Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 5:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጆሮዬ እንዲህ አለ፦ በእውነት ብዙ ታላቅና መልካም ቤት ባድማ ይሆናል፥ የሚቀመጥበትም አይገኝም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ጆሮዬ እየሰማ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “ታላላቅ ቤቶች ወና ይቀራሉ፣ የሚያማምሩም ቤቶች ኗሪ ያጣሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ጆሮዬ እየሰማ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “ታላላቅ ቤቶች ወና ይቀራሉ፤ የሚያማምሩም ቤቶች ነዋሪ ያጣሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እነሆ የሠራዊት አምላክ እንዲህ ብሎ በመሐላ ሲያረጋግጥ ሰምቼአለሁ፦ “የተዋቡ ታላላቅ ቤቶች ሁሉ ፈርሰው ወና ይሆናሉ፤ የሚኖርባቸው ሰውም አይገኝም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ይህ በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጆሮ ተሰ​ም​ቶ​አ​ልና፦ ቤቶች ቢሠሩ ባድማ ይሆ​ናሉ፤ ታላ​ላ​ቅና የሚ​ያ​ምሩ ቤቶ​ችም የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው አይ​ኖ​ርም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 5:9
14 交叉引用  

በኤርምያስ አፍ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፥ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ሰንበትን አገኘች።


በተፈቱም ከተሞች ውስጥ፥ ሰውም በሌለባቸው፥ ክምር ለመሆን በተመደቡ ቤቶች ውስጥ ተቀምጦአልና


እርሱ ከበላ በኋላ ምንም አልተረፈም፥ ስለዚህ በረከቱ አይከናወንለትም።


ይህም ነገር በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተሰማ፦ እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል በእውነት አይሰረይላችሁም ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


የተመሸገችው ከተማ ብቻዋን ሆነች፥ እንደ ምድረ በዳ ሆና የተፈታችና የተተወች መኖሪያ ናት፥ በዚያም ጥጃ ይሰማራል በዚያም ይተኛል ቅርንጫፍዋንም ይበላል።


ባድማ አደርገዋለሁ፥ አይቆረጥም፥ አይኮተኮትም፥ ኵርንችትና እሾህ ይበቅልበታል፥ ዝናብንም እንዳያዘንቡበት ደመናዎችን አዝዛለሁ።


በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።


ድሀውንም ደብድባችኋልና፥ የስንዴውንም ቀረጥ ከእርሱ ወስዳችኋልና ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ሠርታችኋል፥ ነገር ግን አትቀመጡባቸውም፥ ያማሩ የወይን ቦታዎች ተክላችኋል፥ ነገር ግን ከወይን ጠጃቸው አትጠጡም።


እነሆም፥ እግዚአብሔር ያዝዛል፥ ታላቁንም ቤት በማፍረስ፥ ታናሹንም ቤት በመሰባበር ይመታል።


ንጉሡም ተቍኦጣ፥ ጭፍሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።


እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል።


እነሆ፥ እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮኻል፥ የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ፀባዖት ጆሮ ገብቶአል።


跟着我们:

广告


广告