Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 47:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ኀፍረተ ሥጋሽ ይገለጣል እፍረትሽም ይታያል፥ እኔ እበቀላለሁ፥ ለማንም አልራራም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ዕርቃንሽ ይገለጥ፤ ኀፍረትሽ ይታይ፤ እበቀላለሁ፤ እኔ ማንንም ሰው አልተውም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ኀፍረተ ሥጋሽ ይገለጣል እፍረትሽም ይታያል፤ እኔ እበቀላለሁ፥ ለማንም አልራራም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሕዝብ ሁሉ ተራቊተሽ ያዩሻል፤ ኀፍረትሽ ይጋለጣል፤ እኔ ማንንም ሳልምር ሁሉን እበቀላለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ኀፍ​ረ​ትሽ ይገ​ለ​ጣል፤ ውር​ደ​ት​ሽም ይታ​ያል፤ ጽድቅ ከአ​ንቺ ይወ​ሰ​ዳል፤ እን​ዲ​ሁም በአ​ንቺ ፋንታ ሰውን አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጥም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 47:3
27 交叉引用  

የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፤ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ አወቁ፤ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ።


እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፥ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፥ ለግብጽ ጕስቍልና ይነዳቸዋል።


ስለዚህ ጌታ የጽዮንን ቆነጃጅት አናት በቡሀነት ይመታል፥ እግዚአብሔርም ኀፍረተ ሥጋችውን ይገልጣል።


ፈሪ ልብ ላላቸው፦ እነሆ፥ አምላካችሁ በበቀል በእግዚአብሔርም ብድራት ይመጣልና፥ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፥ አትፍሩ በሉአቸው።


በልብሽም፦ እንዲህ ያለ ነገር ስለ ምን ደረሰብኝ? ብትዪ፥ ከኃጢአትሽ ብዛት የተነሣ የልብስሽ ዘርፍ ተገልጦአል ተረከዝሽም ተገፍፎአል።


ስለዚህም የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል።


ፍላጾችን ሳሉ ጋሻዎችንም አዘጋጁ፥ እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ አሳቡ በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ነገሥታት መንፈስ አስነሥቶአል፥ የእግዚብሔር በቀል የመቅደሱ በቀል ነውና።


በከለዳውያንም ምድር ተገድለው፥ በሜዳዋም ላይ ተወግተው ይወድቃሉ።


አጥፊው በባቢሎን ላይ መጥቶባታልና፥ ኃያላኖችዋ ተያዙ፥ ቀስታቸውም ተሰባበረ፥ እግዚአብሔር ፍዳን የሚከፍል አምላክ ነውና፥ ፍዳንም በእርግጥ ይከፍላል።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ ከእነርሱ ጋር ደስ ያለሽን የወደድሻቸውንም ውሽሞችሽ ሁሉ ከጠላሻቸው ሁሉ ጋር እሰበስባቸዋለሁ፥ በአንቺ ላይ በዙሪያሽ እሰበስባቸዋለሁ፥ ኅፍረተ ሥጋሽንም ሁሉ እንዲያዩ በፊታቸው ኀፍረተ ሥጋሽን እገልጣለሁ።


ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።


የጥፋታቸው ቀን ቀርቦአልና፥ 2 የሚመጣባቸውም ነገር ይፈጥናልና 2 እግራቸው ሲሰናከል 2 በቀልና ፍርድ የእኔ ነው።


ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፥ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። ታላቂቱም ባቢሎን የብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።


ሰማይ ሆይ፥ ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ፥ በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፥ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።


跟着我们:

广告


广告