6:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የመድረኩም መሠረት ከጭዋኺው ድምፅ የተነሣ ተናወጠ፥ ቤቱንም ጢስ ሞላበት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከድምፃቸው ጩኸት የተነሣ የመድረኩ መሠረት ተናወጠ፤ ቤተ መቅደሱም በጢስ ተሞላ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከድምፃቸው ጩኸት የተነሣ የመድረኩ መሠረት ተናወጠ፤ ቤተ መቅደሱም በጢስ ተሞላ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከድምፃቸው ጩኸት የተነሣ የቤተ መቅደሱ መድረክ እስከ ሥር መሠረቱ ተናወጠ፤ ቤተ መቅደሱም በጢስ ተሞላ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የመ​ድ​ረ​ኩም መሠ​ረት ከጩ​ኸ​ታ​ቸው ድምፅ የተ​ነሣ ተና​ወጠ፤ ቤቱ​ንም ጢስ ሞላ​በት።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 6:4
12 交叉引用  

መለከቱንም የሚነፉ መዘምራኑም በአንድነት ሆነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ “እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ!” እያሉ በአንድ ቃል ድምጻቸውን ወደ ላይ ከፍ አድርገው በመለከትና በጸናጽል በዜማም ዕቃ ሁሉ እግዚአብሔርን ባመሰገኑ ጊዜ፥ ደመናው የእግዚአብሔርን ቤት ሞላው።


ደመናውም የመገናኛውን ድንኳን ከደነ፥ የእግዚአብሔርም ክብር ማደሪያውን ሞላ።


ሲሄዱም የክንፎቻቸውን ድምፅ እንደ ብዙ ውኃ ድምፅ፥ እንደ ሁሉን የሚችል የአምላክም ድምፅ፥ እንደ ታላቅም ሠራዊት ድምፅ ሆኖ ሰማሁ፥ ሲቆሙም ክንፎቻቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር።


ሁሉንም የሚችል አምላክ እንደሚናገረው ያለ ጽምፅ እንዲሁ የኪሩቤል ክንፎች ድምፅ እስከ ውጭው አደባባይ ድረስ ተሰማ።


መድረኮቹ፥ መቅደሱና በስተ ውስጥ ያለው ክፍል ደጀ ሰላሙም በእንጨት ተለብጠው ነበር፥ በሦስቱም ዙሪያ የዓይነ ርግብ መስኮቶች ነበሩ። መቅደሱም በመድረኩ አንጻር ከመሬት ጀምሮ እስከ መስኮቶቹ ድረስ በእንጨት ተለብጦ ነበር፥ መስኮቶቹም የዓይነ ርግብ ነበሩ፥


በሰሜኑም በር መንገድ በቤቱ ፊት አመጣኝ፥ እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ የእግዚአብሔር ክብር የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶት ነበር፥ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ።


ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፥ እርሱም እንዲህ አለ፦ መድረኮቹ ይናወጡ ዘንድ ጕልላቶቹን ምታ፥ በራሳቸውም ሁሉ ላይ ሰባብራቸው፥ እኔም ከእነርሱ የቀሩትን በሰይፍ እገድላለሁ፥ የሚሸሽ አያመልጥም፥ የሚያመልጥም አይድንም።


በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።


ከእግዚአብሔርም ክብርና ከኃይሉ ጢስ በመቅደሱ ሞላበት፥ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ አንድ እንኳ ወደ መቅደሱ ይገባ ዘንድ አልቻለም።


跟着我们:

广告


广告